ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ካለምንም ምትክ ቦታና ካሳ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን እና የግጦሽ ማሳዎችን በልማት ስም መነጠቃቸውን የተቃወሙት አርብቶ አደሮች በገፍ ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቀዋል። በኩራዝ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የሃመር፣ ጸሚያ፣ ዳሰነች፣ ናያቶም፣ ሙርሲ፣ ኤርቦሬ፣ ማና ብሄረሰብ አባላት የግፍ እስራቱ ተጠቂዎች ሆነዋል። በዞኑ በሚገኙ የወረዳ እስርቤቶችና ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ለሦስተኛ ጊዜ ተቃጠለ ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮልፈ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ካራቆሬ በሚባለው አካባቢ ዘይት ቤት በመባል በሚጠራው ግቢ የሚገኘው ‹‹ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ›› ከጥቅምት 05/09 ጀምሮ እስከ ሰኔ 3 ቀን 20099 ዓ.ም ድረስ ባሉት 9 ወራት ለሦስተኛ ጊዜ መቃጠሉን ዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 8 ሰዓት ...
Read More »በቆሼ አደጋ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸው ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ተጓትቶብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ
ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ደርሶ ከነበረው የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ጋር በተገናኘ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸው ከ20 በላይ ሰዎች ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ተጓትቶብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ 23 የሚሆኑት ሰዎች በስፍራው ይኖሩ ስለመሆናቸው አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው እንዲመጡ መታዘዛቸውን ገልጿል። ከአደጋው የተረፉት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች ጉዳቱ ...
Read More »ኢትዮጵያ ተመድ የእርዳታ ምግብ አቅርቦት በተያዘው ወር ሊያልቅ ይችላል ሲል የሰጠውን ማሳሰቢያ አስተባበለች
ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሃገሪቱ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የተጋለጡ ወደ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች የሚያስፈልጋቸው የምግብ አቅርቦት በተያዘው ወር ሊያልቅ ይችላል ሲል የሰጠውን ማሳሰቢያ አስተባበለች። አለም አቀፍ ተቋማትና የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም ተረጂዎች ከሰኔ ወር መገባደጃ ጀምሮ የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ እንደማይኖር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። ይሁንና በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽን የሰጡ የመንግስት ባለስልጣናት በችግሩ ምክንያት ...
Read More »የቂሊንጦ እስር ቤት አቃጥለዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው ታሳሪዎች የክስ ቻርጁን ወደ ዳኞችና አቃቢያነ ህጎች ወረወሩ
ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009) ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በማቃጠል ጉዳት አድርሰዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች የታደላቸውን ክስ ቻርጅ ወደ ጃኞቹና አቃቢያነ ህጎቹ በመወርወር እንዲሁም በድምፅ ተቃውሟቸውን ማቅረባቸው ተገለጸ። ፍ/ቤቱም ሁኔታውን ተከትሎ የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል። የፍርድ ውሳኔው የተላለፈባቸው ተከሳሾች በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተገናኘ ተደራራቢ ክስ ተመስርቶባቸው ከነበሩ 121 እስረኞች መካከል መሆናቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ሰሞኑን ...
Read More »የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ስራአስኪያጅ አባ ሃይለማርያም የመመረቂያ ጽሁፋቸውን ከሌላ ተማሪ ጽሁፍ ገልብጠው የዶክትሬት ዲግሪ እንዳገኙ ተጋለጠ
ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ፣ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የስራ አስፈጻሚ አባልና በቅርቡ ደግሞ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት “ዕጩ ቆሞስ” ኾነው የተሾሙት አባ ሃይለማርያም መለሰ ፣ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 ለደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ባቀረቡት የዶክትሬት የመመረቂያ ጽሀፍ ላይ ፣ ከዚህ ቀደም በአንድ ኢትዮጵያዊ ቄስ የተጻፈውን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ...
Read More »ብ/ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና የአጋዚ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆኑ
ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ የነበሩት ብ/ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና የአጋዚ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆነው ሲሸሙ ጄል ገብረመድህን በቅጽል ስማቸው ወዲ ነጮ ደግሞ ምክትል ሆነዋል። ብ/ ጄኔራል ጌታቸው በኦሮምያ ከነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ግምገማ ቀርቦባቸው ነበር። በኢትዮጵያ ውስጥ በጭካኔውና በፈጸማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚታወቀውን የአጋዚ ክፍለጦር እንዲመሩ መደረጉ በጄኔራሉ ላይ ቅሬታ ...
Read More »በአማራ ክልል የኮሌራ ወረሽኝ እየተስፋፋ ነው
ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በንጹህ መጠጥ ውሃ እና የምግብ መበከል ምክንያቶች የሚከሰተው የኮሌራ ወረሽኝ በደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ በምእራብ ጎጃም ውስጥ በሚገኙ 12 ወረዳዎች አድማሱን እያሰፋ ነው። እስካሁን ድረስም ከ252 በላይ ነዋሪዎች በአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት መጠቃታቸውን የክልሉ የጤና ቢሮ አስታውቋል። አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት አተት በመባል በሚታወቀው የኮሌራ በሽታ ተጠቂ የሆኑ 47 ታካሚዎች ...
Read More »ነዋሪነቱ በስዊትዘርላንድ ሲዮን ከተማ የነበረውና በበርካታ ሀገራዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ጉልህ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቀው ኢትዮጵያዊ አቶ መኳንንት መታፈሪያ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መኳንንት መታፈሪያ የሀገሩንና የወገኑን ጉዳይ እንደግል ጉዳዩ በመወሰድ ለኢትዮጵያዊያን የመብት ትግል ያለመታከት የዜግነት ድርሻውን ሲወጣ የኖረ ጎልማሳ ነበር። አቶ መኳንንት ከሰብአዊና ማህበራዊ ትጋቶቹ በተጨማሪ በሚኖርበት ከተማ የኢሳትን ቻፕተር በመመስረት ድጋፍ በማስተባበርና እራሱም በመደገፍ ሊረሳ የማይችል ተግባር ሲፈጽም እንደነበረ የስዊትዘርላንድ ኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ለኢሳት በላከው የሀዘን መግለጫ ጠቅሷል። የአቶ ...
Read More »ኢትዮጵያ እንደ መንግስት መቀጠል ካቃታቸው 15 ሃገራት እንዷ መሆኗ አንድ አለም አቀፍ ጥናት አመለከተ
ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ያለመረጋጋት ከሚታይባቸውና እንደ መንግስት መቀጠል ካቃታቸው መካከል ከቀዳሚዎቹ 15 ሃገራት እንዷ መሆኗ አንድ አለም አቀፍ ጥናት አመለከተ። መቀመጫውን በዚሁ በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገውና ፈንድ ፎር ፒስ የተባለው ተቋም በ2017 ይፋ ባደረገው ጥናት የኢትዮጵያ መንግስት ያለመረጋጋት የሚታይበትና ሃገርን አንድ አድርጎ ለመምራት በማይችልበት አቋም ላይ ይገኛል ብሏል። በአለም አቀፍ ተቋሙ መመዘኛ መሰረት እንደ መንግስት መቀጠል አለመቻል፣ ማህበራዊ፣ ...
Read More »