ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2009) በአማራ ክልል በሶስት ዞኖች ስር በሚገኙ 12 ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማትና ትውከት በሽታ ተከስቶ ከ250 በላይ ሰዎች ለህመም መዳረጋቸው የክልሉ ጤና ቢሮ አረጋገጠ። በሃሙስ ዘገባችን ምንጮች በዚሁ የበሽታ ወረርሽኝ በትንሹ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን ማቅረባችን የሚታወስ ሲሆን፣ የክልሉ ጤና ቢሮ የሰጠው ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የለም። በሽታው በአሁኑ ወቅት በ 12 ወረዳዎች መከሰቱን የገለጸው የክልሉ ጤና ቢሮ 47 ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአፍሪካ ቀንድ የኮሌራ በሽታ ሊስፋፋ እንደሚችል ወርልድ ቪዥን አስታወቀ
ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ያለው የድርቅ አደጋ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት እንዲሁም የኮሌራ በሽታ ሊስፋፋ እንደሚችል ወርልድ ቪዥን ግብረ ሰናይ ድርጅት አሳስቧል። በኢትዮጵያ እንዲሁም በጎረቤት ሶማሊያና፣ ደቡብ ሱዳን በመዛመት ላይ ያለው በሽታ ኮሌራ ነው ሲል ድርጅቱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ በቅርቡ ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት የተመረጡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሽታው ኮሌራ ...
Read More »በአዲስ አበባ ኤች አይ ቪ ኤድስ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱንና የበሽታው ስርጭት በዚሁ ከቀጠለ ወረርሽኝ ድረጃ ሊደርስ እንደሚችል ተገለጸ። በከተማዋ በርካታ መዝናኛዎች መስፋፋታቸው እና ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት ለበሽታው ስርጭት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ዋቢ በማድረግ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የበሽታው ስርጭት እየጨመረ መምጣትን ተከትሎ በአዳማ ከተማ ሃገር አቀፍ ...
Read More »ኢትዮጵያ የሶማሊላንድን ወደብ ለመጠቀም ድርድር እያካሄደች ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2009) ኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ወደብን ለመጠቀም የሚያስችል አዲስ ድርድር ወደቡን ከተረከበው የዱባይ ኩባንያ ጋር መጀመሯን የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ አስተዳደር የሆነችው የሶማሊላንድ ባለስልጣናት አስታወቁ። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ወደቡን በጋራ ለማልማት ከሶማሊላንድ ጋር ረጅም ጊዜ የፈጀ ድርድርን ብታካሄድም ስምምነት ሳይደረስ መቅረቱ ይታወሳል። ከኢትዮጵያ ጋር የተጀመረው ድርድር ዕልባት አለማግኘቱን ተከትሎ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ወደቡን ዲፒ ወርልድ ለተሰኘ የዱባይ ኩባንያ አስረክበዋል። ...
Read More »የባህርዳር ከነማ ከትግራይ ዎልዋሎ ክለብ ጋር ግጥሚያ እንዲያደርግ በግዳጅ ወደ አዲግራት መወሰዱ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009) የባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ያለ ፍላጎታቸው ከትግራይ ውልዋሎ ክለብ ጋር ግጥሚያ እንዲያደርጉ በግዳጅ ወደ አዲግራት መወሰዳቸው ተገለጸ። የባህርዳር ከነማ ክለብ ከመቀሌው አቻው ጋር ሲጫወት ከዚህ ቀደም በደጋፊዎች በደል ቢደርስበትም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፍርደግምድል ውሳኔ ተወስኖብኛል በሚል ሲቃወም ቆይቷል። ይህንኑ ውሳኔ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ...
Read More »ኢትዮጵያ ለሚቀጥለው አመት ከቀረበው በጀት የ54 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዳጋጠማት ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009) ለ2010 አም በጀት ከቀረበው የ321 ቢሊዮን ብር ውስጥ የ54 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ማጋጠሙን የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ሃሙስ ገለጸ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተያዘው ሳምንት በሃምሌ ወር ለሚጀምረው ቀጣዩ በጀት 321 ቢሊዮን ብር በጀት ማቅረቡ ይታወሳል። በዚሁ በጀት ዙሪያ ለፓርላማ ማብራሪያ ያቀረበቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ለበጀቱ ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ የ54 ቢሊዮን ብር የበጀት ...
Read More »ብሪታኒያ ለደሃ ሃገራት የምትሰጠው አለም አቀፍ ድጋፍ በተፎካካሪ በፓርቲዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኖ ቀረበ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009) በብሪታኒያ ሃሙስ የፓርላማ አባላትን ለመምረጥ በተካሄደ ምርጫ ሃገሪቱ ለደሃ ሃገራት የምትሰጠው አለም አቀፍ ድጋፍ በፓርቲዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኖ ቀረበ። የብሪታኒያ መንግስት ለበርካታ ደሃ ሃገራት ሲሰጥ የነበረው ይኸው ድጋፍ የሰብዓዊ መብትን ቅድሚያ አልሰጠም እንዲሁም ድጋፍ ለታለመለት አላማ አልዋለም የሚል ትችት ሲቀርብበት መቆየቱ ይታወሳል። ይኸው የሃገሪቱ አለም አቀፍ ዕርዳታ ሃሙስ ሲካሄድ በዋለው ምርጫ በኮንሰርቫቲቭ፣ በሌቨርና በሌሎች የፖለቲካ ...
Read More »በኬንያ ህወገጥ የተባሉ 40 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009) የኬንያ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ 40 ኢትዮጵያውያን ሃሙስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ። የኒጅሩ አስተዳደር ኮማንደር ፓርቲክ ምዋምባ ኢትዮጵያውያኑ በአስተዳደሩ ስር በምትገኘው የቃዬሌ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ እንዳሉ በነዋሪዎች በተደረገ ጥቆማ ሊያዙ መቻላቸውን እንደገለጹ ዘስታር የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧልል። በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብተዋል የተባሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከ10 እስከ 25 ...
Read More »በሲዳማና በወላይታ ድንበሮች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ እየተሰራ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
ሰኔ ፩ ( አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአመታት በፊት በወላይታና ሲዳማ ድንበሮች መካከል ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ ተነስቶ የነበረው ግጭት፣ የብዙ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ፣ ግችቱ በድጋሜ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ነዋሪዎች አስጠንቅቀዋል። ከአመታት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭት 19 ሰዎች ሞተው፣ 65 ቤቶች ተቃጥለው የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ገብቶ እንዳስቆመውና አወዛጋቢ የተባሉ ቦታዎች በወላይታ ዞን ክልል እንዲቆይ ተደርጎ ግጭቱ ...
Read More »ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የዲያስፖራ ቀን ለማክበር እንቅስቃሴ ተጀምሯል
ሰኔ ፩ ( አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን ከሃረር እንደዘገበው የዲያስፖራውን ቀን ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 24 የሚቆይ የዲያስፖራ ቀን በሃረር ለማክበር ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ዝግጅት እየተደረገ ነው። ወኪላችን እንደሚለው በአካባቢው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ባለበት እንዲሁም ድርቅ በገባበት ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ በአል ማክበር አሳዛኝ ነው። የዲያስፖራ አባላትን በቤትና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በመደለል ወደ አገር ውስጥ ...
Read More »