ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ማሻሻያ አድርገውበት በድጋሚ በስድስት ሃገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እገዳ ለሁለተኛ ጊዜ በፌዴራል ዳኞች ታገደ። ፕሬዚደንቱ ሃሙስ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ያወጡትን የጉዞ እገዳ የሜሪላንድና የሃዋይ ግዛቶች የፌደራል ዳኞች ውድቅ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፈውበታል። ፕሬዚደንቱ በድጋሚ ያስታወቁት ደንብ ሃገሪቱን ከሽብር ጥቃት ለመታደርግ ነው ቢሉም የሁለቱ ግዛቶች ዳኞች እገዳው አስተማማኝ አለመሆኑን እና አንድን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የጎንደር ፖሊስ አዛዥና የኮማንድ ፖስቱ አባል ታሰሩ
ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2009) የጎንደር ከተማ ፖሊስ አዛዥ እና የኮማንድ ፖስቱ አባል ታሰሩ። የጎንደር ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር አሰፋ ሹሜ ረቡዕ መጋቢት 6 ፥ 2009 መታሰራቸው ቢረጋገጥም፣ ስለታሰሩበት ምክንያት የታወቀ ነገር የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ኮማንድ ፖስት ስር መቀጠላቸው የተገለጸው ኮማንደር አሰፋ ሹሜ፣ ረቡዕ ከስራና ስልጣናቸው ተነስተው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰራተኞች በቆሼ ለደረሰው አደጋ መስተዳድሩን ተጠያቂ አደረጉ
መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ ቆሼ ተብሎ በሚታወቀው የቆሻሻ መጣያ ስፍራ በመሙላቱ ምክንያት፣ ቆሻሻ መጣያ ስፍራውን በመዝጋት ወደ ታሪካዊ መናፈሻነት ለመቀየር እየሰራ መሆኑንና ሥራውም ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ከአራት ዓመት በፊት በወቅቱ ከንቲባ በነበሩት በኩማ ደመቅሳ ሪፖርት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፉት አራት ዓመታት ግን ቆሻሻ መድፊያውን በተግባር መዝጋት ባለመቻሉ የአሁኑ አደጋ መከሰቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ተጨማሪ ጥቃት መፈጸማቸውን ገለጹ
መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋዮቹ ለኢሳት እንደተናገሩት በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን፣ የዚሁ የዘመቻ አካል የሆነ ጥቃት በአምባጊዮርጊስ ከተማ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ከምሽቱ 6 ሰአት አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት የወረዳው እስር ቤት ከጥቅም ውጭ መሆኑን ተናግረዋል። አምባጊዮርጊስ የመከላከያ ሰራዊት እና የሚሊሺያ አባላት በብዛት የሚገኙበት ከተማ ሆኖ ሳለ ...
Read More »መድረክ ከኢህአዴግ ጋር ብቻ ለመነጋገር ሃሳብ አቀረበ
መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እየተደረገ ባለው 22 ፓርቲዎች የፖለቲካ ድርድር መድረክ ላይ፣ የመድረኩ ተወካይ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ድርድሩ በኢህአዴግና በመድረክ መካከል ብቻ ሊካሄድ ይገባል ብለዋል። ኢህአዴግ ገዢ ፓርቲ በመሆኑ፣ መድረክ ደግሞ የአገሪቱ ዋነኛ ፓርቲ በመሆኑ ድርድሩ በሁለቱ መካከል ሊሆን ይገባል ሌሎች ፓርቲዎች ግን በተሳፊነት ብቻ መቅረብ አለባቸው ብለዋል። ኢህአዴግ በበኩለ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና በፓርላማ ወንበር ...
Read More »ለወራት በእስር ላይ የነበሩት መምህር አለማየሁ መኮንን ተፈቱ
መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወታደራዊ እዙ ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ የቆዩት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ምክትል ሊቀመንበር መምህር ዓለማዬሁ መኮንን በ3000 /ሦስት ሺህ) ብር ዋስ ተፈተዋል፡፡ አቶ አለማየሁ ከእርሳቸው ጋር የነበሩት ሌሎች 10 እስረኞች ሲለቀቁ እርሳቸው ብቻ ታስረው እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር። በሌላ በኩል በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ወልደሃና መጋቢት ...
Read More »በቆሼ በደረሰው አደጋ ሟቾችን በፍጥነት የማውጣት ስራ ባለመሰራቱ አሰከሬን መሽተት ጀምሯል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
መጋቢት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቆሸ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ፣ ሟቾችን በፍጥነት ለማውጣት ባለመቻሉ የአስከሬኑ ሽታ ከቆሻሻ ሽታው ጋር ተደማምሮ ፍለጋውን አስቸጋሪ አድርጎታል። የኢህአዴግ አገዛዝ ሁለት ስካቫተር እና 3 አምቡላንስ መኪኖችን ብቻ በማቅረቡ፣ ፍለጋው እንዲጓተትና በህይወት የተረፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ እንዲስተጓጎል እያደረገ ነው የሚል ትችት ከቀረበበት በሁዋላ፣ ትናንት ሁለት ተጨማሪ ስካቫተር መኪኖችን ...
Read More »አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከስልጣናቸው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል
መጋቢት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ስብሰባ ከመጋቢት 4/2009 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ሃሙስ በሚደረገው ስብሰባ ጉባዔው አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከስልጣን በማንሳት፣ አማራን በመዝለፍና በማዋረድ የሚታወቁትን አቶ አለምነው መኮንንን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አንዳንድ የካቢኔ አባላት ህዝቡን ለማረጋጋት አቶ ገዱ ለ3 ወራት ያክል በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ሃሳብ ያቀረቡ ቢሆንም፣ እስካሁን ባለው ...
Read More »ከዋልድባ ገዳም ታፍነው የተወሰዱት አባ ገብረኢየሱስ እስካሁን ያሉበት አድራሻ አልታወቀም
መጋቢት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጥንታዊው እና ታሪካዊው የዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ስም ውድመት እንዲደርስ መደረጉን በመቃወም ባለባቸው ሃይማኖታዊ ግዴታዎች ገዳሙን በመወከል ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአካልና በደብዳቤ ያቀረቡት አባ ገብረኢየሱስ በገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም። በገዳሙ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎችን ሲሰጡ የነበሩትን የአባ ገብረኢየሱስን በገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ታፍነው ...
Read More »የታይላንድ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ የተጓጓዘው የአውራሪስ ቀንድ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላትን ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆናቸውን ገለጹ
ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2009) የታይላንድ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ ከተጓጓዘውና በሃገሪቱ አለም አቀፍ አውሮፓላን ማረፊያ ማክሰኞ ከተያዘው 21 የአውራሪስ ቀንድ ዝውውር ጋር የተገናኙ አካላት ለማወቅ ምርመራ መጀመራቸውን አስታወቁ። አምስት ሚሊዮን ዶላር (ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ) ግምት ያለው ይኸው የአውራሪስ ቀንድ በአየር ማረፊያው በጥርጣሬ በተካሄደ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ቢቢሲ ዘግቧል። መነሻውን ከኢትዮጵያ ያደረገው ሻንጣ ለመረከብ በአየር ማረፊያው ከቬይትናምና ከካምቦዲያ የተጓዙ ሁለት ...
Read More »