.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአፋር ህዝብ ፓርቲ በአፋር ክልል በውጭ አገር ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዘ፣ የመንግስት እጅ ሳይኖርበት እንደመማይቀርም ገለጠ

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ለኢሳት እንደተናገሩት  በውጭ አገር ዜጎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ ፓርቲያቸው ያወግዘዋል። በኦጋዴን ክልል የኢትዮጵያ መንግስት በ9 ቻይናውያን እና ከ60 በላይ ኢትዮጵያውያን ከ4 አመታት በፊት የተፈጸመውን ግድያ ምክንያት በማድረግ እስከዛሬ ድረስ አካባቢውን የጦር ቀጠና ማድረጉ ይታወቃል። በሰሞኑ ጥቃት 5 የጀርመን፣ የሀንጋሪና ኦስትሪያ ዜጎች ሲገደሉ፣ ሁለት የጀርመን፣ እንድ የኦስትሪያና ...

Read More »

የኢትዮጵያ እና የኬንያ መንግስታት እንዲሁም የአለማቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ቀንድ ለረገፈው ከ50 እስከ 70 ሺ ለሚጠጋ ህዝብ ሞት ተጠያቂ ናቸው ተባለ

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኦክስፋምና ሴቭ ዘችልድረን በጋራ ባወጡት መግለጫ አምና በተከሰተው ረሀብ እስከ 70 ሺ የሚጠጋ ህዝብ ረግፏል። የአለማቀፉ ማህበረሰብ ጥያቄ ሲቀርብለት ፈጥኖ መለስ ቢሰጥ ኖሮ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያና የኬንያ መንግስታት  ረሀብ የለም በማለት ችግሩን ለመሸፋፋን መሞከራቸው  ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ የለም አንድም የሞተ ሰው የለም ብለው መናገራቸው ይታወሳል። ከቢቢሲ ዘገባ  ለመረዳት እንደሚቻለው የኬንያ ...

Read More »

50 ሺህ የ ኦሮሞ ተወላጆች በራሳቸው ቋንቋ እንዲማሩ ጥያቄ በማቅረባቸው ለ እስራትና ለተለያዩ በደሎች መጋለጣቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ገለጠ

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ( ኢሰመጉ) የሚለውን  ስያሜውን በመንግስት ጫና  ወደ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ለመለወጥ የተገደደው  ብቸኛው  የኢትዮጵያ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሰሞኑን ባወጣቸው ሁለት ልዩ መግለጫዎች፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች  የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን አጋልጧል ። ሰመጉ በ118ኛ እና በ119ኛ ልዩ መግለጫው የተፈፀሙትን  የመብት ጥሰቶች በስፋት በመዘርዘርም፤  የእርምት እርምጃ እንዲወስድባቸው ለሚመለከታቸው መንግስታዊና ...

Read More »

የኢትዮጵያ ህዝብ ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲነሳ ጄኔራል ከማል ገልቹ ጥሪ አቀረቡ

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህብር ራዲዮ ከላስቬጋስ እንደዘገበው፤የመገንጠል ሀሳቡን ከፕሮግራሙ ያወጣው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ በአሁኑ ወቅት የግንባሩ ዋነኛ ዓላማ በተባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ ክንድ ወያኔን በማንበርከክ ለህዝቡ ጥያቄ እንዲገዛ ማድረግ መሆኑን በድጋሚ በማረጋገጥ፤ ህዝቡ ሳይከፋፈልና ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። እንደ ህብር ዘገባ፤ጄኔራል ከማል  ይህን ጥሪ ያቀረቡት፤እሳቸው የሚመሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፤ በቅርቡ የመገንጠል ፕሮግራሙን  ...

Read More »

ኢሳትን ለመደገፍ በቦስተን የተዘጋጀው የእራትና የመዝናኛ ምሽት የተሳካ እንደነበር ኮሚቴው አስታወቀ

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ የገና በአልን በማስመልከት እና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳትን) ለመደገፍ በቦስተን የተዘጋጀው የእራትና የመዝናኛ ምሽት በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት እና ኢሳትንም ለመደገፍ በርካታ ገንዘብ የተሰበሰበበት እንደነበር ኮሚቴው አስታወቀ አርቲስት ታማኝ በየነ በሚታወቅበት ተመልካቾቹን በተለያየ ስሜት ውስጥ በሚከተው በቭድዮ መረጃዎች እና ቀልዶች በሚዋዛው ንግግሩ ሃገራችን ያለችበትን ሁኔታ ለዝግጅቱ ታዳሚዎች አስረድቷል! ንግግሩን የጀመረው ቦስተን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እጅግ ...

Read More »

ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች ያለፈቃዳቸው ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲነሱ ተደርጓል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ክስ አቀረበ

ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የሰብአዊ መብቶች አቀንቃኝ ድርጅት “ሞትን እዚህ እየጠበቅን ነው፤ በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል ሰዎች በሀይል ከቦታቸው እየተፈናቀሉ በመስፈር ላይ ናቸው” በሚል ርእስ  ባወጣው መግለጫ የመለስ መንግስት ሰፈራ በሚባለው መርሀ ግብር ከ70 ሺ በላይ የጋምቤላ ተወላጆችን ከቀያቸው አፈናቅሎ፣ ምግብ፣ የእርሻ መሬት፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎት በሌለበት ቦታ አስፍሯቸዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በሰፈራው አንሳተፍም ባሉት ሰዎች ላይ የሀይል ...

Read More »

ፈኖተ ነጻነት ያሳለፍነው ሳምንት በመላ አገሪቱ ውስጥ ውጥረት የሰፈነበት ነበር አለ

ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነጻነት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውጥረት ሰፍኖ መሰንበቱን አስነብቧል። በምእራብ ጎጃም ዞን በአዴት ከተማ ቤት ከማፍረስ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ አንድ የወረዳ ባለስልጣን መገደሉንና ሎሎች ሶስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጧል። በአሁኑ ጊዜም ህዝቡ ቤቱን ላለማስፈረስ በመወሰኑ፣ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑን ጋዜጣው ዘግቧል። በጅማ ዩኒቨርስቲ ደግሞ አንድ የግቢው ሰራተኛ የተወሰኑ ተማሪዎችን ሰብስቦ እናንተ ...

Read More »

በእስራኤል ኢትጵያዊቷ ከስራ ሃላፊነቷ በዘረኝነት ምክንያት መነሳቷ እያነጋገረ ነዉ

ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእስራኤል ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ከስራ ሃላፊነቷ እንድትነሳ ያደረጋት የኢትዮጵያዊቷ ፀጋ መላኩ ጉዳይ ከዘረኝነት ጋር የተያያዘ መሆኑን የቴል-አቪቭ የጋዜጠኞች ማህበር ዳይሬክተር ዮሲ ባርሞሃ መናገራቸዉን ጀሩሳሌም ፖስት የተባለዉ ጋዜጣ ገልጿል። ፀጋ መላኩ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት/እስራኤላዊ በመሆን የእስራኤል ረሸት አሌፍ የራዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር በመሆን ለሶስት አመታት በኮንትራት ስታገለግል የቆየች ሲሆን በሙያና ተግባሯ እጅግ ተቀባይነትን አግኝታ እንደነበር ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት የሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ

ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በለድ-ዌይን በተባለዉ የማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ክልል ዉስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ሁለት የሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን ኦጋዴን ቱዴይ የዜና ምንጭ ከናይሮቢ ገለፀ። በቁጥጥር ስር የዋሉት የሶማሊያ የሽግግር መንግሰት ተባባሪ የሆነዉ የአህሉ ሱና ሱፊ ፓራ ሚሊቴሪ ቡድን መሪ አዳን አዋሌና ከፊል ራስ ገዝ የሆነዉ የሸበሌ ሸለቆ አስተዳዳሪ አብዱል ፈታህ ሃሰን ጃማ ናቸዉ። መሪዎቹን የኢትዮጵያ ...

Read More »

በጋምቤላ ሲካሄድ የሰነበተው ግምገማ አነጋጋሪ ሆኗል ሲል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ገለጠ

ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ሲካሄድ በሰነበተው ግምገማ ከሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ ውጪ መወሰኑ አነጋጋሪ ሆኗል ሲል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ  ገለጠ፣ የኢሳት የጋምቤላ ምንጮች ግን ፕሬዚዳንቱም በቅርቡ ከስልጣን ይወርዳሉ ይላሉ። ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ዜና የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋሕአዴን/ ከፌደራል ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት በተላኩት አቶ ዘመዴ ዘመድኩንና አቶ አለባቸው ንጉሤ አማካይነት ከታህሳስ 17 ቀን ...

Read More »