አንድነት ፓርቲን ወክለው በመድረክ ውስጥ የሚሳተፉ ሦስት አመራሮች ተመረጡ

አንድነት  ለኢሳት በላከው መግለጫ ፤ፓርቲው ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ፤ የፖርቲው ሊቀ-መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ፣  ኢ/ር ዘለቀ ረዲ የመድረክ ሥራ አስፈጻሚና ህዝብ ግንኙነት፣ አቶ ተመስገን ዘውዴ ደግሞ  የመድረክ የውጪ ዘርፍ አባል ሆነው እንዲሰሩ 

 በሥራ አስፈጻሚው ተወስኗል።  ገዥው ፓርቲ አቶ አንዷለምን ጨምሮ ሌሎችን የፓርቲው አመራሮችና አባላት በማሰር ድርጅቱን ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት የተለያዩ ጫናዎች መፍጠሩን ቢቀጥልም፤ የፓርቲው እንቅስቃሴ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን  አንድነት አስታውቋል።

 አንድነት በቅርቡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ፓርቲውን እንዲመሩ በሊቀመንበር አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።