.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ለ2016 አም የሚሸልመው አፍሪካዊ መሪ ማጣቱን ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በአፍሪካ የመልካም አስተዳደር ዴሞክራሲ እንዲጎለብት አስተዋጽዖን ላደረጉ መሪዎች የአምስት ሚሊዮን ዶላር አመታዊ ሽልማት የሚሰጠው ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ለሁለተኛ ተከታታይ አመት ለ2016 አም የሚሸልመው መሪ ማጣቱን ማክሰኞ ገለጸ። በፋውንዴሽኑ የሽልማቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሳሊም አህመድ ሳሊም ለ2016 አም ለሽልማቱ የሚበቁ የቀድሞ የአህጉሪቱ መሪዎችን ለመምረጥ በተደረገ ስራ አንድም መሪ መስፈርቱን ሊያሟላ እንዳልቻለ ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። በዴሞክራሲያዊ ...

Read More »

በቴክኒክ ችግር በህንድ ለማረፍ የተገደደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) ቅዳሜ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር በህንድ ለማረፍ ተገዶ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንድ ቀን መዘግየት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ማቅናቱን የህንድ የአቪየሽን ባለስልጣናት ገለጹ። 255 መንገደኞችን እና የበረራ ባለሙያዎችን ይዞ ከሙምባይ ወደ ካትማንዱ ከተማ በማቅናት ላይ እንዳለ ፓይለቱ (የአውሮፕላኑ አብራሪ) የቴከኒክ ችግር እንዳጋጠመውና ለማረፍ መገደዱን ለትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት ማድረጉን ኢንዲያ ቱዴይ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ET8806 የሚል ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የኮሌራ በሽታ በመዛመት ላይ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በበርካታ ዞኖች የኮሌራ በሽታ በመዛመት ላይ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ይፋ አደረገ። ቢርቆድ፣ ቀብሪደሃር፣ ደገሃቡር፣ ሽኮሽና፣ እና ጉናጉዱ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች እየተዛመተ ባለው በዚሁ ተላላፊ በሽታ እስካሁን ድረስ በትንሹ 103 ሰዎች መያዛቸውን የሶማሌ ክልል የጤና ባለሙያዎች ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ለሁለተኛ ጊዜ በክልሉ ተከስቶ የሚገኘው ...

Read More »

የነጃሺ ኢትዮ-ተርኪሽ ትምህርት ቤቶች ለጀርመን ባለሃብቶች በሽያጭ ተዘዋወሩ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ለቱርክ ተላልፈው እንደሚሰጡ ቃል የገባችውና በቱርክ መንግስት ጥያቄ ቀርቦባቸው የነበሩ የነጃሺ ኢትዮ-ተርኪሽ ትምህርት ቤቶች ለጀርመን ባለሃብቶች በሽያጭ ተዘዋወሩ። ቱርክ ትምህርት ቤቶቹ አሸባሪ ድርጅት ብላ ከፈረጀችው ከጉለን ንቅናቄ ድርጅት ጋር ግንኙነት ያለው ነው በማለት ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶቹን አስተላልፋ እንድትሰጣት በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ይታወሳል። በቅርቡ በቱርክ ጉብኝትን ያደረጉት የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መንግስት ጥያቄ ...

Read More »

አሜሪካ አልሸባብን ለመውጋት አዲስ እቅድ መንደፏ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) አሜሪካ የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አሸባብን ለመዋጋት አዲስ የፖሊሲ አቅጣጫ መንደፏን የሃገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት አስታወቁ። የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ያዘጋጀው ይኸው የፖሊሲ አቅጣጫ የአሜሪካ ወታደሮች በቅርበት በታጣቂ ሃይሉ ላይ ጥቃትን እንዲፈጽሙ የሚጠቁም ሲሆን፣ አሜሪካ ለሶማሊያ መንግስት የምትሰጠው ወታደራዊ እገዛም እንዲጠናከር እቅድ መኖሩን ወታደራዊ ሃላፊዎቿ ለVOA እንግሊዝኛው ክፍል ገልጸዋል። በኢራቅ በሶሪያ የሚካሄዱ ጥቃቶች ተጠናክረው በአዲስ መልክ ...

Read More »

የአድዋን ድል በማስመልከት ለሃገራቸው አስተዋጽዖ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን ሽልማት ተበረከተ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) የአድዋን ድል በማስመለከት በአሜሪካ ዋሽንግተን በተካሄደው ስነ-ስርዓት ለሃገራቸው አስተዋጽዖ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን ሽልማት ተበረከተ። “የዳግማዊ ምኒሊክ ሜዳሊያ” በሚል ስያሜ የተሰጠውን ሽልማት ያገኙ ኮማንደር ጣሰው ደስታ፣ አቶ ኤሊያስ ወንድሙ እንዲሁም አቶ ፈንታሁን ጥሩነህን ጨምሮ 10 ያህል ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሃገር ዜጎች መሆናቸውም ተመልክቷል። በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ የካቲቲ 18 ፥ 2009 በዋሽንግተን ዲሲ አርሚ ኒቪ ክለቡ በተካሄደው ስነስርዓት ላይ ...

Read More »

በመተማ ወረዳ በሚደረገው የጦር መሳሪያ ገፈፋ በርካታ አርሶአደሮች ሲታሰሩ ብዙዎች ደግሞ ጫካ ገብተዋል

የካቲት ፳ ( ሃያ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር በመተማ ወረዳ ሻሽዬ ቀበሌ የጦር መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ከተጠየቁት መካከል በርካቶች መሳሪያችንን አናስረክብም በማለታቸው ሲተሰሩ፣ ሌሎች ደግሞ ጫካ ገብተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በአካባቢው የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት ህዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቀ ይገኛል። በቀበሌው ውስጥ ታዋቂ ከሆኑት ባለሃብቶች መካከል ሼህ አዲስ፣ አቶ ደስታው፣ አንደበት ወርቃያሁና ሌሎችም የተያዙ ሲሆን፣ ባሎቻቸው ጫካ የገቡባቸው ...

Read More »

በኦሮምያና ሶማሊ ድንበር ባለው ግጭት ከ200 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አስታወቀ

የካቲት ፳ ( ሃያ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያና ሶማሊ ክልል አዋሳኝ ድንበር ላይ ባለው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከሶማሊ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በማበር በባሌ፣ ሳውና እና ቄለም ወለጋ 19 ገድለው 13 ማቁሰላቸውን፣ የኦሮሞ ተወላጆች በወሰዱት የአጸፋ መልስ ደግሞ 35 የፈደራል እና የልዩ ጦር አባላት መገደላቸውን፣ ከ 50 ያላነሱ ደግሞ መቁሰላቸውን እንዲሁም በጉጂ፣ ቦረና፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ...

Read More »

በባህርዳር የሚፈጸመውን ጥቃት ምንጩን ማወቅ አለመቻላቸውን ከንቲባው ተናገሩ

የካቲት ፳ ( ሃያ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባህር ዳር ከተማ አዲሱ አስተዳደር ቅዳሜ ከተወሰኑ የከተማዋ ማህበረሰብ ጋር በሙሉዓለም አዳራሽ ባደረጉት ውይይት፣ ከንቲባው አቶ አየነው በላይ፣ “ በከተማዋ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ቢኖሩም የከተማዋ ደህንነቶችም ሆኑ የጸጥታ አካላት ሊደርሱባቸው አለመቻላቸውን፣ ይህም የከተማዋን አስተዳደርና የጸጥታ ዘርፍ አካላት ግራ ከማጋባት አልፎ ማስጨንቁን ተናግረዋል። በባህር ዳር ከተማ በየጊዜው የተካሄዱት የቦምብ ፍንዳታ ጥቃቶችና ...

Read More »

በጅንካ ታስረው የሚገኙት የህሊና እስረኞች የረሃብ አድማ ጀመሩ

የካቲት ፳ ( ሃያ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ከህዳር 4 /2009 ዓም ጀምሮ ክስ ሳይመሰረትባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አራት የኅሊና እስረኞች ከ የካቲት 20 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የረሃብ አድማ በማድረግ ላይ ናቸው። እስረኞች ይህን የረሃብ አድማ ለማድረግ የወሰኑት ከዞን እስከ ፌዴራል ኮማንድ ፖስት ድረስ ጉዳያቸው እንዲታይላቸው፣ በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም፣ እንዲሁም ፓርቲያቸው ...

Read More »