መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል እየታዩ ስላሉት ተደጋጋሚ ግጭቶች፣ ከፍተኛ የሆነ ረሀብ፣ የፍትህ፣ የመልካም አስተዳዳር እጦት እንዲሁም የማዳበሪያ እዳን አስመልክቶ ለኢሳት ሰፊ ቃለ ምልልስ የሰጡት የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና የደቡብ ቀጣና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ ከችግሩ ብዛት የተነሳ ህዝቡ መሪዎችን ለመብላት መዘጋጀቱን ይህም በቅርብ ቀን የሚታይ መሆኑን ገልጠዋል። አቶ ዳንኤል አክለውም በክልሉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አምነስቲ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂው የመለስ መንግስት ነው አለ
መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ማርች 12 ፣2012 ባወጣው መግለጫ የመለስ መንግስት በሲቪል ማህበረሰብ ህግ መሰረት ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዳይንቀሳቀሱ በማድረጉ ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚታየውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ይፋ ለማድረግ አልተቻለም። በዚህ ህግ የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ በጸጥታ ሀይሎች ዳፋውን እያየ መሆኑን ድርጅቱ ገልጧል። አብዛኞቹ የሰብአዊ መብት ...
Read More »በትግራይ ምንነቱ ባልታወቀና በሽታ ሰው እያለቀ ነው
መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል ምንነቱ ባልታወቀና መድሀኒት ሊገኝለት ባልቻለ በሽታ ሰው እያለቀ መሆኑን አቶ አስገደ ገብረሥላሴ አጋለጡ። የክልሉ ጤና ቢሮ በሽታውን ማወቅ አልተቻለም ይላል። የቀድሞው የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት)ታጋይና የአሁኑ የአረና ለትግራይ ፓርቲ አመራር አባል አቶ አስገደ እንዳሉት ከ10 ዓመት በፊት በመዳባይ ዘና ወረዳ በምትገኝ አንዲት አነስተኛ ቀበሌ ውስጥ ተከስቶ ለብዙ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ...
Read More »አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያ በርካታ ችግሮች ተደቅነውባታል አለ
መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የአለማቀፍ የገንዘብ ተቋሙ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ናዮኪ ሺኖሀራ ከአቶ መለስ እና ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ከተነጋገሩ በሁዋላ ባወጡት መግለጫ ፣ ኢትዮጵያ የገንዘብ ግሽበትን በመቆጣጠር፣ እየጨመረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት በማስታገስና ኢንቨስትመንትን በመሳብ በኩል ከፍተኛ ፈተናዎች ተደቅነውባታል። ምክትል ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስትመንት አመቺ የሆኑ ለውጦችን እንዲያካሂድና በቂ የሆነ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲኖር መስራት እንዳለበት ...
Read More »የአልሸባብ ሚሊሻዎች በኢትዮጵያ ጦር ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ሀሰት ነው አለ
መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የአልሸባብ ሚሊሻዎች ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ላይ በከፈቱት ጥቃት ከፍ ያለ ጉዳት እንዳደረሱ በዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን የተሰራጨውን ዜና ውሸት ነው ስትል ኢትዮጵያ አስተባበለች። አልሸባብ በበኩሉ የማረካቸውን የኢትዮጵያ ወታደሮች የድምፅ መረጃ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ በማስታወቅ፤ ኢትዮጵያ የደረሰባትን ኪሳራ ልታስተባብል እንደማትችል ገልጿል። አልሸባብ ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ ጦር ላይ መንገድ ዘግቶ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ፤ በርካታ ...
Read More »ከሰባ በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንዳለው አልሸባብ፤ ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ላይ ድንገት በከፈተው የማጥቃት እርምጃ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን ከአካባቢው የሚወጡ ሪፖርቶች ያመላክታሉ። እንደ ዜና አውታሩ ዘገባ፤የኢትዮጵያና ጥቂት የሶማሊያ ወታደሮች የማዕከላዊ ጌዲኦ አካል በሆነችው በዩኩሩት ባለፈው ማክሰኞ ንጋት ላይ በአልሸባብ ተዋጊዎች ተከበቡ። ከዚያም ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ውጊያ ተካሄደ። በሞቃዲሾ ሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለው፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች ባለፈው ...
Read More »ሙስሊሞች የኮሚቴውን ውሳኔ ካደመጡ በሁዋላ አለመረጋጋት እየታየ ነው
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በጁማ ጸሎት በአወልያ ከ400 ሺ ህዝብ ያላነሱ ሙስሊሞች ተገኝተው የኮሚቴውን ውሳኔ ካደመጡ በሁዋላ አለመረጋጋት እየታየ መሆኑ ተገለጠ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተለው ዘጋቢያችን እንደገለጠው በዛሬው እለት ሙስሊሙ የመረጣቸው ኮሚቴዎች እንደታሰሩ የሚያመለክቱ፣ ሙስሊሙ ተቃውሞውን እንዲያሰማ የሚጠይቁ መልእክቶች በሞባይል ስልክ ( ኤስ ኤም ኤስ) እና በበራሪ ወረቀቶች ሳይቀር ሲበተን አርፍዷል። ይሁን እንጅ ህዝበ ሙስሊሙ አመራሮቹ ያልታሰሩ ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን አባረረ
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ባለፉት 5 ቀናት በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በተመራው ግምገማ የመስተዳድሩ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሐይሌ ፍሰሐ፣ ምክትላቸው አቶ አበበ ዘልኡል፣ የመሬት አስተዳደር እና ግንባታ ሃለፊ ቃሲም ፈንቴእና ምክትላቸው ይርጋለም አለሙ፣ የከተማ ውሀና የመሬት ልማት ባንክ ሃላፊ አቶ ሳህለ ሰርሻ፣ የአዲስ አበባ የዲዛይንና ግንባታ ልማት ሃለፊ አቶ አበበ ከበደ ጃለታ ከስራ እንዲባረሩ ተደርጓል። ባለስልጣኖቹ የተባረሩት ...
Read More »ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በጠና ታመዋል
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በጠና ታመው ኮሪያ ሆስፒታል መግባታቸውን አዲስ አድማስ ዘገበ። ላለፉት 11 ዓመታት በኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄርነት የቆዩት መቶ አለቃ ግርማ፤ የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ከሥልጣን ለመውረድ የስድስት ወራት ዕድሜ ቀርቷቸዋል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን በመሰናበቻቸው ዋዜማ በጠና ታመው በኮሪያ ሆስፒታል የቅርብ እርዳታና ክትትል እየተደረገላቸው ነው። የሆስፒታሉ ምንጮች ለጋዜጣው እንደጠቆሙት፤ ፕሬዚዳንቱ ከትናንት በስቲያ በጠና ታመው ...
Read More »በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኖርዌይ መንግስት በስደተኞች ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ
መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኖርሜይ መንግስት በስደተኞች ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ በስዊዲን የኖርዌይ ኢምባሲ ፊት ለፊት ኢትዮጵያውያውያኑ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የኖርዌይ መንግስት የወሰደው እርምጃ ህገወጥ ነው ብለዋል። በተቃውሞው ሰልፍ ላይ በስቶክሆልም ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ደጋፊ የውጭ አገር ዜጎች ተገኝተዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate ...
Read More »