.የኢሳት አማርኛ ዜና

አሊ አብደላ ሳልህ ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳልህ ተገደሉ። ሳላህ የተገደሉት በሰነአ በመኪናቸው ላይ በተከፈተ ጥቃት ነው። የሃውቲ አማጽያን መሪ ሳላህ ከጠላት ጋር በማበር የሲቪሎችን ሕይወት በማጥፋታቸው ጥቃቱ ተፈጽሞባቸዋል ሲል መግለጫ ሰጥቷል። የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በሀገሪቱ መዲና ሰነአ በመኪናቸው ላይ በተከፈተ ጥቃት መገደላቸውን አልጀዚራ በሃውቲ ቁጥጥር ስር ያለን የሀገር ውስጥ ሬዲዮ ጠቅሶ ዘግቧል። በማህበራዊ ድረገጾች በተለቀቀ ...

Read More »

የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ወደ ሃዋሳና አዲስ አበባ እየሄዱ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010)  በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች አካባቢውን እየለቀቁ ወደ ሃዋሳና አዲስ አበባ እየሄዱ መሆናቸው ተነገረ። በአካባቢው ሃብትና ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ስፍራውን ለመልቀቅ የተገደዱት በጌዲዮ ተወላጅ አመራሮች ጫና እየደረገባቸው በመሆኑ ነው ሲሉ የኢሳት ምንቾች ገጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የአካባቢውን ሕዝብ ሰሞኑን ሰብስበው የጌዲዮ አመራሮችን መውቀሳቸው ተነግሯል። የጌዲዮ ዞን አስተዳደር አመራሮች በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ...

Read More »

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር በወልድያ ባሉ ከተሞች ተሰማራ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) በወልዲያ ትላንት የተጀመረው የህዝብ ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎች መዛመቱን ተከትሎ የህወሃት መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር በየከተሞቹ ማስገባቱ ተገለጸ። በወልዲያ፣ ሀይቅ፣ ቆቦ መውጪያና መግቢያ ላይ በርካታ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን የሚወጣና የሚገባ ተሽከርካሪ እያስቆሙ እንደሚፈትሹ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሀይቅ ከተማ ታግተው ያሉት የሰላም ባስ አውቶቡሶችን ለማስለቀቅ የህወሃት ወታደሮች በሄሊኮፕተር መግባታቸውን ተከትሎም በሀይቅ ከተማ ውጥረት መንገሱ ይነገራል። በትላንቱ ህዝባዊ ...

Read More »

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት የለም አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ የተመረጡት የቀድሞው የኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር የለም ሲሉ አስተባበሉ። አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት አለ ማለት ልጆችን አያ ጅቦ መጣብህ እያሉ እንደማስፈራራት ይቆጠራልም ብለዋል። የአማራና የኦሮሞ ሕዝን እሳትና ጭድ ናቸው በማለት የሚታወቁት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት አለ በሚል የተነዛው የፈጠራ ወሬ አደገኛ ውጤት አስከትሏል ...

Read More »

የሱዳን ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገቡ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የሱዳን ወታደሮች 40 ኪሎ ሜትር ያህል ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ ክልል በመግባት ሰብል ማቃጠላቸውን የኢሳት ምንጮች አጋለጡ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ወታደሮቹ በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ኮርመር እስከሚባል አካባቢ ዘልቀው መግባታቸው ታውቋል። አሰሪ የተባለውን የኢትዮጵያ መሬት መቆጣጠራቸውንም ለማወቅ ተችሏል። የህወሃት መከላከያ ሰራዊት ከባህርዳርና መተማ ተነስቶ ወደ ስፍራው እየተጓዘ መሆኑ ቢታወቅም የመከላከያ ሰራዊቱ አካሄድ ግን ወታደሮቹን ለማስወጣት ይሁን ...

Read More »

አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በመከላከያ ሃይል እንዲጠበቁ ተደረገ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010) በኦሮሚያ ክልል ያሉ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በመከላከያ ሃይል እንዲጠበቁ መደረጉ ተሰማ። የፖሊስ ሃይሉን ገሸሽ ያደረገ ይህ ተግባር ምናልባትም አመጽ እያሰማ ያለውን ህዝብ በሃይል ለማፈን የተቀነባበረ ሴራ መኖሩን እንደሚያሳይ ምንጮች ገልጸዋል። በክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም ግቢዎቻቸውን እየለቀቁ በመውጣት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትላንት በስቲያ በአዳማ ናዝሬት ስኳር ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ በህዝብ ቁጥጥር ...

Read More »

ማይክል ፍሌን ጥፋተኛ ነኝ አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010)   የፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀድሞ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ማይክል ፍሌን ዛሬ በፍርድ ቤት ጥፋተኝነታቸውን አመኑ። ማይክል ፍሌን በፍርድ ቤት ቀርበው የሀገሪቱ የፌደራል ምርመራ ቢሮ/ኤፍ ቢ አይ/ ጉዳዩን በተመለከተ ባደረገላቸው ምርመራ መዋሸታቸውን አምነዋል።        የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ማይክል ፍሌን ሩሲያ ባለፈው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች በሚል የፌደራል ምርመራ ቢሮ/FBI/ ምርመራ ሲያደርግላቸው በወቅቱ የሰጡት ቃል ከእውነት ...

Read More »

ጋዜጠኛ ሳሙኤል ፈረንጅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010)  በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነትና በስራ አስኪያጅነት ለረጅም አመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ ሳሙኤል ፈረንጅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ሳሙኤል ፈረንጅ ከጋዜጠኝነቱ ሌላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገሉ ታውቋል። አቶ ሳሙኤል ፈረንጅ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በጋዜጠኝነትና በስራ አስኪያጅነት ለረጅም አመታት አገልግሏል።በሌሎች የመንግስት ተቋማትም በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል። ከአባቱ ከቀኝ አዛማች ፈረንጅና ከእናቱ አበበች ገመዳ በ1929 ...

Read More »

የ104 ዓመቷ አዛውንት በድብደባ ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010) የ104 ዓመት አዛውንት ሴት በእስር ቤት በድብደባ ተገደሉ። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ በሚገኝ እስር ቤት ባለፈው ረቡዕ የታሰሩት ወ/ሮ አምባሮ ሺክህ ዳይብ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸው አልፎ ዛሬ አስከሬናቸው ለቤተሰብ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። የእሳቸው ልጅ የ83 ዓመቱ አዛውንት አሊ አብዱላሂ ፊሂዬም በእስር ቤት የሚገኙ ሲሆን ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ ህዝቡ እንዲከታተል ጥሪ ቀርቧል። መነሻው የፖለቲካ አቋም ነው። የአዛውንቷ የልጅ ...

Read More »

በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ትዕዛዝ ተላለፈ

(ኢሳት ዜና– ሕዳር 22/2010) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ ሰክረው በፈጠሩት ችግር ምክንያት ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ዲፕሎማቱ ተስፋኪሮስ ሃይሉ ገብረማርያም ባለፈው ቅዳሜ በስካር መንፈስ መኪና ሲያሽከረክሩ ካደረሱት ተደራራቢ የትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ሲያስቆማቸው ለህጉ ከመገዛት ይልቅ በኢትዮጵያና በቱርክ መሃል ጦርነት እጭራለሁ ሲሉ ማስፈራራታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። የቱርክ መገናኛ ብዙሃንም ዲፕሎማቱ ያሳዩትን ያልተገባ ባህሪ ...

Read More »