(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2010) በቀበሌ ሕብረት ሱቆች በኮታ እየተሸጡ ያሉ ሸቀጦች ህገ ወጥ በሆነ መንገድ አየር በአየር እንደሚቸበቸቡ ነዋሪዎች ገለጹ። ሸቀጦቹን ለመግዛት ሙሉ ቀን የሚያዘው ወረፋ አሰልቺ መሆኑንም ነዋሪዎቹ በምሬት ተናግረዋል። የኢሳት የአዲስ አበባ ወኪል በቀበሌ ሕብረት ሱቆችና ሸማቾች ማህበራት ተዟዙሮ እንደተመለከቱው ነዋሪዎች በሬሽን ኩፖን በኮታ መልኩ ስኳር፣ዘይትና የመሳሰሉትን ሸቀጦች ለመግዛት በእኩለ ለሊት በመነሳት ወረፋ መያዝ ግዴታቸው ሆኗል። ሸቀጦቹንም ለመግዛት ሙሉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የፖለቲካ ድርጅት ለማቋቋም አስባችኋል የተባሉ 19 ሰዎች ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2010) በአማራ ክልል የፖለቲካ ድርጅት ለማቋቋም አስባችኋል የተባሉ 19 ሰዎች በባህርዳር ከተማ በጅምላ መታሰራቸው ተነገረ። እስሩ የተፈጸመባቸው ምሁራንና ጋዜጠኞች በብሔር ላይ የተመሰረተ የአማራ ድርጅት በህጋዊ መንገድ ለማቋቁም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው ተብሏል። በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የአገዛዙ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት ከምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝተው የአማራ ብሔራዊ ድርጅት ለማቋቋም እንቅስቃሴ የጀመሩት 19 ሰዎች በወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያው ኮማንድ ፖስት ተለቅመው ታስረዋል። ...
Read More »እነ እስክንድር ነጋ በድጋሚ መታሰራቸው የስርአቱን አለመለወጥ ያሳያል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2010) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣አንዱአለም አራጌ እና ተመስገን ደሳለኝኝን ጨምሮ 12 ታስረው የተለቀቁ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንደገና በቁጥጥር ስር መዋላቸው የአገዛዙን አለመለወጥ እንደሚያሳይ ተነገረ። እነ እስክንድር ነጋ በተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት ቤት በተካሄደ ግብዣና የሽልማት ስነስርአት ላይ እያሉ ትናንት ዕሁድ በፖሊስ ታስረው ተወስደዋል። የእስሩ መንስኤ ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ ለምን ያዛችሁ፡፣ ግብዣውስ እንዴት ያለፈቃድ ተካሄደ በሚል እንደሆነ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል። ...
Read More »የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ቀጠለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2010) ትናንት እሁድ የፓርቲውን ሊቀመንበር በመምረጥ ይጠናቀቃል የተባለው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ትናንት ከተቋረጠ በኋላ እንደገና ዛሬ መቀጠሉን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ስብሰባው የተቋረጠው ሕወሃት የብቻውን ስብሰባ ለማድረግ በመጠየቁ እንደሆነም ታውቋል። በጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ምርጫ ላይ ስምምነት በመጥፋቱ አቶ ሃይለማርያም እንዲቀጥሉ በአንዳንድ ወገኖች ሃሳብ መቅረቡም ተመልክቷል። በሳምንቱ አጋማሽ ይጠናቀቃል የተባለው ስብሰባ ወደ ሳምንቱ መጨረሻ ቢገፋም በተባለውና በተነገረው መሰረት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ...
Read More »በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ታሰሩ በባህርዳር በህቡዕ ልትደራጁ አስባችሁዋል ተብለው የተያዙትም አልተለቀቁም
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ታሰሩ በባህርዳር በህቡዕ ልትደራጁ አስባችሁዋል ተብለው የተያዙትም አልተለቀቁም (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ፣ በህዝባዊ ጫና ከእስር የተፈቱት ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ወታደራዊ እዙን ሳታስፈቅዱ ስብሰባ አድርጋችሁዋል እንዲሁም አርማ የሌለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተጠቅማችሁዋል በሚል ተይዘው ታስረዋል። ትናንት እሁድ ጆሞ በሚባለው አካባቢ በቅርቡ ከእስር ለተፈቱት ሰዎች በተዘጋጀ የምስጋና ...
Read More »የደደር ወረዳ ወጣቶች የጦር መሳሪያዎችን በመቀማትና መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ እያደረጉ ነው
የደደር ወረዳ ወጣቶች የጦር መሳሪያዎችን በመቀማትና መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ እያደረጉ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ወኪላችን እንደገለጸው ትናንት በምስራቅ ሃረርጌ ወረዳ ማጫ ቀበሌ ማህበር የሚገኙ ወጣቶች እራሳቸውን በማደራጀት በአካባቢው ከሚገኙ የሚሊሺያ አባላት ላይ የጦር መሳሪያዎችን በመንጠቅና አካባቢውን በድንጋይ በመዝጋት ተቃውሞ እያደረጉ ነው። ወጣቶቹ የቀሙትን የጦር መሳሪያው እንዲመልሱ እንዲሁም ተቃውሞአቸውን እንዲያቆሙ ለማሳመን የተላከው የኦሮምያ ፖሊስና የክልሉ አድማ ...
Read More »በኢሊባቦር ዞን በደርግ ጊዜ ስፍረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው
በኢሊባቦር ዞን በደርግ ጊዜ ስፍረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በ1977 ዓም የነበረውን ድርቅ ተከትሎ ከትግራይ ወደ ኢሉባቦር ዞን ተሰደው የነበሩና በመቱ ወረዳ በሮይ እና በቾ በሚባል አካባቢ እንዲሁም በሁሩሙ ወረዳ ያሉ ሰፋሪዎች ያላቸውን ማንኛውንም ንብረት ሸጨው እንዲወጡ በትግራይ ልማት ማህበር እና በህወሃት ታዘናል በማለት ንብረታቸውን እየሸጡ ...
Read More »በርካታ የታሰሩ ወጣቶችን የጫኑ 2 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ገቡ
በርካታ የታሰሩ ወጣቶችን የጫኑ 2 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ገቡ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የአይን እማኞች ለኢሳት እንደገለጹት ዛሬ ከጠዋቱ 8 ሰአት ከ18 ደቂቃ ላይ በርካታ ወጣቶቹን የጫኑ 2 ኦራል መኪኖች ወደ አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ያመሩ ሲሆን፣ ወጣቶቹ በራሳቸው ልብስ አፋቸው ተለጉሞ፣ እጃቸውም በገደም ታስሮ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ሁለቱም መኪኖች ስናይፐር በታጠቁ የአጋዚ ወታደሮች እየታጀቡ በመጓዛቸው ...
Read More »89 በመቶው ትምህርት ቤቶች ከዓለም አቀፍ መመዘኛ በታች መሆናቸውን የትምህርት ሚንስቴር ጥናት አረጋገጠ
89 በመቶው ትምህርት ቤቶች ከዓለም አቀፍ መመዘኛ በታች መሆናቸውን የትምህርት ሚንስቴር ጥናት አረጋገጠ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) ተማሪዎችና መምህራን በቋንቋ መግባባት ተቸግረዋል በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የጥራት ደረጃቸው አጠያያቂ ደረጃ ላይ መድረሱን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥራት ጉባዔ ላይ ተገልጿል። በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና መምህራን መካከል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ማነስ ምክንያት ...
Read More »በተጠናቀቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በአባይ ጸሃዬ የተማራው ህወሃት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ጸብ ቀረሽ ክርክር ማድረጉ ታወቀ
በተጠናቀቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በአባይ ጸሃዬ የተማራው ህወሃት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ጸብ ቀረሽ ክርክር ማድረጉ ታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ለሳምንት በተደገረው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ህወሃት በአቶ አባይ ጸሃዬ ዋና ተከራካሪነት ተወክሏል። ከአቶ አባይ ጀርባ አቶ ስብሃት ነጋና አቶ በረከት ስምዖን ተሰልፈው በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ አድርገዋል። ኦህዴድ በአቶ ለማ መገርሳ ዋና ተከራካሪነት ሲቀርብ፣ ...
Read More »