.የኢሳት አማርኛ ዜና

ዶናልድ ትራምፕ ወታደራዊ ሰልፍ እንዲዘጋጅ ጠየቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር በዋሽንግተን ታላቅ ወታደራዊ ሰልፍ/ፓሬድ/እንዲያዘጋጅ ጠየቁ። በፕሬዝዳንቱ የቀረበው የወታደራዊ ትዕይንት ጥያቄ ከተለያዩ ወገኖች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ባለፈው አመት በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው የፈረንሳውያኑ አመታዊ ባስቲል ዴይ ወታደራዊ ሰልፍ ላይ ተገኘተው የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወታደራዊ ሰልፉን “በሕይወቴ እንዲህ ያለ ከፍተኛ ወታደራዊ ሰልፍ አይቼ አላውቅም” በማለት ገልጸውት ነበር። ስለፈረንሳዩ ሰልፍ አድናቆታቸውን የገለጹት ...

Read More »

የበይነ መረብ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) በአለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ግብረሃይል የተጠራውን የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ዘመቻ ለማጠናከር ዛሬ የበይነ መረብ ዘመቻ በማካሄድ ላይ መሆኑ ታወቀ። ዘመቻው ፌስ ቡክንና ቲውተርን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ መረጃ መረቦች መጀመሩ ተገልጿል። የዘመቻው አላማ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ህዝብን ለመግደልና ለመጨቆን የሚጠቀምበት መሆኑን ለማሳወቅና የዘመቻውን አስፈላጊነት ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል። ...

Read More »

ለፕሬዝዳንት ሙላቱ ህክምና የተጻፈው ደብዳቤ ሾልኮ ወጣ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለህክምና ወደ ቻይና ይሄዳሉ በሚል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የተጻፈላቸውን የውስጥ ደብዳቤና የተመደበላቸውን የሰው ሃይል ብዛት የሚያሳይ መረጃ ይፋ ሆነ። የውስጥ ደብዳቤው ከፕሬዝዳንቱ ጋር ለህክምና ወደ ውጪ የሚጓዙት ሰዎች ብዛት 11 መሆኑን ያሳያል። ለእያንዳንዳቸው ተጓዦችም የ10 ቀናት የውሎ አበል በውጭ ምንዛሪ እንደተዘጋጀላቸውና ለመጠባበቂያ የሚሆንም 10ሺ የአሜሪካን ዶላር እንደተመደበላቸው መረጃው አጋልጧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ...

Read More »

ኦህዴድ 14 የምክር ቤት አባላትን አባረረ 4 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን አገደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ 14 የምክር ቤት አባላትን በማባረር እንዲሁም አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ 4 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በማገድ ስብሰባውን አጠናቀቀ። ለአስር ቀናት በአዳማ ያካሄደውን ስብሰባ ትላንት ያጠናቀቀው ኦህዴድ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል፣አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት እንዲኖርና ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን እንደሚሰራም አስታውቋል። የኦሮሞ ሕዝብ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን የሀገራችንን ቀጣይ ጉዞ የማቃናት ሚናውን ዛሬም እንደትላንቱ ሊጫወት ይገባልም ብሏል። ...

Read More »

ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ከሃላፊነት ሊነሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 30/2010)   በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ በአሸናፊነት የወጣውና በአቶ ስብሃት ነጋ የሚደገፈው ቡድን ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ከሃላፊነት እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ገለጹ። የሕወሃትን የበላይነት ባስጠበቀ ሆኖም በሀገሪቱ የተከሰተውን ውጥረት በሚያረግብ መልኩ እየተከናወነ ነው የተባለው የሰራዊቱ አመራር ብወዛ፣በክፍለ ጦር አዛዦችና በተዋረድ ባሉ መዋቅሮች ላይ ምንም አይነት መሰረታዊ ለውጥ ሳያመጣ የሕወሃት ታጋዮች በአመራሩ ስፍራ እንደሚቀጥሉም ተመልክቷል። የሃገሪቱን አራት ...

Read More »

በኬንያ ከተዘጉት ሶስት የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁለቱ ስራ ጀመሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰይመው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የሚያሳየውን ትዕይንት ለመዘገብ በመንቀሳቀሳቸው ከተዘጉት ሶስት የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁለቱ ስራ መጀመራቸው ታወቀ። ሲትዝን የተባለው የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ግን አሁንም ከሳምንት በላይ ስርጭቱ እንደተቋረጠ ይገኛል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥር 30/2018 የተቃዋሚ ፓርቲ መሪና እጩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰይመው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የሚያሳየውን ...

Read More »

አዞላና ኢፓማ የተባሉ አረሞች ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) በጣና ሃይቅ ላይ አዞላና ኢፓማ የተባሉ አረሞች በተጨማሪ ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ። እምቦጭ አረም ሃይቁ ላይ እያደረሰ ያለው አደጋም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የውሃ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ የጣና ሃይቅ ባለፉት አመታት የተለያዩ የህልውና ፈተናዎች ገጥመውታል ሲሉ ለቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ተናግረዋል። ፈተናዎቹን የአፈር መከላት፣የደለል ክምችት፣ተገቢ ያልሆነ የስነ-ሕይወት አጠቃቀም፣ልቅ ግጦሽና የባህር ሸሽ ...

Read More »

በጉዲፈቻ የተወሰዱ ሰባት ሺ ህጻናት የት እንደደረሱ አይታወቅም ተባለ

  (ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2018) በጉዲፈቻ ከኢትዮጵያ ወደ ወጭ የተወሰዱ ሰባት ሺ ህጻናት የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሃምቢሳ ወደ ውጭ በጉዲፈቻ የሚሰጡ ህጻናት በተገቢው ህጋዊ አሰራር እየተፈፀመ አለመሆኑን ለፓርላማ ገልፀዋል፡፡ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሃምቢሳ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ያሉ ደላሎች ወላጆችን በማታለልና ከሌሎች አካላት ጋር በመመሳጠር በህገወጥ መንገድ ህፃናትን ወደ ተለያዩ ሀገራት ልከዋል፡፡ ...

Read More »

የአለም ባንክ ቋሚ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ ነዋሪዎች 200ሺ የሚሆኑት ራሳቸውን መመገብ ባለመቻላቸው የአለም ባንክ ቋሚ ድጋፍ ሊያደርግላቸው መሆኑ ተገለጸ። አቅመ ደካሞች ለሆኑት በየወሩ ቋሚ ክፍያ በመስጠት እንዲሁም ሌሎቹን ደግሞ በአካባቢ ጽዳትና መሰል ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ገንዘቡ እንደሚከፈላቸው ተመልክቷል። በፍጹም ድህነት ውስጥ ከሚገኙት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች 32ሺ የሚሆኑት አቅመ ደካሞች በመሆናቸው በነፍስ ወከፍ በወር 170 ብር በቤተሰብ ቁጥር ተባዝቶ ...

Read More »

የአጼ ቴድሮስ ሐውልት ተመረቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) የአጼ ቴድሮስ ሐውልት በደብረታቦር ከተማ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ተመረቀ። በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በ2 ሚሊየን ብር ወጪ የተሰራው የአጼ ቴድሮስ ሃውልት 7 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት ያለው ነው። በኢትዮጵያ የንግስና ታሪክ ከ1847 እስከ 1860 ኢትዮጵያን የመሩት አጼ ቴድሮስ የሀገር አንድነት ተምሳሌት ናቸው። በከፋፍለህ ግዛው ስልት በተነጣጠለ ሁኔታ በኢትዮጵያ የነበረውን የዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ለማስወገድ ደፋ ቀና ያሉት አጼ ቴድሮስ በእንግሊዞች ...

Read More »