.የኢሳት አማርኛ ዜና

ነብይ ነኝ ባዩ ናይጄሪያዊ በቁጥጥር ስር ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) ነብይ ነኝ ባዩ ናይጄሪያዊ አደንዛዥ እጽ ሲያዘዋውር በቁጥጥር ስር መዋሉን የዛምቢያ ፖሊስ ገለጸ። የ42 አመቱ ናይጄሪያዊ አይዛክ ጁልየስ አማታ በዛምቢያ ርዕሰ መዲና ሉሳካ በቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ መሆኑ ታውቋል። 26 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እጽ እንደተገኘበትም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል። ሉሳካ ኬኔት ካውንዳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በቁጥጥር ስር የዋለው አይዛክ ኦማታ ወደ እስር ቤት መወሰዱም ታውቋል። በእጽ አዘዋዋሪነትም እንደሚከሰስ ...

Read More »

ጊዜያዊ የትምህርት ማቋረጥ የጠየቁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ አይመለሱም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጊዜያዊ የትምህርት ማቋረጥ(ዊዝድሮዋል) የጠየቁ ተማሪዎች የመልሶ ቅበላ እንደማይፈቀድላቸው የመንግስት ቃል አቀባይ ገለጹ። ቃል አቀባዩ ዊዝድሮዋል መሙላት ቴክኒካል ጉዳይ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። የመንግስት ቃል አቀባዩ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ በጽሕፈት ቤታቸው ለመንግስት፣ለፓርቲና ለግል መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የጊዜያዊ ትምህርት ማቋረጥ(ዊዝድሮዋል) መሙላት አይችሉም ሲሉ ተደምጠዋል። ቃል አቀባዩ በ2010 ጊዜያዊ ማቋረጥን መሙላት ...

Read More »

የኦሮሞ ሕዝብ ለምን ተበደለ ተብሎ መዘገቡ ትክክል አይደል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ለምን ተበደለ፣ጥቅምስ ለምን ቀረበት በሚል ኦቢኤን ቴሌቪዥን መዘገቡ አግባብ አይደለም ሲሉ የብሮድካስት ባለስልጣን አቶ ዘርአይ አስገዶም ገለጹ። አቶ ዘርአይ የክልልና የግል መገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች በተገኙበት መድረክ እንዳሉት ቴዲ አፍሮ ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ ሲያውለበልብ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ በፌስቡክ ገጻቸው ድጋፍ ሰጥተዋልም ብለዋል። የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክ ኦቢኤን በድምጻዊ አጫሉ ሁንዴሳ በኩል ወጣቶች ቤተመንግስት እንዲገቡ ...

Read More »

ሰላም ባስ የጎዞ መስመሩን ለሁለተኛ ጊዜ ቀየረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በወልዲያ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ የቀየረውን የጎዞ መስመር በአፋር ክልል በገጠመው የጸጥታ ችግር እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ለመቀየር መገደዱን አስታወቀ። በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ ግዴታ ስለሆነበት የታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ሕወሃት/ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ጥር 15/2010 “ለተከበራችሁ ደንበኞቻችን” በሚል ያወጣው ማስታወቂያ ከአዲስ አበባ መቀሌና ...

Read More »

በቆቦ ህዝባዊው ተቃውሞ ተባብሶ ቀጠለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 17/2010) በሰሜን ወሎ ቆቦ ትላንት የተጀመረው ህዝባዊ አመጽ ዛሬ ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ። የአጋዚ ሰራዊት በወሰደው ርምጃ 9 ሰዎች መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አንድ የአጋዚ ወታደርም መገደሉ ታውቋል። ህዝቡ ራሱን ለመከላከል ከዘመተበት የህወሃት ጦር ጋር መጋጠሙ ይነገራል። ከህወሃትና ብአዴን ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ንብረቶች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው። የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ፍርድ ቤት፣ 4 ቀበሌዎች መቃጠላቸውን በቪዲዮ ተደግፎ ለኢሳት ...

Read More »

በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ከ7 በላይ ተማሪዎች መጎዳታቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) በደቡብ ክልል ሆሳዕና ከተማ በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ ግጭት ከ7 በላይ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግጭቱ ብሔርን መሰረት አድርጎ መቀስቀሱን ዘገባዎች አመልክተዋል። ዩኒቨርስቲው ግጭቱን ለማርገብና ለመቆጣጠር ኮማንድ ፖስት ማቋቋሙ ታውቋል። በሆሳዕና ከተማ ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ብሔርን መሰረት ያደረገ ግጭት በመፈጠሩ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እስከመውጣት ደርሰዋል። የችግሩ መንስኤ በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የተነሳ ነው ቢባልም ቀደም ብሎም ፖለቲካዊ ...

Read More »

ዮዌሪ ሙሴቬኒ ዶናልድ ትራምፕን አደነቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) አሜሪካ በታሪኳ ካገኘቻቸው ምርጥ ፕሬዝዳንቶች አንዱ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ሲሉ የዩጋንዳው መሪ ዮዌሪ ሙሴቬኒ ገለጹ። ዶናልድ ትራምፕ አፍሪካን በተመለከተ በግልጽ በመናገራቸው ወድጄያቸዋለሁ በማለት ከቅሬታና ተቃውሞ ይልቅ አድናቆት ቸረዋቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ በኢሚግሬሽን ጉዳይ ላይ በዚህ ወር መጀመሪያ በኋይት ሃውስ በተደረገ ስብሰባ የአፍሪካ ሀገራትን ውዳቂ ሲሉ መጥራታቸው ይታወሳል። አፍሪካን በተመለከተ ዶናልድ ትራምፕ በግልጽ በመናገራቸው ወድጄያቸዋለሁ በማለት ዮዌሪ ሙሴቬኒ አስተያየታቸውን ...

Read More »

ለትግራይ ተወላጆች የተዘጋጀው ፌስቲቫል ተሰረዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በውጭ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በከፍተኛ ወጪ ያዘጋጀው ፌስቲቫል ተሰረዘ። በመጪው ሃምሌ በመቀሌ ሊካሄድ የነበረው ፌስቲቫል የተሰረዘው በሕወሃት ውስጥ ከተፈጠረው ክፍፍል ጋር በተያያዘ እንደሆነ የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል። ሆኖም ለትግራይ ተወላጆች የተላለፈው መልዕክት ፌስቲቫሉ የተሰረዘው በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ነው የሚል ነው። በአቶ አባይ ወልዱ የሕወሃት ሊቀመንበርነትና በርሳቸው ቡድን የበላይነት ወቅት የተደረገው ይህ ጥሪ በአይነቱ ልዩና ...

Read More »

ህዝብን በመጨፍጨፍ ትግሉን ለመቀልበስ አይቻልም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) ህዝብን በመጨፍጨፍ ትግሉን ለመቀልበስ አይቻልም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ በወልዲያ በህወህት ታጣቂዎች የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ ። ትግሉን ከአሁኑ በተሻለ ህዝቡና ታጋይ ሃይሎች አዲስ መርሀግብር በመንድፈ በጋራ መታገል ይኖርብናል በማለት ጥሪውን አቅርቧል። በተመሳሳይ የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብቶች ሊግ በወልዲያ የተፈጸመውን ጥቃት ትውልድ ላይ የተቃጣ ብሔራዊነትን አደጋ ላይ የጣለ ሲል መግለጫ አውጥቷል። የ2010 የጥምቀት በዓል በአብዛኛው የሀገሪቱ ...

Read More »

አራት ተከሳሾች ተፈረደባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2010) መንግስት ክሳቸውን ሰርዞ እፈታቸዋለሁ ካላቸው 115 እስረኞች መካከል 4ቱ ችሎት ቀረበው እንደተፈረደባቸው ታወቀ። ይፈታሉ ተብሎ ስማቸው ከተጠራውና ለስልጠና ወደ ቃልቲ ተውሰደ ከነበሩት 115 እስረኞች መካከል እንደነበሩም ታውቋል። ነገ ግን ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት እነዚሁ ክሳቸው ተነስቶላቸዋል የተባሉት 4 ተከሳሾች ቀርበው የተላለፈባቸውን ፍርድ እንዲሰሙ መደረጉ ታውቋል። የህግ ባለሙያዎች በበኩላቸው እንዲህ አይነቱ አካሄድ ...

Read More »