የህወሃት ደጋፊዎች የተቃዋሚዎችን ህዝባዊ ስብሰባ ለመቃወም በአውሮፓ የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን ሰልፍ መጥራታቸው ታወቀ።

ሰኔ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በኖርዌይና በስዊትዘርላንድ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰብ ተግባር ያከናወነው አርበኞች ግንቦት ሰባት ነገ ቅዳሜም ተመሳሳይ  ህዝባዊ ስብሰባ በጀርመን ፍራንክፈርት ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁ የታወቀ ሲሆን ይህን ስብሰባ ለመቃወም መንግስት በኤምባሲው አማካይነት የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል። የተቃውሞ  ሰልፉን ለሚወጡ የመንግስት ደጋፊዎችም ዛሬ  ምሽት በፍራንክፈርት ከተማ ሆቴል ተይዞ የእራት ግብዣ እንደተሰናዳም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።