የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያን ህዝብ ሽብር የሚያስተምሩ ይመስላል ሲሉ ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ተናገሩ

ህዳር 23 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያን ህዝብ ሽብር የሚያስተምሩ ይመስላል ሲሉ ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ተናገሩ ፕሮፌሰሩ ዛሬ ቅዳሜ ታትሞ በወጣው ፍትህ ጋዜጣ ላይ ” ዳገት ላይ ሰው ጠፋ” በሚል ርእስ ባወጡት ጽሁፍ ፣ በስንት ነገር እየተዋረድን ገለባ እንሆናለን፣ በስንት ነገር እያፈረን አንገታችንን እንደፋለን?'” ሲሉ በመጠየቅ ፣ የአንዳንድ ባለስልጣኖች ንግግርም ሆነ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሽብርን የሚያስተምሩ ይመስላል” ሲሉ አክለዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አክለውም ” አንድ ኢትዮጵያዊ እራሱን በእሳት ሲያቃጥል ለመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል። ባለስልጣኖች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አስተማሪው ራሱን ማቃጠሉ የ ሽብር ጥንስስ ሊሆን እንደሚችል የተረዱት አይመስልም” ይላሉ።

ለመሆኑ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት በአሜሪካና አውሮፓ እንዲኖሩ ከተፈቀደላቸው፣ የሽብርተኝነት ትግሉ አጋር ተደርጋ የምትቆጠረው አሜሪካ እንዴት እነዚህን ኢትዮጵያውያንን ከአገሯ አላስወጣቻቸው በማለት የሚጠይቁት ፕ/ር መስፍን ፣ ወይ አሜሪካ ወይም ኢህአዴግ የአለማቀፍ ሽብር ትርጉሙ አልገባቸውም ሲሉ ተሳልቀዋል።

በዚሁ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ወጣቱ ብእረኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ አኬላዳማ በሚል የቀረበው ፊልም ደረጃውን ያልጠበቀ በአማተር ተዋንያን የተሰራ ቀሽም ድራማ ነው ብሎታል።

ተመስገን አንድ “አቶ ይርጋ ይመር የተባሉ ሰው የጓደኛዬንና የእኔን ሚስት ገደሉ ፣ እንዲህ ያለ ግፍ ይሰራል ይህን ሁሉ የሚአደርገው መለስ ዜናዊ ነው ” ብለው የሚናገሩትን፣ መለስ ዜናዊ ነው የሚለውን በመቁረጥ
ማቅረባቸውንም በጽሁፉ አጋልጧል።

አኬልዳማው የአይሁድ ወይስ የኢህአዴግ በሚል ርእስ ጽሁፉን ያሰፈረው ተመስገን ፣ በድራማው ላይ የተመለከትነው ሰላማዊ ትግል እንጅ ሽብር አይደለም ብሎአል።

ኢህአዴግ የሚበጀበው ለውጥ ማምጣት እንጅ ህዝብን ማሸበር አለመሆኑንም ተመስገን ምክሩን ለግሷል።