.የኢሳት አማርኛ ዜና

ዶክተር አቡነ ኤውስጣጢዎስወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ሲኖዶሱ ማሳሰቢያ ሰጠ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 19/2009)በሀገር ቤት የሚገኘውና በብጹእ አቡነ ማቲያስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ ጳውሎስ ከነበሩበት ግቢ ከጥቅምት 30 2004 ጀምሮ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ 5 ደብዳቤዎችን መጻፉንና በስልክም ተደጋጋሚ ጥረት ማድረጉን አስታውቋል። ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ በአቡነ ጳውሎስ ሲጠየቁ በስነ መለኮት የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪ የነበሩት አቡነ ኤውስጣጢዎስ ትምህርቴን ጨርሼ እመለሳለሁ በማለታቸው ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዲመለሱ በሚደረግባቸው ግፊት አለመግባባት መፈጠሩን የቤተክህነት ምንጮች ይገልጻሉ። ...

Read More »

በአማራ ክልል የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ መስፋፋቱ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና– ሐምሌ 19/2009)በአማራ ክልል በአምስት ዞኖችና 35 ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ተስፋፍቷል ሲሉ ነው የኢሳት ምንጮች በመረጃቸው ያመለከቱት። በአሁኑ ወቅትም በአንዳሳ፣ወንቅሸት፣አቡነሃራና ወረብ ከሚባሉ አካባቢዎች በበሽታው ተጠቅተው የመጡ 17 ሰዎች በሆስፒታሉ ተኝተው እየታከሙ መሆናቸው ተገልጿል። በባህር ዳር ከተማ ወደ አዲስ አለም ሆስፒታል ከመጡ ታካሚዎችም 15 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው መረጋገጡን ለማወቅ ተችሏል። በአማራ ክልል ጤና ቢሮ አንድ የስራ ሃላፊ ለመገናኛ ...

Read More »

  ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሙስና አለመታሰራቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 19/2009)በሀገር ቤት የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል ከተባሉት 34 ባለስልጣናት፣ነጋዴዎችና ደላሎች መካከል የተንዳሆና መተሃራ ስኳር ፋብሪካ የቀድሞ ሃላፊዎች ተጠቃሽ ሆነዋል። ሰንደቅ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የቀድሞ ሃላፊዎች ስራ አስኪያጁ አቶ አበበ ተስፋዬ፣የፋይናንስ ዘርፍ ስራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ድምጹ፣እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ዳይሬክተሩ አቶ በሃይሉ ገበየሁ፣የፋብሪካው የቀድሞ የግዢና ንብረት አስተዳደር ሃላፊው አቶ ኤፍሬም አለማየሁ ከታሳሪዎቹ መካከል ...

Read More »

የነጋዴዎች አድማ በአዲስ አበባ አየር ጤና አካባቢና በደጀን ቀጥሎ ውሎአል

ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ አገሪቱ ላለፉት 2 ሳምንታት የተካሄደው የንግዱ ማህበረሰብ አድማ ዛሬም ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ በአየር ጤና አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ መደብሮችን በመዝጋት ተቃውሞ እያደረጉ ሲሆን፣ አካባቢው በፖሊሶች ተወሯል። በደጀን ከተማም እንዲሁ ትናንት የተጠራውን አድማ ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ዛሬ ተግባራዊ አድርገውታል። ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ጭር ብላ የዋለች ሲሆን፣ ...

Read More »

በጉጂ ዞን ያለው ግጭት ተባብሶ ቀጥሎአል

ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃምሌ 16 ቀን 2009 ዓም ከቀንድ ከብቶች መዘረፍ ጋር በተያያዘ በጉጂ ኦሮሞዎችና በኮሬ ብሄረሰብ መካከል የተጀመረው ግጭት ተባብሶ ቀጥሎአል። ካለፉት 4 ቀናት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት እስካሁን ከሁለቱም ወገን ከ13 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን እና ከ300 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ ገልማ መታሪ በሚባለው ...

Read More »

አገሩ ባለቤት አልባ ሆኗል ሲሉ የኢህአዴግ የታች አመራር አባላት ተናገሩ

ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ የወረዳ አመራሮች እንደሚሉት ባለፉት 26 ዓመታት አገሪቱ ባለቤት አልባ በመሆኗ ዝርፊያው ተጧጡፏል ። “ይችን አገር ከእንግዲህ ምን ልናደርጋት ነው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። አቶ መላኩ አምሳሉ ላለፉት 24 አመታት በተለያዩ የአመራር ቦታዎች ላይ ሰርተዋል። በእነዚህ አመታት ሁሉ የተረዱት ነገር ቢኖር አገሪቱ ባለቤት አልባ መሆኗን ነው። ሙስናው እና ቢሮክራሲው አለ፣ ...

Read More »

አቃቢ ህግ የአቶ በቀለ ገርባን የዋስትና መብት ተቃወመ

ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦፌኮ ም/ል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ የቀረበባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ተቀይሮና በወ/ህ ቁጥር 257/ሀ መሰረት እንዲከላከሉ ፍርድ ቤት የወሰነላቸው መሆኑን ተከትሎ፣ አንቀጹ የዋስትና መብት የማያስከለክል በመሆኑ የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢያመለክቱም፣ አቃቢ ህግ ተቃውሞ አቅርቧል። አቃቢ ህግ “ ይህ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ማየት ሲጀምር በህግ አግባብ ተከሳሹን የዋስትና ...

Read More »

በሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ወረቀት ከሌላቸው 400 ሺህ ከሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ወደ ሀገራቸው የተመለሱት 60 ሺህ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘገበ።

ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪያድ ባለፈው መጋቢት ወር ህጋዊ ወረቀት የሌላቸው ስደተኞች በ90 ቀናት ውስጥ ሀገሯን እንዲለቅቁ የሰጠችው ማስጠንቀቂያና የጊዜ ገደብ የተጠናቀቀው ትናንትና ነው። በተጠቀሰው ጊዜ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ቢሆንም አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ባለመፈለጋቸው ዛሬ በሳኡዲ አረቢያ መንግስት ተጨማሪ የአንድ ወር የምህረት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያውያኑ ...

Read More »

በግብር ትመና ላይ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 18/2009)በመንግስት በኩል የሚሰጡት የተምታቱ መግልጫዎች አነጋጋሪ ሆነዋል።የጋቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ከበደ ጫኔ በ24 ሰአት ልዩነት ሁለት ተቃራኒ መግለጫዎችን ሰጥተዋል። እሁድ ለንባብ በበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ የተናገሩት አቶ ከበደ ጫኔ ነጋዴው የፈለገውን የአቅሙን እንዲከፍል ውሳኔ ላይ ተደርሷል ብለዋል። በማግስቱ ይህን ሀሳባቸውን በመሻር የተተመነውን ግብር ነጋዴው የከፍላል ሲል ገልጸዋል።ተቃውሞው ወደ አጠቃላይ ህዝባዊ አመጽ የሚሸጋገር ከሆነ የግብር ተመኑ ሊሻር ይችላል ...

Read More »

በአሜሪካ ሲያትል ከተማ አንድ ኢትዮጵያዊ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሕይወቱ አለፈ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 18/2009) ይትባረክ ደሞዝ የተባለው የ36 አመት ኢትዮጵያዊ ወጣት ህይወቱ ያለፈው ባለፈው እሁድ ሲሆን አስከሬኑ የተገኘው ከ24 ሰአት ፍለጋ በኋላ ነበር። በአሜሪካ ዋሺንግተን ግዛት ሲያትል ከተማ ነዋሪ የሆነው ይትባረክ ደሞዝ እሁድ ማለዳ ሊነጋጋ ሲል ከሚነዳት ጀልባ ዘሎ ባህር ውስጥ ከገባ በኋላ ህይወቱ ማለፉ ተመልክቷል። በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለጹት ወጣቱ ከመዝለሉ በፊት ከጀልባዋ ውስጥ የሚረብሽ ከፍተኛ ድምጽ ተሰምቷል። ይህንን ...

Read More »