.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወለድ አርሶ አደሩን እያሰደደ ነው፡፡

ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ አርሶአደሮች ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የራሱ ድርጅት ከሆነው ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በምህጻረ ቃል አብቁተ በግድ ተበድረው እንዲወስዱ በማድረጉ፣ አርሶአደሮች በወለድ አመላለስ እና በምርታመነት ችግር ምክንያት መሬታቸው እና ከብቶቻቸው እየተወረሱባቸው እንደሚገኙ እየተናገሩ ነው። በምዕራብ አማራ በሚገኙ 73 ወረዳዎች አምና 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በግዳጅ በወሰዱት ብድር ምክንያት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር በጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዘ።

ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ ስፖርት አዘጋጅ በመሆን የሚሰራውን ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒን የመስራት ነጻነት በሚጋፋ መልኩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር የጻፈውን ደብዳቤ ተከትሎ ማህበሩ በአባላቱ ሥም የተቃውሞ መልስ ጽፏል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም በብስራት ሬዲዮ ጣቢያ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን የሚኮንኑ እና ሚዛናዊነት ...

Read More »

አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለአራት አገራት 639 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ዕርዳታ ለመስጠት ወሳኔ አሳለፈ:: ልገሳው ኢትዮጵያን አያካትትም።

ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ639 ሚሊዮን ዶላር በጀት አጽድቋል። ይህም አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አራት አገራት እንደሚውል የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (USAID) አስታውቋል። ከአራቱ አገራት አገራት ውስጥ በዘንድሮው ዓመት ኢትዮጵያ አልተካተተችም። ናይጀሪያ121 ሚሊዮን፣ ደቡብ ሱዳን 199፣ ሶማሊያ 126 ሚሊዮን እና የመን 191 ሚሊዮን ዶላር እያንዳንዳቸው እንደሚያገኙ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት 39 የፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰባዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ጥሪ አቀረቡ

ኢሳት ዜና ( ሃምሌ 4, 2009 ) የአውሮፓ ህብረት 39 የፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰባዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ጥሪ አቀረቡ ። የፓርላማ አባላቱ የፈረሙት ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ ያለው የሰባዊ መብት ረገጣ ሙሉ በሙሉ መጣራት ይኖርበታል ።በአገዛዙ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የሰባዊ መብት ኮሚሽን ተካሄደ የተባለው የምርመራ ሪፖርት የገለልተኛነት ጥያቄ እንዳለበትም የፓርላማ አባላቱ ገልጸዋል ። የአውሮፓ ህብረት የ39ኙ የፓርላማ አባላት ፊርማ ያለበት ...

Read More »

ለአበባ እርሻ የመሬት እጦት መኖሩን ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ገለጹ

ኢሳት ዜና (ሀምሌ 4 ,2009 )በኢትዮጵያ የአበባ ኢንቨስትመንት በመሬት አቅርቦት እጥረት መገታቱን ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላማ ገለጹ ። በኢህአዴግ ፓርላማ የ2010 በጀትን ለማጽደቅ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪኣም ደሳለኝ የሃገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ መሆኑን ተናግረዋል ። ችግሩን እንዲጎላ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል በአበባ ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ምክንያት የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ፌደራል መንግስት ያረገው ጥረት የክልል መስተዳደሮች መሬት አናቀርብም በማለታቸው ተስተጓጉሏል ሲሉ ስሞታ አቅርበዋል ...

Read More »

በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 4 ,2009 ) የአዲስ አበባ አስተዳደር በመካከለኛ ገቢ ለሚኖሩ ሰዎች በገነባቸው የኮንደሚኒየም ቤቶች ላይ ያደገው የዋጋ ጭማሪ ተመዝጋቢዎችን ማስቆጣቱ ተነገረ ። አስተዳደሩ የ972 ቤቶችን እጣ ከማውጣቱ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ መካከለኛ ገቢ ላላቸው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋን በፊት ከታቀደው 56 በመቶ ጭማሪ አድርጓል ። ለቤቶቹ 11 ሺህ 88 ተመዝጋቢዎች የነበሩ ሲሆን ሁሉም ሙሉ በሙሉ የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ...

Read More »

በእስራኤል ኢትዮጵያውያን ከቀያቸው ተፈናቀሉ

(ኢሳት ዜና –  ሐምሌ 4/2009)  በእስራኤል ማቫሰርት ጺዮን አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ናቸው ከቀያችን አላግባብ ተፈናቅለናል ሲሉ በዋና ከተማዋ ቴልአቪቭ በመውጣት ድምጻቸውን ያስሙት መኖሪያቸውን እንዲለቁ የተሰጣቸው ከሁለት ወራት ያነሰ የጊዜ ገደብም ቢሆን አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ ተናግረዋል። ለተፈናቃዮቹ ጥብቅና የቆመው አካልም የተወሰደው እርምጃ ትክክል አይደለም ሲል ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርቧል። እንደተቆርቋሪው አካል አገላልጽ ከሆነም ለተፈናቃዮቹ መዘጋጃ የሚሆን ተጨማሪ የሶስት አመት የጊዜ ...

Read More »

በመላ አገሪቱ ያሉ ነጋዴዎች የእለታዊ ገቢ ግብርን እየተቃወሙ ነው

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣ በወልድያ፣ በሻሸመኔና በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በግምት ላይ የሚጣለውን ግብር በመቃወም ላይ ሲሆኑ፣ በምስራቅ ሃረርጌ በጨለንቆና በጭሮ ከተማ ደግሞ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን አሰምቷል። ነጋዴዎቹ ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጠነ ግብር እንዲከፍሉ መደረጋቸውን የግብር መከፈያ ጽ/ቤትን በመክበብ ሲቃወሙ ውለዋል። ስቱዲዮ በገባንበት ሰአት ወኪላችን ባደረሰን ዘገባ ...

Read More »

ብአዴንን ደግፈን በመታገላቸው እንደሚጸጸቱ የሰቆጣ ነዋሪዎች ተናገሩ

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዋግ ነዋሪዎች በከተሞች ዙሪያ በተጠራ ስብሰባ ላይ ፣ ድርጅቱ በአካባቢያቸው ተመስርቶ አስፈላጊውን ድጋፍ አድርገውለት ለስልጣን ቢያበቁትም፣ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ግን እንደጠላቸውና እንደረሳቸው ተናግረዋል። “አንዳንድ ጊዜ የትግል ታሪካችንን ለመናገር ስንፈልግ፣ የታላላቅ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ታሪክ እንኳን ለመናገር ስንፈልግ፣ የሚያሸማቅቅ ሁኔታ ነው ያለው” በማለት በድርጅቱ እንደሚያፍሩበት ገልጸዋል። ይህ ህዝብ “ይህንን ድርጅት ደግፎ ...

Read More »

ከሰራዊቱ የተገለሉ ወታደሮች በከፍተኛ ጉስቁልና ውስጥ እንገኛለን በማለት ምሬታቸውን ገለጹ

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላፉት አስር እና 20 ዓመታት በመላከያ ግንባሮች በትግል ያሳለፉ እና አካላቸውን አጠው የተመለሱ የኢትዮጵያ መከላከያ አባላት፣ በከፈሉት መስዋዕትነት ምንም አይነት ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆኑ ባህር ዳር በተካሄደው የመከላከያ ተመላሽ አባላት ውይይት ላይ ተናግረዋል። ከ3 አመታት በፊት ከመከላከያ የተሰናበተ ወታደር፣ “ስንሄድ በከብሮ ተሸኝተን ነበር፣ አሁን ግን ተረስተን በጉስቁልና እየኖርን ነው” በማለት ...

Read More »