ሻሸመኔ ውስጥ ሂጃብ ለብሰው የተገኙ ተማሪዎችን ለመከልከል በተፈጠረ ግርግር ከ50 ያላነሱ ሰዎች መታሰራቸው ታወቀ

ህዳር 25 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ በምህርት ሃላፊዎች በኩል ቢነገራቸውም፣ ተማሪዎቹ ግን መብታችን ነው በማለት ተቃውሞ አንስተዋል።

በዚሁ ጭቅጭቅ በተፈጠረ ግርግር ከ50 ያላነሱ ሰዎች መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አህባሽ የተባለ የእስልምና እምነት አስተምህሮ ለማስፋፋት ፖሊሲ ቀርጾ መንቀሳቀሱን  በውጭ አገር የሚገኙ የእምነቱ ምሁራን መቃወማቸው ይታወሳል።

ከስድስት ወራት በፊት 8 የሚጠጉ የወሎ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ሂጃብ በመልበሳቸው ማእከላዊ እስር ቤት መታሰራቸው ይታወቃል።

በሻሸመኔ በተፈጠረው ግርግር የታሰሩት ሰዎች ስለመፈታትና አለመፈታታቸው እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።