.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢትዮጵያ ውስጥ በሁለት እስር ቤቶች ውስጥ ብቻ 401 የፖለቲካ እስረኞች እንደሚገኙ ተገለጸ

መጋቢት ፳፮ (ሃይ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በፖለቲካ አመለካከቱ የታሰረ አንድም ሰው የለም ቢልም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ  በሁለት እስር ቤቶች ውስጥ ብቻ 401 የፖለቲካ እስረኞች እንደሚገኙ ተገለጸ። የተጠቀሰው የፖለቲካ እስረኞች አሀዝ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት የታሠሩትን ብቻ እንጂ፤ከዚያ በፊት ያለውን እንደማያካትትም ተመልክቷል። ምንጮቹን በመጥቀስ ፍኖተ ነፃነት  እንደዘገበው፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፖለቲካ አመለካከታቸው ሳቢያ የሀሰት ክስ የተመሰረተባቸው  401 እስረኞች የሚገኙት፤በቃሊቱና ...

Read More »

የሱማሌ ክልል ሦስቱ ርዕሳነ- መስተዳድሮች ከሥልጣናቸው ተሻሩ

መጋቢት ፳፮ (ሃይ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሱማሌ ክልል ሦስቱ ርዕሳነ- መስተዳድሮች ከሥልጣናቸው ተሻሩ። የሁለቱ ያለመከሰስ መብት ተነስቷል። በጅጅጋ ከተማ ከትናትንት በስቲያ  በተጀመረው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አራተኛ መደበኛ ጉባዔ ፤ሦስቱም የክልሉ ምክትል ርዕሳነ- መስተዳደሮች ከሥልጣናቸው ተሻሩ፡፡ ቀደም ሲልም ለአንድ ክልል ሦስት ሰዎች  ከተሰጣቸው  የቢሮ ሃላፊነት ባሻገር በምክትል ፕሬዚዳንትነት  ጭምር እንዲሾሙ መደረጋቸው ብዙዎችን ማስገረሙ ይታወሳል። የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ ...

Read More »

ሚድሮክ ወርቅ በጉጂና በቦረና ዞኖች ነዋሪዎችን ለማፈናቀል ማቀዱ ተቃውሞ አስነሳ

መጋቢት ፳፭ (ሃይ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሻኪሶ ወረዳ በሬጂ ቀበሌ፣ በሰባ ቦሩ ወረዳ በ ቡሪ ኢጄርሳ ቀበሌ እንዲሁም በቦረና ዞን  በመልካ ሶዳ ወረዳ ሀሎ መጣዳ ቀበሌ ስር የሚገኙ ኤቢቻ፣ ሎቶሪ፣ ኦኮቴ፣ ኦዳ ሀንቃሪ ፣  ደዳቡቱ እና አዩ ቦዳ ቀበሌዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች   የካሳ ክፍያ እና  የመስፈሪያ ቦታ  ሳይሰጣቸው አካባቢውን ለሚድሮክ ኢትዮጵያ አስረክበው እንዲወጡ በመታዘዛቸው የአካባቢው ነዋሪዎች “አካባቢውን ለቀን አንወጣም ...

Read More »

በዱባይ አንድ ኢትዮጵያዊት በአሰሪዋ ተገድላ በጊቢው ውስጥ ተቀብራለች

መጋቢት ፳፭ (ሃይ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዱባይ አንድ ኢትዮጵያዊት በአሰሪዋ ተገድላ በጊቢው ውስጥ ተቀብራለች የኢትዮጵያ ቆንስላ ዜናው እንዳይወጣ እያባበለ ነበር ተብሎአል:: ታሪኩ የተፈጸመው የዛሬ ሁለት ወር ገዳማ ነው ዱባይ ውስጥ ነው። በአንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ 3 ኢትዮጵያውያውያን እና ሁለት የፊሊፒንስ ዜጋ ተቀጥረው ሲሰሩ ከቆዩ በሁዋላ አንደኛዋ የፈሊፒንስ ዜጋና ኢትዮጵያዊቷ ቤቱን ለቀው ጠፍተው ሲሄዱ ሁለት አትዮጵያውያንና አንድ የፊሊፒንስ ዜጋ ...

Read More »

መድረክ የፖለቲካ ተጽእኖው በረታብኝ አለ

መጋቢት ፳፭ (ሃይ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ  ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አዳራሽ ቅዳሜ መጋቢት 22 ቀን 2004 ዓም ስብሰባ ቢጠራም፣ አዳራሹን ያከራየው ድርጅት በመጨረሻ አዳራሹን እንደማያከራይ በመግለጡ በኑሮ ውድነቱና በአዲሱ የሊዝ አዋጅ ዙሪያ ሊካሄድ የነበረውን ስብሰባ ለመሰረዝ ተገዷል። የመድረክ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ መድረክ ስብሰባ ለማካሄድ ከመንግስት ፈቃድ ማግኘቱን እና አስፈላጊውን ...

Read More »

የአፋር ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተፋጧል ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ታስረዋል

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመለስ መንግስት በአፋር አካባ ቢ የጀመረው የስኳር ልማት ፕሮጀክት ከተወላጆች ከፍተኛ ተቃውሞ ስለገጠመው ልዩ ሀይሉን እና የመከላከያ ሰራዊት አባላቱን በአካባቢው አሰማርቶ ተወላጆችን በማሰር፣ በመድብደብና በማሰቃየት ላይ ነው። የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ሳይፈቅዱ አካባቢውን ማረስ መጀመሩን የአካባቢው ሰዎች መቃወም በመጀመራቸው ሁለት ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ 8 ሴቶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ...

Read More »

በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊቱ አባለት በነዋሪዎች ላይ አሰቃቂ እርምጃ እየወሰዱ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በጋምቤላ በቅርቡ 19 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊቱ ገዳዮችን ለማደን ከፍተኛ ዘመቻ ሲያካሂድ ቢቆይም እስካሁን ድረስ አልተሳካለትም። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በዘመቻው አንድም ሽፍታ ያልተያዘ በመሆኑ ሰራዊቱ የአካባቢውን ነዋሪዎች ሽፍቶቹን አውጡ በማለት እያሰቃዩ ነው። የመከላከያ ሰራዊት በጋምቤላ ጸጥታ የማስከበሩን ሀላፊነት ከክልሉ መንግስት ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ በህዝቡ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ከፍተኛ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸው ተሰማ

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን በሚሰጠው የትምህርት አይነት ከዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ጋር ሲወዛገቡ የቆዩት ከ1ኛ እስከ 5ኛ አመት የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርት ያቆሙት አሁን ባለው የትምህርት አሰጣጥ ተምረንም ኮብል ድንጋይ ከማንጠፍ ሌላ የሚጠብቀን የለንም በሚል ነው። ዝርዝር ሁኔታውን ለማጣራት ኢሳት ተደጋጋሚ ሙከራ በማድረግ ላይ ነው። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate ...

Read More »

በእግር ኳስ ግጥሚያው አምባሳደሮቹ አለመጫዎታቸው እያነጋገረ ነው

መጋቢት ፳፬ (ሃይ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዳሴውን ግድብ ግንባታ አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መመቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የውጪ አገር ዲፕሎማቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት ጋር የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚያደርጉ ኢቲቪና ሌሎች የመንግስት ብዙሀን መገናኛ ሲዘግቡ ቢሰነብቱም፤አምባሳደሮቹ አለመጫዎታቸው እያነጋገረ ነው። ኢቲቪ ከቀናት በፊት ፤የመንግስት ባለሥልጣናት ከውጪ አምባሳደሮች ጋር የ እግር ኳስ ጨዋታ እንደሚያካሂዱ በማሣወቅና   የአምባሰደሮቹን ቡድን ለመግጠም ባለሥልጣናቱ  ስላደረጉት ዝግጁነት ...

Read More »

ብአዴን ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉትን የአማራ ተወላጆች ካምፕ ውስጥ እንዲገቡ አደረገ

መጋቢት ፳፪ (ሃይ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት ጉዳይ አስፈጻሚ እየተባለ ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወይም ብአዴን፣ ከደቡብ ክልል በቤንች ማጅ ዞን በጉራ ፋርዳ ወረዳ በግፍ ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የመጡ ወደ 200 የሚጠጉ የአማራ ተወላጆችን ተጠልለው ይገኙበት ከነበረው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲወጡ በማድረግ በሁለት ማጎሪያ ካምፖች እንዲቀመጡ አድርጓል። ተፈናቃዮቹ ወደ አዲስ ...

Read More »