ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸውን መግለጥ ያልፈለጉ የክልሉ መምህራን እንደሚሉት፣ መንግስት የክልሉን የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት፣ አቶ መንግስቱ አህመዴን፣ ከስልጣን ለማስወገድ የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉ ፣ በመምህራን እና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ እንዲጨምር አድርጎታል። የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ የወረዳ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው “የማህበሩ ሊቀመንበር የግንቦት7 አባል ነው፤ መምህራን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ እና ከመንግስት ጋር እንዲጋጩ እየቀሰቀሰ ነው” በማለት መናገራቸው ታውቋል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ኮሚቴዎች በባህር ዳር ተገናኝተዉ መነጋገራቸዉን ቪዢን ዴይሊ የተሰኘዉ የሱዳን የሚዲያ ማእከል ገለጸ
ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኮሚቴዉ በድንበር አካባቢ በድብቅ የሚካሄደዉን የጦር መሳሪያ ዝዉዉር ለመግታት፤ አዘዋዋሪዎቹን ለመያዝና ለማሰር፤ በድንበሩ አካባቢ ያሉ ትናንሽ ከተማዎችና ወረዳዎች በፀጥታ ጥበቃ ረገድ ይበልጥ በሚጠናከሩበት፤ እና መረጃ በሚለዋወጡበት መንገድ ላይ መክሯል። እንዲሁም የቀንድ ከብት በሽታዎችን ለመቆጣጠርና የእንሰሳት የህክምና መስጫ ጣቢዎችን ለማቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ ተገልጿል። የሱዳን የድንበር ኮሚቴ የተመራዉ ያልተማከለዉ የመንግስት ም/ቤት ዋና ፀሃፊ በሆኑት ፕሮፌሰር ...
Read More »በጋሞጎፋ ዞን በጨንቻ ከተማ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ
ህዳር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአካባቢው የሚኖሩት የጋሞ ተወላጆች ተቃውሞውን ያነሱት፣ የእርሻ ማሳቸውን ወደ ከተማ ለማካለል ሙከራ ማድረጉን ለመቃወም ነው። ከሁለት ቀናት በፊት 5 ሺ የሚጠጉ ነዋሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ተገኝተው ሰልፉን የበተኑ ሲሆን፣ መንግስትም በአካባቢው የስልክ ግንኙነት እንዳይኖር አድርጎ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ውጥረቱ አሁንም እንዳለ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ ህዝቡ ሰልፉ ከተበተነ በሁዋላም ...
Read More »ኢትዮጵያ ከቻይና እና ከህንድ ባንኮች ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየተበደረች መሆኑ ታወቀ
ህዳር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትራንስፎርሜሽን እና እድገት ስም የመለስ መንግስት ባለፉት 10 አመታት ብቻ ከቻይናና ከህንድ መንግስታት ከ 25 ቢሊዮን ዶላር በላይ መበደሩን መረጃዎች አመልክተል። ይህን ኢትዮጵያ ከፍተኛ በሆነ ብድር ከተዘፈቁ አገሮች ተርታ እንዳስመደባት ታውቋል። ለኢትዮጵያ ከፍተኛውን ብድር ከሰጡት የቻይና ባንኮች መካከል ፣ ኤግዚም ባንክ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ አበድሯል። የባንኩ ምክትል ስራ አስኪያጅ ...
Read More »ሻሸመኔ ውስጥ ሂጃብ ለብሰው የተገኙ ተማሪዎችን ለመከልከል በተፈጠረ ግርግር ከ50 ያላነሱ ሰዎች መታሰራቸው ታወቀ
ህዳር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ በምህርት ሃላፊዎች በኩል ቢነገራቸውም፣ ተማሪዎቹ ግን መብታችን ነው በማለት ተቃውሞ አንስተዋል። በዚሁ ጭቅጭቅ በተፈጠረ ግርግር ከ50 ያላነሱ ሰዎች መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አህባሽ የተባለ የእስልምና እምነት አስተምህሮ ለማስፋፋት ፖሊሲ ቀርጾ መንቀሳቀሱን በውጭ አገር የሚገኙ የእምነቱ ምሁራን መቃወማቸው ይታወሳል። ከስድስት ወራት በፊት 8 ...
Read More »ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞና በጋሬ ማህበረሰብ አባላት መካከል የተቀሰቀሰ ከፍተኛ ግጭት ወደ ኬንያ ድንበር ተሻግሮ- አራት ኬንያውያን በኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ገልፍ ታይምስ ዘገበ
ህዳር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኬንያ ምስራቃዊ ክልል የፖሊስ ኮማንደር ማርኩስ ኦቾላ በሞያሌ ቀጣና “አዲ” ተብሎ በሚጠራውና ከኢትዮጵያ ጋር በሚዋሰነው የኬንያ መንደር በትንሹ አራት ሰዎች የተገደሉት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በ ኦሮሞና በ ጋሬ ብሄረሰብ አባላት የተከሰተ ከፍ ያለ ግጭት ወደ ኬንያ በመዛመቱ እንደሆነ በኬንያ ፓርላማ ቀርበው አስረድተዋል። “ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት በክልላቸው ውስጥ የተነሳውን ግጭት እንዲያስቆሙ ነግረናቸዋል። እኛም ከነሱ ጋር በመሆን ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያን ህዝብ ሽብር የሚያስተምሩ ይመስላል ሲሉ ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ተናገሩ
ህዳር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያን ህዝብ ሽብር የሚያስተምሩ ይመስላል ሲሉ ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ተናገሩ ፕሮፌሰሩ ዛሬ ቅዳሜ ታትሞ በወጣው ፍትህ ጋዜጣ ላይ ” ዳገት ላይ ሰው ጠፋ” በሚል ርእስ ባወጡት ጽሁፍ ፣ በስንት ነገር እየተዋረድን ገለባ እንሆናለን፣ በስንት ነገር እያፈረን አንገታችንን እንደፋለን?'” ሲሉ በመጠየቅ ፣ የአንዳንድ ባለስልጣኖች ንግግርም ሆነ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሽብርን የሚያስተምሩ ይመስላል” ...
Read More »የአማራ ክልል መምህራን ማህበር ሊቀመንበርን ከስልጣን ለማውረድ ሙከራ የሚያደርገው መንግስት፣ ከመምህራን ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብቶአል
ህዳር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል መምህራን ማህበር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ መንግስቱ አህመዴ፣ ናዝሬት በተካሄደው አገር አቀፍ የመምህራን ማህበር ጉባኤ ላይ ስብሰባ ረግጦ ወጥቷል ተብሎ ነው እስካሁን ድረስ ይፋ ባይሆንም፣ በመንግስት ግፊት የአገር አቀፉ የመምህራን ማህበር ግለሰቡን ከሀላፊነት አግደዋቸዋል። ይሁን እንጅ መምህር መንግስቱ በክልሉ መምህራን ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸው በመሆኑ መንግስት እገዳውን በይፋ ለመምህራን ለማስታወቅ አልደፈረም። መምህር መንግስቱ ...
Read More »አኬልዳማ የፈጠራ ድራማ ፣ የመለስ አገዛዝ ካልተገደደ በስተቀር በፈቃዱ ከዘረኛና አምባገነናዊ አቋሙ ፈቀቅ እንደማይል በማያሻማ ሁኔታ አሳይቶናል ሲል የግንቦት 7 ንቅናቄ ገለጠ
ህዳር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አኬል ዳማ ተብሎ በመለስ መንግስት የተቀነባበረው የፈጠራ ድራማ ፣ የመለስ አገዛዝ ካልተገደደ በስተቀር በፈቃዱ ከዘረኛና አምባገነናዊ አቋሙ ፈቀቅ እንደማይል በማያሻማ ሁኔታ አሳይቶናል ሲል የግንቦት 7 ንቅናቄ ገለጠ ንቅናቄው “አኬልዳማን ይመልከቱ፣ መለስን ለማስወገድ ይነሱ” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ፣ አኬልዳማ ፊልም ” የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ምን ያህል ፈሪ እና በፍርሃቱም ምክንያት ምን ያህል ጨካኝ እንደሆነ ይረዳሉ። ...
Read More »የመለስ መንግስት የስልክና የኢሜል መልእክቶችን ለመጥለፍ እንዲሁም የሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለማፈን የሚጠቅመውን ቴክኖሎጂ ከህንድና ከቻይና ኩባንያዎች መግዛቱን ዊኪሊክስ አጋለጠ
ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመለስ መንግስት የስልክና የኢሜል መልእክቶችን ለመጥለፍ እንዲሁም የሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለማፈን የሚጠቅመውን ቴክኖሎጂ ከህንድና ከቻይና ኩባንያዎች መግዛቱን ዊኪሊክስ አጋለጠ ዊኪሊክስ በዋጣው አዲስ መረጃ በአለም ላይ ለዚሁ ተግባር የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚሸጡ የ150 ኩብንያዎችን ስም ይፋ አድርጓል። የዊኪሊክሱ መስራችን ባለቤት የሆነው ዊሊያም አሳንጄ ለዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እንደተናገረው አንድ የህንድ ኩባንያ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የስለላና የማፈኛ ...
Read More »