.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአማራ ክልል ታስረው የነበሩ 19 ጋዜጠኞችና ምሁራን ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2010)በአማራ ክልል ታስረው የነበሩ 19 ጋዜጠኞችና ምሁራን መለቀቃችውን ዘገባዎች አመለከቱ። በእስር ላይ የቆዩት አስራ ዘጠኙ ምሁራን እና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ በአማራ ክልል ዘመቻ ተጀምሮ ነበር።  ከባህርዳር ከተማ አስቸኳይ አዋጁን ጥሳችኋል ተብለው በእስር ላይ የቆዩት እነዚሁ ምሁራንና ጋዜጠኞች ሁሉም ተለቀዋል። በድጋሚ የታሰሩት እነ እስክንድር ነጋ ግን አሁንም ከእስር አለመለቀቃቸው ታወቋል። በአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ተንቀሳቅሳችኋል በሚል ከመጋቢት 15/2010 ጀምሮ ...

Read More »

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ህዝባዊ መንግስት እንዲያቋቁሙ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2010) ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ህዝባዊ መንግስት እንዲቋቋም እንዲያደርጉ ጠየቀ። ስድስት ጥያቄዎችን በማንሳት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ተግባር እንዲለውጧቸው ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ያደረገው ዛሬ ባወጣው መግለጫው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ የተናገሩትን ወደ መሬት አውርደው በተግባር እስኪያሳዩን ስጋታችን ይቀጥላል ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ስለኢትዮጵያ በክብርና በፍቅር ያደርጉትን ንግግር ግን በአድናቆት እንደሚመለከተው ጠቅሷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቃላቸውን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያቋቋመችው ባንክ እንዲመዘገብ ጠየቀች

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2010)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከትግራይ ባለሃብቶች ጋር በመሆን ያቋቋመችው  ባንክ እንዲመዘገብ ለብሔራዊ ባንክ ማመልከቻ አቀረበች። ከብሔራዊ ባንክና ከቤተክህነት ምንጮች በሰነድ ተደግፎ ለኢሳት ከደረሰው መረጃ መረዳት እንደተቻለው የባንኩን ድርሻ 63 በመቶ የትግራይ ባለሃብቶች፣19 በመቶ ቤተክህነት ሲይዙ ቀሪው 18 በመቶ ትንንሽ አክሲዮን ለሚገዙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለሽያጭ ቀርቦ ተሸጧል። “ዳሎል” በሚል ስያሜ በመቋቋም ላይ ያለው ባንክ ቤተክርስቲያኒቱ በልዩ ልዩ ባንኮች ...

Read More »

ህወሃት የሶማሊ ክልል ባለስልጣናት በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ እንዲካተቱ ግፊት እያደረገ ነው

ህወሃት የሶማሊ ክልል ባለስልጣናት በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ እንዲካተቱ ግፊት እያደረገ ነው (ኢሳት ዜና መጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ/ም) ከመጀመሪያው ጀምሮ የዶ/ር አብይ አህመድን የኢህአዴግ ሊቀመንበርነትና ጠ/ሚኒስትርነት ሹመት አጥብቆ ሲቃወመው የነበረው ህወሃት፣ በካቢኔው ውስጥ ተጽኖ ለመፍጠር እና በብአዴንና በኦህዴድ መካከል ተፈጥሯል የሚለውን መርህ አልባ ግንኙነት ለመበጠስ በማሰብ የኢትዮ-ሶማሊ ክልል ባለስልጣናት በቂ የስልጣን ቦታ እንዲሰጣቸው ግፊት ማድረግ ጀምሯል። ህወሃት የኢትዮ-ሶማሊያውያን በፌደራል መንግስቱ ...

Read More »

አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር በአፋጣኝ የሕዝቡን ጥያቄዎች በመመለስ ሕዝባዊ መንግስት እንዲያቋቁሙ ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ነፃ አውጪ ግንባርና የጎንደር ኅብረት ጠየቁ

አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር በአፋጣኝ የሕዝቡን ጥያቄዎች በመመለስ ሕዝባዊ መንግስት እንዲያቋቁሙ ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ነፃ አውጪ ግንባርና የጎንደር ኅብረት ጠየቁ (ኢሳት ዜና መጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ/ም) “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመላው ኢትዮጵያ እንደ ሰደድ እሳት የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ እምቢተኝነትን ተከትሎ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። አገዛዙ ለሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጥ በተደጋጋሚ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት የዜጐችን ደም ማፍሰስ፣ በጅምላ ማሰር፣ ...

Read More »

በባህርዳር ታስረው የነሩ 19 ሰዎች ከእስር ተለቀቁ

በባህርዳር ታስረው የነሩ 19 ሰዎች ከእስር ተለቀቁ (ኢሳት ዜና መጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ/ም) ያልተፈቀደ ስብሰባ አድርጋችሁዋል በሚል ላለፉት 2 ሳምንታት በእስር ቤት ያሳለፉት የዩኒቨርስቲ መምህራን፣ ጋዜጠኞች፣ ጠበቆችና በተለያዩ ሙያዎች ተሰማርተው የሚገኙ 19 ሰዎች መፈታታቸው ታውቋል። ታስረው ከተፈቱት መካከል በባህርዳር ዩንቨርሲቲ መምህርና የጣና ደህንነትና የአካባቢ ጥበቃ ማህበር ፕሬዚደንት የሆነው ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበረና የ”አንፀባራቂው ኮከብ” ...

Read More »

የኢትዮጵያ፣የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት በካርቱም ሊመክሩ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2010) በሕዳሴው ግድብ ላይ ለመነጋገር የኢትዮጵያ፣የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት ነገ በካርቱም እንደሚገናኙ ታወቀ። በግድቡ ዙሪያ በሃገራቱ በተለይም በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት በሚል የተጠራው ስብሰባ ላይ ለመገኘት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረቡዕ ካርቱም እንደሚገቡ ኦህራም ኦንላይን ዘግቧል። ባለስልጣኑም የስብሰባው አላማ ውዝግቡን ለመቋጨት እንደሆነም አስገንዝበዋል። በካርቱም ነገ በሚካሄደው ስብሰባ የየሃገራቱ የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የደህንነት ባለስልጣናት የሚገኙበት መሆኑም ...

Read More »

እነአቶ መላኩ ፈንታ በተወሰኑ ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 25/2018) በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው ከአራት ዓመታት በላይ ሲከራከሩ የከረሙት እነአቶ መላኩ ፈንታ  በተወሰኑ ክሶች ጥፋተኛ ሲባሉ በሌሎች ክሶች ደግሞ በነፃ ተሰናበቱ፡፡ አቶ መላኩና አቶ ገብረ ዋህድ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ሙስና ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር ። በዚሁ ክስ የተካተቱት አቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ አቶ ...

Read More »

በ10 ዩኒቨርስቲዎች ብቻ የ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጉድለት ተገኘ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2010)ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በ10 ዩኒቨርስቲዎች ብቻ የ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጉድለት መኖሩን የጠቅላላ ኦዲት ቢሮ ገለጸ። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ብቻ 64 ሚሊየን ብር ጉድለት በመኖሩ በፓርላማ የመንግስት ወጭ አስተዳደርና ቁጥጥር ኮሚቴ ተቋሙን መገሰጹ ታውቋል። በኢትዮጵያ ካሉ 158 የመንግስት ተቋማት ብቻ ባለፈው አመት የ20 ቢሊየን ብር ጉድለት መገኘቱን የጠቅላላ ኦዲት ቢሮ መግለጹ ይታወሳል። በኢትዮጵያ ...

Read More »

የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ንግግር የዋና የመነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሎአል

የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ንግግር የዋና የመነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ የጠ/ሚኒስትርነት ሹመቱን ሲቀበሉ ያደረጉት ንግግር በማህበራዊ ሚዲያውም ሆነ ከማህበራዊ ሚዲያው ውጭ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በንግግሩ መደሰታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እየገለጹ መሆኑን ወኪሎቻችን ያደረሱን ሪፖርት ያመለክታል። በተለይ የኢትዮጵአን ታሪክና የአገር አንድነትን አስመልክቶ ያቀረቡት ንግግር ለብዙ ኢትዮጵያውያን የደስታ ስሜት የሰጠ መሆኑን ...

Read More »