.የኢሳት አማርኛ ዜና

ባይዶዋን የተቆጣጠረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ከተማዋን ለአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል አስረክቦ ሊወጣ ነው ተባለ

ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው  የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ግዛት ለቆ እንዲወጣ የተወሰነው የአፍሪካ ህበረት የሰላምና የደህንነት ጉባኤ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ ፣ የኬንያ ፣ የዩጋንዳ እና የብሩንዲ ጥምር ጦር ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለውን አልሸባብን ለመውጋት በእየአቅጣጫው ዘመቻዎችን መክፈታቸው ይታወሳል። የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱዌሊ ሙሀመድ በበለደወይን መገኘታቸውን ቢቢሲ አክሎ  ዘግቧል። የኢትዮጵያን ጦር 5 ሲ የሚሆኑት ...

Read More »

ባንኮች ደንበኞቻቸው ከ200 ሺ ወይም ከ10 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ሲያስገቡም ሆነ ሲያስወጡ ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የመረጃ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዙ

ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ደንበኞቻቸው ከ200 ሺ ወይም ከ10 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ሲያስገቡም ሆነ ሲያስወጡ ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የመረጃ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዙ የጸረ ሽብር የመረጃ መእከል ለግልና ለመንግስት ባንኮች ባወረደው መመሪያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊም ሆነ የውጭ አገር ዜጋ ከ200 ሺ ብር ጀምሮ በባንኮች ለማስቀመጥ ወይም ለማውጣት በሚሄድበት ጊዜ፣ ባንኮች የግለሰቦችን ስምና ማንነት ለብሄራዊ ...

Read More »

ኢቲቪ ‘‘አኬልዳማ’’ በሚል ርዕስ ያስተላለፈው ፕሮፓጋንዳ የተሰራው መንግስት እልክ በመጋባቱ መሆኑን አቶ በረከት ስምኦን ጠቆሙ

ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ‘‘አኬልዳማ’’ በሚል ርዕስ ያስተላለፈው ፕሮፓጋንዳ  እንዲሰራ የተወሰነው፤ መንግስት  ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከፕሬሶች  ጋር እልክ በመጋባቱ  መሆኑን አቶ በረከት ስምኦን ጠቆሙ። አብዛኛው ህዝብ-ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዓመታዊ ግብር  አልከፍልም ማለቱንም ተናገሩ። ለዝርዝሩ ደረጀ ሀብተወልድ፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በረከት ስምኦን  ሰሞኑን ለሕዝብ ...

Read More »

የገናን በአል ምክንያት በማድረግ የእርድ እንስሳት ዋጋ ጨመረ

ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው የገናን በአል ተከትሎ የእርድ እንስሳት ዋጋና  በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የእርድ ከብት ከ12 ሺ ብር ጀምሮ በመሸጥ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ዶሮ ከ170 እስከ 200 ብር፣ በግ ከ1200 ብር እስከ 1700 ብር፣ ፍየል ከ1000 እስከ 1800 ብር በመሸት ላይ ነው። ቅቤ  በኪሎ በአማካኝ 130 ብር ዘይት 24 ብር ...

Read More »

ዶክተር መረራ ጉዲና በድጋሚ ድርጅታቸው ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ (ኦህኮ) ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላይ ጉባኤ፤ ፓርቲውን ላለፉት 16 ዓመታት ሲመሩ የቆዩትን ዶ/ር መረራ ጉዲናን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መረጧል ። በ1997 ዓ.ም ከቀድሞ ቅንጅት በመቀጠል በፓርላማው ከፍተኛ ድምፅ አግኝቶ የነበረው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሕብረትም (ኢዴኃህ)፤ እንዲፈርስ ተወስኗል። “እርስዎ በድጋሚ የተመረጡት ፓርቲው ሌላ ሰው ስለሌለው ነው ወይ?” ተብለው  የተጠየቁት ...

Read More »

በ3 ቁጥር ማዞሪያ ቶታል አካባቢ የሚገኘው የአወሊያ ቁጥር 2 ት/ት ቤት ተማሪዎች በትላንትናው ቀን ማክሰኞ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በ3 ቁጥር ማዞሪያ ቶታል አካባቢ የሚገኘው የአወሊያ ቁጥር 2 ት/ት ቤት ተማሪዎች በትላንትናው ቀን ማክሰኞ በ እስላማዊ ምክር ቤት ወይም መጅሊስ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ፡፡ ተማሪዎቹ ቀኑን ሙሉ የዋለ ተቃውሞ ሊያሰሙ የቻሉበት ምክንያት፤ መጅሊሱ የአረብኛ መምህሮችን ከትምህርት ቤቱ በማባረሩና፤ በምትኩ በራሳቸው ያሰለጠኗቸውንና የአሕባህሽ ተከታይ የሆኑትን በማሰማራት ተማሪዎቹን ከእስልምና ለማስወጣት በማሰባቸው ነው። ተማሪዋቹ የአህባሽን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በመንግስት ላይ ድል ተቀዳጀሁ አለ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የዘመቻ ደምመላሽ ሰራዊት በሰሜን ጎንደር ላይ አርማጭሆ ዶጋው ልዩ ስሙ ጉርማጭት በተባለ አካባቢ ላይ በታህሳስ 21- 2004 ዓ.ም በመቶ አለቃ ገበየሁ ከሚመራው ልዩ ሃይል ጋር በተካሄደ ውጊያ 9 የመንግስት ልዩ ሃይል ታጣቂዎች መግደሉን፣  16ት ወታደሮችን ደግሞ ማቁሰሉን ገልጧል። ከባድና ቀላል መሳሪያዎችን ከነ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን ያስታወቀው  የኢሕአግ ወታደራዊ መምሪያ ፣ የዘመቻ ደምመላሽ ...

Read More »

ሶማሊ-ላንድ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የተመዘገቡ 20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አስገድዳ ወደ ኢትዮጵያ መለሰች

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ሶማሊ-ላንድ  በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የተመዘገቡ 20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን  አስገድዳ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጓን ሂዩማን ራይትስ ዎች ገለጠ። ዳግም የዚህ ዓይነት ድርጊት እንዳትፈጽምም ጠይቋል። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር  ባለፈው ዲሴምበር 28፤  የሶማሊላንድ አስተዳደር  ለመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ወደ ሶስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ እንዲሰጣቸው አመልክተው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ያሉትን 20 ኢትዮጵያውያን በሀይል በማስገደድ ወደ ...

Read More »

በወጣቶች አነሳሽነት የተቋቋመው ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ መሥራች ጉባዔውን ባለፈው እሑድ አካሄዷ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲውን ከመሠረቱት ግለሰቦች መካከል መርህ ይክበር በሚል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት ይገኙበታል፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ቃል አቀባይ አቶ አርዓያ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እሑድ በፓርቲው ጽሕፈት ቤት በተካሄደው መሥራች ጉባዔ 150 ሰዎች የተሰበሰቡ ሲሆን፣ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ይልቃል ጌታሁን  የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ሰላሳ ሰባት አባላት ያሉት የፓርቲው ...

Read More »

“ ከአሁን በሁዋላ የኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ ተለይቶ የሚታይ አይደለም” ሲሉ አቶ አሚን ጁንዲ ገለጹ

ታህሳስ 25 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ዋና ፀሀፊ የሆኑት አቶ አሚን ይህን ያሉት፤ የድርጅታቸውን አዲስ የፕሮግራም ለውጥ አስመልክቶ ከህብር ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አዲሱ አቋማችሁ በአቶ መለስ ስርዓት ላይ ከሚፈጥረው ጫና አኳያ እንዲሁም እየለወጣችሁት ያላችሁት ለረዥም ጊዜ ስታራምዱት የቆያችሁትን አቋም ከመሆኑ አንፃር ከውስጥም ከውጭም ተቃውሞ ቢነሳባችሁ ምን ያህል ተዘጋጅታችሁዋል? በማለትም የራዲዮው ...

Read More »