ህዳር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ፣ ኖቬምበር 14 ፣ 2011 ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ፣ የመለስ መንግስት በንጹሀን ዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን እመቃ አውግዘዋል፣ በእስር ላይ የሚገኙት የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የመለስ መንግስት በርካታ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን በሽብር ስም ማሰሩ ይታወቃል።
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አርቲስት ደበበ እሸቱ ከእስር ተለቀቀ
ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብር ወንጀል ተከሶ ለአለፉት አምስት ወራት በእስር ላይ ይገኝ የነበረው አርቲስ ደበበ እሸቱ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ መፈታቱ ታወቀ። አርቲስ ደበበ ከጠበቃው ጋር እንዳይገናኝ ተደርጎ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል። አርቲስቱ አርብ ህዳር 1 ቀን 2004 ዓም ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ በፌደራል ፖሊሶች ታጅቦ ወደ ቤቱ መወሰዱንና ቤተሰቦቹ እንዲረከቡት መደረጉን በስፍራው አብረውት የነበሩ ወዳጆቹ ለኢሳት ተናግረዋል። ...
Read More »በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የድምጽና የምስል ማስረጃ ባለመሟላቱ ፍርድ ቤቱ ማስረጃ የመመልከቱን ሂደት እንዲቋረጥና ተለዋጭ ቀጠሮ ለህዳር 6 ቀን ሰጠ
ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢብዴፓ) ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚያብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ ሂሩት ክፍሌ፣ የፍትህ ዓምደኛ ርዮት ዓለሙ ትናንት ህዳር 1 ቀን 2004 ዓም አቀርበዋለሁ ያለው የድምጽና የምስል ማስረጃ ባለመሟላቱ ፍርድ ቤቱ ማስረጃ የመመልከት ሂደቱ እንዲቋረጥ ወስኖ ተለዋጭ ...
Read More »የአቶ መለስ መንግስት በስድስት ጋዜጠኞች ላይ የመረሰተውን የሽብርተኝነት ክስ በፍጥነት እንዲያነሳ ሲ.ፒ.ጄ ጠየቀ
ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት በስድስት ጋዜጠኞች ላይ የመረሰተውን የሽብርተኝነት ክስ በፍጥነት እንዲያነሳ፤ መቀመጫውን ኒው ዮርክ ያደረገው ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት-ሲ.ፒ.ጄ ጠየቀ። ሲ.ፒ.ጄ ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግስት አዲስ ባወጣው የፀረ-ሽብር ህግ መሰረት ሰሞኑን ስድስት ጋዜጠኞችን ጨምሮ በ 24 ሰዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መመስረቱን በመጥቀስ፤ ክስ ከተመሰረተባቸው ጋዜጠኞች መካከል እስክንድር ነጋ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በእስር ...
Read More »አቤ ቶክቻው ተሰደደ
ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለዛ ባለው አዝኛኝ ጽሁፉ ፖለቲካውን እያዋዛ የህብረተሰቡን ብሶት ሲያሰማ የቆየው “አቤ ቶክቻው” አገር ለቅቆ ወጣ። አቤ ቶክቻው ቀደም ሲል ባውራምባ ታይምስ፤አሁን ደግሞ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን እያዋዛ በማቅረቡ በተደጋጋሚ ከደህንነት ሀይሎች ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው ቆይቷል። በተለይ ባለፈው ሳምንት፦” ጠቅላይ ሚኒስትሬ እንደሚያነቡኝ ባወቅኩ ጊዜ ደስ አለኝ”በሚል ርዕስ አቶ መለስ የዘንድሮውን ፓርላማ የ ስራ ዘመን ሲከፍቱ ...
Read More »በዋካ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የቶጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የህዝቡ ጥያቄ ፍትሀዊ ሆኖ እያለ እኛ ግን እስከዛሬ ስናፍነው ነበር በማለት ስልጣናቸውን ለቀቁ
ህዳር 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በዋካ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የቶጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የህዝቡ ጥያቄ ፍትሀዊ ሆኖ እያለ እኛ ግን እስከዛሬ ስናፍነው ቆይተናል፣ ከእናንተ ጋር ከእንግዲህ አልሰራም በማለት ስልጣናቸውን ለቀቁ የኢሳት የደቡብ ወኪል እንደገለጠው አስተዳዳሪው አቶ ፈቃዱ ወልደ ሩፋኤል “የህዝቡ ጥያቄ ፍትሃዊ ሆኖ እያለ፣ እኛ ግን ጥያቄውን ለማፈን በተደጋጋሚ ሙከራ አድርገናል” በማለት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል። እርሳቸውን ተከትለው ሌለው ስልጣን ...
Read More »በእስር ላይ በሚገኙት ፖለቲከኞች ላይ አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ታወቀ
ህዳር 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደገለፀው ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይቀርባሉ ተብሎ ጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ፣ የፓርቲው የአመራር አባላት ናትናኤል መኮንን፣ አሳምነው ብርሃኑ፣ የመኢዴፓ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ዘመኑ ሞላ እና ...
Read More »የኢህአዴግ መንግሥት ሽብርተኞች ብሎ በአንደኛ ተከሳሽ ኤልያስ ክፍሌ የክስ ፋይል በከሰሳቸው ላይ ዐቃቤ- ሕግ የሰው ምሥክሮችን አሰማ
ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት ሽብርተኞች ብሎ በአንደኛ ተከሳሽ ኤልያስ ክፍሌ የክስ ፋይል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢብዴፓ) ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚያብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ ሂሩት ክፍሌ እና የፍትህ ጋዜጣ ዓምደኛ ርእዮት ዓለሙ ላይ ዐቃቤ- ሕግ የሰው ምሥክሮችን አሰማ፤ የድምጽና የምስል ማስረጃዎችን ደግሞ ለማቅረብ ለዓርብ ህዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ...
Read More »የስምንተኛ ክፍል የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት መጽሀፍ አንዳንድ ገጾች ተቀደው እንዲያቃጥሉ ታዘዙ
ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብዙ ሚሊዮኖች ዶላር ወጥቶበት እንዲታተም በተደረገው የስምንተኛ ክፍል የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት መጽሀፍ ውስጥ “ተማሪዎችን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ የሚያበረታቱ ጽሁፎች ተካትተዋል” በሚል ምክንያት፣ ተማሪዎችና መምህራን የመጽሀፉን አንዳንድ ገጾችን ቀደው እንዲያቃጥሉ ታዘዙ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው መጽሀፉ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ ታትሞ ወደ አገር ውስጥ የገባ ነው። መጽሀፉ ባለፈው መስከረም ወር በሚታደልበት ጊዜ ተማሪዎች መጽሀፉን ቀድደው ...
Read More »“ከኢትዮጵያ ጋር የረዥም ጊዜ ግንኙነት ቢኖረንም ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግን ዝም እንድንል የሚያደርገን አይደለም” ሲሉ የጀርመን ምክር ቤት አባላት አስታወቁ
ጥቅምት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ከኢትዮጵያ ጋር የቆየና የሰነበተ የረዥም ጊዜ ግንኙነት አለን፤ይህ ግን በኢትዮጵያ እየታየ ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዝም እንድንል የሚያደርገን አይደለም” ሲሉ የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት አስታወቁ። የምክር ቤት አባላቱ ይህን ያስታወቁት በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በሰጡት ወቅት ነው። የሊበራል ፓርቲ ተወካዩዋ ወይዘሮ ማርቲና ሹስተር ኢትዮጵያ አዲስ ባወጣችው የፀረ-ሽብር ህግ ...
Read More »