.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በመድረክ ላይ የሚያደርገውን ወከባ አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ

ኢሳት ዜና፡- ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመልከተው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመድረክ አባላት ላይ የሚያደርገውን ማሳደድ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። የአረና ትግራይ አባል የሖነው አማረ ተወልደ በሁመራ አካባቢ የድርጅቱን ወረቀት ሲበትን ተገኝቷል በሚል ሰበብ ለበርካታ ቀናት በቁጥጥር ስር ከዋለ በሁዋላ በመጨረሻም ንብረቱንና እቃዎቹን ተቀምቶ በሳምንቱ መጨረሳ ተለቋል። በተመሳሳይ ዜናም የዚሁ የአረና ትግራይ አባል የሆኑት አቶ አያሌው በዬነ በሽሬ ከተማ የፓርቲውን ወረቀት ...

Read More »

የሜድሮክ ኮንስትራክሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ

ኢሳት ዜና:- ከ 500 በላይ የሚሆኑት የሚድሮክ ጉርድ ሾላ፣ የረር በርና አያት ሳይት መንገድ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ የመቱት፤  ባለፈው ሐሙስ ነው። ኑሮ ሰማይ በነካበት በአሁኑ ሰዓት የአብዛኞቻችን ደመወዝ ከ 500  ብር ብዙም አይበልጥም የሚሉት እነዚሁ ሠራተኞች፤”‹ከዚህች ኪስ ከማትገባ ደመወዝ ላይ ለታክስና ለዓባይ ግድብ ተቆርጦላት  በእጃችን የምትደርሰን ከቤት ኪራይ እንኳ የማታልፍ ሆናለች>›ሲሉ ምሬታቸውን አሰምተዋል። “የዓመታት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄያችን ምላሽ ሊያገኝ ...

Read More »

የምክር ቤት አባልነቴ፤ በቴሌቪዥን ቢሆንልኝ ይሻል ነበር” ሲሉ በፓርላማው ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪል ተናገሩ

ኢሳት ዜና:- አቶ ግርማ ሰይፉ ከአውራምባ ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፤ ሰሞኑን አቶ መለስ በፓርላማ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከወትሮው በተለየ መልኩ በ አቶ መለስ አስተያዬት ዙሪያ ሀሳባቸውን ለመስጠት እንዳልተፈቀደላቸው ጠቅሰዋል።   “ይህ ነገር መታረም ካልቻለ  ምናልባትም ለምክር ቤቱ ጥያቄዎቻችንን አስገብተን እሳቸው መልስ እንዲሰጡና እኛ በቴሌቪዥን ብንከታተል የሚሻል ይመስለኛል”ያሉት አቶ ግርማ፤ “የምክር ቤት አባል መሆኔ ትርጉም የሚኖረው፤በተሰጡት አስተያዬቶች ላይ ሀሳቤን በማንጸባረቅ ስችል ይመስለኛል”ብለዋል። ...

Read More »

የመለስ መንግስት ጋዳፊ እንዲህ አይነት አሳዛኝ እጣ ከመድረሱ በፊት ለውጥ እንዲያደርጉ መክረናቸው ነበር ሲል መግለጫ ሰጠ

ኢሳት ዜና:- የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ቃል አቀባይ አቶ ደና ሙፍቲ እንደተናገሩት ” ገና ከመሰረቱ የሊቢያ አደባባዮች በህዝብ ሳይጥለቀለቁ ፣ ደም ፈሶ ህይወት ሳይጠፋ፣  የሙአመር ጋዳፊ የ42 አመታት ቤተሰባዊ አገዛዝ እንዲበቃ የህዝብ ጩህት ጆሮ እንዲያገኝ ሊቢያውያን ከሰብአዊነት ተሽረው አይጦች ሲባሉ ኢትዮጵያ ይህ አካሄድ እንደማያዋጣና ጋዳፊ ከመፍትሄ ይልቅ የችግሩ አካል መሆናቸውን ስትገልጽ  ቆይታለች” ብለዋል። ቃለ አቀባዩ “ጋዳፊ  የኢትዮጵያንም ሆነ የሌሎች ሀገራትን ጥሪ በተለመደው ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊ በሽብር ተጠርጥረው በታሰሩት ሰዎች ላይ በቂ ማስረጃ አለን አሉ፤ በሌሎችም ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

ኢሳት ዜና:- አቶ መለስ ለፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት በመድረክ አመራር ውስጥ በርካታ የአሸባሪ ቡድኖች አባላት አሉ  ብለዋል። እንደርሳቸው ገለጣ የአሸባሪ ቡድኖች የተባሉት የኤርትራ መንግስት፣ ግንቦት7፣ ኦነግ፣ ኦብነግና በአገር ውስጥ በህጋዊ ሸፋን የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ናቸው። አቶ መለስ እንደሚሉት በሽብር ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ግለሰቦች ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት የሚያሳዬው ማስረጃ በቅርቡ ለፍርድ ቤት ይቀርባል። የስዊድን ጋዜጠኞች እንደ ኢትዮጵያውያኑ ሁሉ በእኩልነት ...

Read More »

አቶ መለስ “በህዳሴው ዋዜማ ላይ እንገኛለን” እያሉ በሚናገሩበት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በዳቦ እጥረት እየታመሰች መሆኗ ተዘገበ።

ኢሳት ዜና:- ከ ዛሬ 20 ዓመት በፊት ስልጣን ላይ ሲወጡ የላቀው ምኞታቸው በ 10 ፤ ቢበዛ በ 15 ዓመት ውስጥ የ ኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስት ጊዜ ሲበላ ማዬት እንደሆነ አቶ መለስ ዜናዊ መናገራቸው ይታወሳል ። ይሁንና ከ20 ዓመት የስልጣን ቆይታቸው በኋላ በኢትዮጵያ መሬት ላይ በተጨባጭ የታየው ነገር አስከፊ ድህነትና ረሀብ መሆኑን፤ የአገዛዙ ገፈት ቀማሽ የሆኑት እጅግ ብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን ይናገራሉ። ዘይትና ሳሙና ...

Read More »

በአርባ ምንጭ በህዝቡና በመንግስት መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ አሣሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ።

ኢሳት ዜና:- እስካሁን ወደ 65 የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸው የታወቀ ሲሆን፤ የአካባቢው ህዝብም በመንግስት ላይ ማኩረፉ እየተነገረ ነው። የኢሳት ወኪሎች እንዳጠናቀሩት መረጃ ከሆነ፤ውጥረቱ ይበልጥ እየተባባሰ የመጣው፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በወረዳቸው፣ በዞናቸውና በቀበሌያችው በተንሰራፋው የመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት፣ ለችግር መጋለጣቸውን አዲስ አበባ በመምጣት ለመገናኛ ብዙሀን ይፋ ያደረጉ የአርሶ አደሮች ተወካዮች ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ነው። በመጀመሪያ የታሰሩት፤ አቤቱታ ለማቅረብ  አዲስ አበባ የመጡት አቶ ዳሞታ ...

Read More »

የሆስተሷ የአበራሽ ኃይላይን ሁለት ዓይኗን አጥፍቶ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰባት ተጠርጣረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡

ኢሳት ዜና :- ሆስተስ አበራሽ ለህክምና ከሄደችበት ባንኮክ- ታይላንድ ከሁለት ሣምንት በኋላ እንደምትመጣ በአቃቤ ህግ የተገለጸ ሲሆን ሁለቱም ዓይኖቿ መቶ በመቶ የማየት ተስፋ እንደሌላቸው ከሀኪሞቿ እንደተነገራትና በጭንቅላቷ፣ በሰውነቷና በእጆቿ ላይ ያደረሰባት ከባድ ጉዳትን በመታከም ላይ ነች ሲሉ አጎቷ አቶ አስመላሽ ሞላ ለሪፖርተራችን ገልጸዋል፡፡  የአቃቤ ህግ የክስ ቻርጅ እንደሚያስረዳው በመዝገብ ቁጥር 112 ሺ 331 አቶ ፍሰሃ ታደሰ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪ ...

Read More »

አቶ ያረጋል አይሸሹም ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳ በሁዋላ በቁም እስር ላይ እንደሚገኙና ንብረታቸውን ካስረከቡ በሁዋላም ወደ ወህኒ እንደሚወርዱ ታወቀ

ኢሳት ዜና :- የቀድሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያረጋል አይሸሹም፣ ያለመከሰስ መብታቸውን ፓርላማው አንስቷል፡፡ አቶ ያረጋል የተነሱት የሕግ፣ የፍትሕና የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸውን ጠቅሶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ከተቀበለው በሁዋላ ነው። አቶ ያረጋል የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ በክልሉ እንዲሠሩ በጀት ...

Read More »

14 ወጣት የሠራዊቱ አባላት የአቶ መለስን አገዛዝ በመቃወም የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄን መቀላቀላቸው ተገለፀ።

ኢሳት ዜና :- የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ- በምህፃረ-ቃል “ትህዴን”  የወጣቶቹንና የወታደሮች ፎቶ አያይዞ ለኢሳት የላከው መግለጫ እንደሚያለክተው፤ የአቶ መለስን ሥርዓት ከድተው ወደ ትህዴን የተቀላቀሉት ወጣቶች፤ ከአማራ፣ ከኦሮሚያ ፣ከትግራይና ከደቡብ ክልሎች  የመጡ ናቸው። ወ/ር ብዙዓለም ሽፋራው እርቄ፣ አስር አለቃ ሁሴን መሃመድ አህመድ፣ ምክትል አስር አለቃ ቦጋለ ኩራቻ ፣ወታደር እድሪስ ሁሴን መሃመድ፣ አስር አለቃ ሁሴን ደመቀ ተገኘ፣ ምክትል አስር አለቃ ኢብራሂም ደግፌ ...

Read More »