.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሴቶች ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬታማ አይሆንም ተባለ

መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግማሽ ህዝብ የሚሆኑትን ሴት እህቶቻችን ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬቱ ያማረ እንደማይሆን፣ ቢሆንም ራሱን ለጥፋት እንደሚያጋልጥ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።  አቶ ኦባንግ ይህን የተናገሩት፤  ሰሞኑን ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 3 ቀን  በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኢትዮጵያ ሴቶች ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ  ነው።  “የሴቶችን መብት በማስከበር ለሥልጣን ማጎናጸፍ” በሚል ርዕስ  ...

Read More »

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመድረኩ አባላት እና የመድረኩ አስተዳዳሪዎች የድጋፍ ዝግጅት ያደረጉት ብቸኛው የኢትዮጵያ ሳተላይት  ቴሌቪዥን ህብረተሰቡን ለማገልገል የሚያደርገውን ጥረት በማድነቅ ነው። በኢትዮጵያ የውይይት መድረክ ( ወይም ፓልቶክ) ከፍተኛ ተደማጭነትና ታዳሚ ያለው ኢካዲኤፍ ለኢሳት በተደጋጋሚ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል። መድረኩ በተከታታይ ዝግጅቶች ተመሳሳይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱንም ከአስተዳዳሪዎች ለመረዳት ተችሎአል። የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ  ከዚህ በፊት በተለያዩ ...

Read More »

ኤርትራ፤ ኢትዮጵያ ችግሯን በጦርነት እየሸፈነች ነው አለች

መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊ ት ወደ ኤርትራ ድንበር በመግባት በኤርትራ ወታደራዊ ተቋማትና ማሰልጠኛዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ማስታወቁን ተከትሎ ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት የጸብ አጫሪነት እርምጃ የድንበር ኮሚሽኑ የሰጠው ውሳኔ 10ኛ አመት እየተቃረበ መምጣቱን ተከትሎ የአለማቀፍን ትኩረት ለማስቀየር ታልሞ የተደረገ መሆኑን ኤርትራ ገልጣለች። የድንበር ኮሚሽኑ ባድመ ለኤርትራ ይገባል በማለት ከ10 አመታት በፊት ቢወስንም ኢትዮጵያ እስከዛሬ ለማስረከብ ...

Read More »

በአወልያ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል

መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ በሆነ የጸጥታ ቁጥጥር በተካሄደው ተቃውሞ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄያቸው መልስ እስከሚያገኝ ድረስ ተቃውሞዋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጠዋል። አንዳንድ የተመረጡ የኮሚቴው አባላት መንግስት ወደ አወልያ እንዳይሄዱ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ስለሰጣቸው በግቢው አለመታየታቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ የኮሚቴው አባላት ያልሆኑት ሌሎች ሙስሊሞች ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሙስሊሙን መሪዎች በደህንነት መኪኖች ሲከታተሉዋቸው መሰንበቱን  ተከትሎ የጸጥታ መደፍረስ ሊከሰት ይችላል ...

Read More »

የመለስ መንግስት ዜጎችን ለማፈናቀል ማቀዱን የሚያሳይ አዲስ ሰነድ ይፋ ሆነ

መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የህዝቅተኛ የኦሞ ሸለቆ አካባቢ ነዋሪዎችን ከቦታቸው በማንሳት በቦታው ላይ የሸንኮራ ገዳ ተክል ለመትከል መታቀዱን በድብቅ የወጣው ሪፖርት ያመለክታል። ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል በደረሰው መረጃ የሙርሲ፣ የቦዲና የኩዌጎ ነዋሪዎችን በቦዲ ለማስፈር ዘግጅቶች እየተካሄዱ ነው። በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተካሄ መሆኑን ተገልጧል። አንድ የሙርሲ ተወላጅ ” መንግስት መሬቴን ስለወሰደው ሞትን እየተጠባበኩ ነው። ” ብሎአል። ሌላ ...

Read More »

የአለም ደቻሳ ጉዳይ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያስቆጣ ነው

መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በሊባኖሳዊው ጎረምሳ ከተደበደበች በሁዋላ እራሱን ያጠፋቸው አለም ደቻሳ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያስቆጣ ነው በአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ሰዎች እንደገለጡት ድርጊቱ ኢትዮጵያኖች ያሉበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳይ ነው። አለም ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት መደብደቡዋ ፣ ጉዳዩን አሳዛኝ ማድረጉን የገለጡት ነዋሪዎች፣ የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት በውጭ በሚገኙ ኢንባሲዎቹ አማካኝነት ካላረጋጋጠ ኢምባሲ መክፈት ለምን እንዳስፈለገም ጠይቀዋል። ...

Read More »

ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጥቃት መሰንዘሩዋን አስታወቀች

መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣው መግለጫ የኤርትራ መንግሥትና ተላላኪዎቹን የጥፋት ተልዕኮ ማዕከላትን ዛሬ ማለዳ ላይ አውድሟል ብሎአል። የሚኒስቴሩ የኢንዶክትሬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ማዕከል ኃላፊ ኮሎኔል ገብረ ኪዳን ገብረ ማርያም  ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ባሉት ራሚድ፣ገላሃቤና ጌምቤ በተባሉ ሥፍራዎች ተሰባስቦ የነበረውን ኃይል ሙሉ በሙሉ አውድሟል ብሎአል። ሠራዊቱ የኤርትራ መንግሥትና ተላላኪዎቹን የጥፋት ተልዕኮ ለማክሸፍ ተመሳሳይ ድርጊቶችን ለማድረስ ከሚያደርገው ...

Read More »

በጋምቤላ የተፈጸመው በመንግስት ሀይሎች ሳይሆን አይቀርም ተባለ

መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ባለፈው ሰኞ በተፈጸመው ጥቃት ከ30 በላይ በብዛት የጋምቤላ ኮሌጅ ተማሪዎች የሆኑትን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተጠልፎ፣ 19 ሰዎች ከተገደሉና 8 ሰዎች ደግሞ ከቆሰሉ በሁዋላ ድርጊቱን የፈጸሙትን ሰዎች ለማጣራት የኢሳት የጋምቤላ ዘጋቢ ላይ ታች ሲል ቆይቷል። ዘጋቢያችን ባደረሰን መረጃ ለጥቃቱ ምናልባትም የክልሉ ባለስልጣናት ወይም የፌደራል መንግስቱ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም። ትናንት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ...

Read More »

አንድ ኢትዮጵያዊ በኡጋንዳ ታርዶ ተገኘ

መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በንግድ አማካሪነት ይሰረ የነበረው እድሜው ከ55 እስከ 60 የሚገመተው አቶ ወልዩ ሀሰን ጣሄር ባለፈው ቅዳሜ አንገቱ በገጀራ ተቆርጦ ትናንት ተገኝቷል። አስከሬኑ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን፣ ከግድያው ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ አንዲት ሴት መያዙዋን የዩጋንዳ የኢትዮጵያውያን ኮሚቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘለቀ ጀበሮ ለኢሳት ተናግረዋል። የድርጅታቸው ሾፌርና ዘበኛው መጥፋታቸውንም አቶ ዘለቀ አክለው ተናግረዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the ...

Read More »

በየመን የታገቱ ከ3 ሺ በላይ ሴቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ተደፈሩ

መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በሃርደሀ የመን የታገቱት ከ3 ሺ በላይ ሴቶች በተደጋጋሚ ጊዜ እንደተደፈሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር አስታወቀ ኢትዮጵያውያኑ ሀርዳህ ከተማ ውስጥ ሻርቂያ በምትባል መንደር ለረጅም ጊዜ ታግተው ቆይተዋል።  በርካቶቹ የውስጥ ሱሪ ብቻ ለብሰው መገኘታቸውን ኮሚሽኑ ገልጧል። ድርጊቱን ያጋለጡት ሁለት ሰዎች በአጥር ዘልለው ለማምለጥ በመቻላቸው ነው። ሀርዳህ ውስጥ የወንጀልምርመራ ሰራተኛ የሆኑት አሊ አብራሂም ” ለ15 ...

Read More »