.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሳዉዲ መካ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ያለፈቃድ ከሚገባቸዉ ጊዜ በላይ ሲኖሩ የተገኙ 85 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ፡ የየመን እና የህንድን ፓስፖርት የያዙ  በሳዉዲ አረቢያ የሄዱበትን የሃጅና ኡምራ የፀሎት ጉዞ ካጠናቀቁ በሁዋላ ያለፈቃድ በመኖራቸዉ 85 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አረብ ኒዉስ ገለፀ። ግለሰቦቹ በህገ ወጥ መንገድ በኮንስትራክሽንና በሌሎች የጉልበት የስራ መስኮች የተሰማሩ እንደነበር ሌተና ኮሎኔል ሙሃመድ አል ሁሴን የመካ ፓስፖርት ፖሊስ ሃላፊ ገልፀዋል። በማእከላዊ ዞን ዉስጥ አጅያድ፤ ሬኦ፤ ካድዋ በተባሉት አካባቢዎች ...

Read More »

በጄኔራል ከማል ገልጁ የሚመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ፣ የሚደነቅ ነው ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ተናገሩ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም ኢሳት ዜና:- የቀድሞው የኦፌዴን ሊቀመንበር እና አሁን የንቅናቄው የክብር ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለኢሳት እንደተናገሩት  በጄኔራል ከማል ገልቹ የተመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ በደስታ ነው የምከታተለው ብለዋል። “የኦሮሞ ህዝብ የሚሸሽ ወይም የሚገነጠል ህዝብ አይደለም” የሚሉት አቶ ቡልቻ፣ ሁሉም በዚህ ሀሳብ ዙሪያ ቢሰባሰብ ጤነኛ እንሆናለን ሲሉ አክለዋል ። አቶ ቡልቻ የጄኔራል ከማል ቡድን ከዚህ በፊት ሌላ ...

Read More »

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ኤልያስ ክፍሌ ከጥፋት ነፃ ናቸው አሊያም ጥፋተኛ ናቸው የሚል ፍርድ ዛሬ ሳይሰጥ ቀረ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ለዛሬ ለፍርድ ቀጥሮት የነበረውን በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባልና ጋዜጠኞች ላይ ከጥፋት ነፃ ናቸው አሊያም ጥፋተኛ ናቸው የሚል ፍርድ ዛሬ ሳይሰጥ ቀረ፡፡ የፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ በአሸባሪነት ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚያብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ...

Read More »

መንግስት በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ መስክሮችን አሰማ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት የፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ በነ በቀለ ገርባ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው ዘጠኝ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ከቦረና ሞያሌ እና ከሰሜን ሸዋ ኦሮሚያ ዞን ያስመጣቸውን አባላቱ አዲስ አበባ ሆቴል አስቀምጦ የምስክርነት ቃል በማስጠናት ዋና የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ያላቸውን 18 ሰዎች ትላንትና እና ዛሬ በዋለው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት አቀርቧል፡፡ የተቀሩ ሰባት  የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን፣ ...

Read More »

በአፋር ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል እንደጨመረ ነው ተባለ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም ኢሳት ዜና:-የአፋር ህዝብ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ አባቃላ እየተባለ በሚጠራው የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ በርካታ የተቃዋሚ መሪ ዘመዶች እና መንግስትን የሚቃወሙ አፋሮች በብዛት እየታጎሩ ነው። ከ300 በላይ የሚሆኑት አፋሮች ላለፉት 2 አመታት ፍትህ አጥተው በእስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው አስታውቋል። የአፋር ህዝብ ፓርቲ ዞን አንድ፣ ዞን ሁለትና ዞን ሶስት እየተባለ በሚጠራው አካባቢዎች አርብቶ አደሮችን እያፈናቀሉ መሆኑን ጠቅሶ፣ ይህን ...

Read More »

በፈረንሳይ ኣስገዶም ዮናታን (ኢስማኢል ኢብሳ )የተባለ ኢትዮጵያዊ በፖሊሶች ተደብድቦ መገደሉ ተሰማ

ጥር 1 ቀን 2004 ዓም ኢሳት ዜና:-በፈረንሳይ መዲና ልዩ ስሙ ካሌ እየተባለ በተለምዶ በሚጠራው ኣካባቢ ኣስገዶም ዮናታን (ኢስማኢል ኢብሳ )የተባለ ኢትዮጵያዊ በፖሊሶች ተደብድቦ መገደሉ ተሰማ ፡፡ ጋዜጠኛ ዘላለም ገብሬ ከአሜሪካ እንደዘገበው “ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ለመግባት ጥረት በማድረግ ላይ እያሉ በፈረንሳይ ፖሊሶች እና በኢትዮጵያኖች መካከል በተነሳው ኣለመግባባት አና በተፈጠረው ግብ ግብ  መሰረት ህይወቱ አልፎአል። ወጣት ከደረሰበት ጉዳት ህይወቱን ለመታደግ ወደ ሆስፒታል ...

Read More »

የኦፌዴንና የኦህኮ አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

የኢህአዴግ መንግሥት በአሸባሪነት ወንጀል ክስ መስርቶ በእስር ላይ ካዋላቸው ስድስት ወር የተጠጋቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ፓርቲ እና የመድረክ የአመራር አባል የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረንስ (ኦህኮ) ፓርቲ እና የመድረክ የአመራ አባል የሆኑት አቶ ኦልባና ሌሊሳ እና ሌሎች ሰባት የኦሮሞ ተወላጆች ዛሬ ታህሳስ 30 ቀን 2004 ዓ.ም  ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ ...

Read More »

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ፤የማልታ መንግስት ያሰራቸውን ከ50 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እንዲፈታ ጠየቀ

የንቅናቄው ዋና ስራ-አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በማልታ ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ለሚስተር ማሪዮ ፍሪጀሪ በፃፉት ደብዳቤ፤ ኢትዮጵያውኑ በእስር ላይ ረዘም ላለ ወራት መቆየታቸው  እጅግ እንዳሣሰባቸው ገልፀዋል። እንዲሁም በእስር ቤት ውስጥ ሳሉ በተለይ ከጤናቸው ጋር በተያያዘ እያጋጠሙዋቸው ላሉ ችግሮች በቂ የህክምና አገልግሎትና መድሀኒት ሊያገኙ አለመቻላቸውም ድርጅታቸውን እጅግ እንደሚያሣስበው አቶ ኦባንግ ገልጸዋል። አገራቸው ውስጥ በተፈጠረ ፖለቲካዊ ችግር ሳቢያ ወደ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲን ወክለው በመድረክ ውስጥ የሚሳተፉ ሦስት አመራሮች ተመረጡ

አንድነት  ለኢሳት በላከው መግለጫ ፤ፓርቲው ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ፤ የፖርቲው ሊቀ-መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ፣  ኢ/ር ዘለቀ ረዲ የመድረክ ሥራ አስፈጻሚና ህዝብ ግንኙነት፣ አቶ ተመስገን ዘውዴ ደግሞ  የመድረክ የውጪ ዘርፍ አባል ሆነው እንዲሰሩ   በሥራ አስፈጻሚው ተወስኗል።  ገዥው ፓርቲ አቶ አንዷለምን ጨምሮ ሌሎችን የፓርቲው አመራሮችና አባላት በማሰር ድርጅቱን ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት የተለያዩ ጫናዎች መፍጠሩን ቢቀጥልም፤ የፓርቲው እንቅስቃሴ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ -ክርስቲያን ህንፃዎች ህገ-ወጥ ተብለው ፈረሱ

 ቤተ-ክርስቲያኒቱ ዳግማዊ ምኒልክ ፊት ለፊት በሚገኘው በተለምዶ ‹‹ጠጠር ሕንፃ›› በሚባለው ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ግንባታዎቿ ሕገወጥ እየተባሉ እንዲፈርሱ መደረጋቸውን አጥብቃ ተቃወመች::  የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ አስተዳደር መሰንበቻውን በቤተክህነት ሕንፃ ላይ ባካሄደው ዘመቻ፤ አምስት የንግድ ቤቶችንና መጋዘኖችን አፍርሷል::  እንደ ሪፖርተር ዘገባ፤ ከቤተክህነት ቤቶቹንና መጋዘኖቹን ተከራይተው ይሠሩ የነበሩ ነጋዴዎች ወረዳው የወሰደውን ዕርምጃ ሕጋዊነት የሌለው ሲሉ ከቤተክህነት ጋር በመሆን እየተቃወሙት ይገኛሉ::  ተቃውሞ ...

Read More »