ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት የፌዴራል ዐቃቤ-ሕግ በእነአንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል ከከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላትና ጋዜጠኞች ውስጥ በሀገር ውስጥ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን የሚከላከሉት ስምንት ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ለውሳኔ ዛሬ ጠዋት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ቢቀርቡም ፍርድ ቤቱ በተለዋጭ ቀጠሮ ለሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ሰጥቶ አሰናብቷቸዋል፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተቃውሞ ለአደረጉ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አረጋገጡ
ግንቦት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትናንት ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን ፆማቸውን በመዋል ተቃውሞ በማሰማት ላይ ላሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አረጋገጡ። ተማሪዎቹ፤ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ሙስሊም ሀይማኖታዊ መብቶቹን ለማስከበር እያደረገ ያለው ትግል የነሱም ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ፤ መብታቸው እስኪከበር ድረስ ከሙስሊም ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን እንደሚሰለፉ ገልጠዋል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ከዚህም ባሻገር መንግስት ያሰማራቸው ታጣቂዎች በአርሲ-አሰሳ መስጅድ ሀይማኖታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ...
Read More »ኢህአዴግ መጅሊስ እንዲፈርስ ቢወሰንም ሙስሊሞቹ ግን ትግሉ ይቀጥላል ይላሉ
ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ መንግሥት በሙስሊሙ ማህበረሰብ በተፈጠረበት ጫና ሃይማኖቱን በበላይነት ሲመራ የነበረውንና በመንግሥት የሚደገፈውን መጅሊስ እንዲፈርስ ባለፈው ሃሙስ ውሳኔ ማሳለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በመጅሊስ የተጠሩ የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰቦች ከፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን ከሰኔ መጀመሪያ እስከ ሐምሌ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ አዲስ መጅሊስ በምርጫ ይቋቋማል ...
Read More »አንድነት ፓርቲ መንግስት ያወጣውን የቅድመ ምርመራ ህግ እንዲያነሳ ጠየቀ
ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ዛሬ ” ከመቃብር ተመልሶ የመጣውን የሳንሱር መቀስ እንቃወመዋለን ወደ መቃብሩ እንዲመለስም እንታገለዋለን ” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ብርሀንና ሰላም ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን በማስመሰል ካዘጋጀው ውል ጀርባ ሌላ እጅ እንዳለ ይጠረጠራል በማለት ከገለጠ በሁዋላ፣ አዋጁ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ተብሎ በሚታሰበው ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ላይ የቅድመ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ ነው ...
Read More »የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላት በከፍተኛ ሙስና ተዘፍቀዋል
ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የሚገኙ 32 የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ከግዥና ንብረት አስተዳደር ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ሙስናና ብልሹ አሠራር ውስጥ ተዘፍቀው እንደሚገኙ አንድ ጥናት አረጋገጠ፡፡ የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሸን በተቋማቱ ላይ ያካሄደውን ጥናት በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገበት ወቅት የሰለጠነ የሰው ኃይል በብቃት የማፍራት ኃላፊነት የተጣለባቸው እነዚሁ ተቋማት ለመማር ማስተማር ሒደቱ ወሳኝ የሆኑ ግዥዎችን ሕግና ...
Read More »የጋምቤላ መንግስት የፖሊስና መካለከያ ሰራዊት ቁጥር እንዲጨመር ጥሪ አቀረበ
ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የጋምቤላ ዘጋቢ ኡጁሉ ኦሞድ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ኦሞድ ኦቦንግ ለአቶ መለስ ዜናዊ፣ ለኢህአዴግ ጽህፈት ቤት፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ለፌደራል ፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት በላኩት ደብዳቤ፣ የጋምቤላ የጸጥታ ችግር ከክልሉ መንግስት አቅም በላይ በመሆኑ ተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲላክላቸው ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንቱ በደብዳቤያቸው በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ...
Read More »ህዝቡ በዋጋ ንረቱ መማረሩን ሲቀጥል ስታትስቲክስ ቢሮ ግሽበቱ 2 በመቶ መቀነሱን ገለጠ
ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በያዝነው ወር ሀሉም ነገር መጨመሩን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል። በአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ጤፍ እስከ 1300 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋም የጤፍ ዋጋ መጨመር እንጅ መቀነስ አላሳየም። የበቆሎ እና ሌሎችም ለምግብ ፍጆታነት የሚውሉ ሸቀጦች ተነጻጻሪ ጭማሪ አሳይተዋል። የዘይት ዋጋ ባለበት ቢቆይም፣ ስኳር እና ሻይ ቅጠል ጭማሪ አሳይተዋል። ባለፉት ...
Read More »ኢትዮ ቴሌኮም ድብቅ መሳሪያ ተክለው ከውጪ አገር የሚደውሉ የስልክ ጥሪዎች እየተፈፀመ ነው አለ
ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ወይም ኩባንያዎች ድብቅ መሳሪያ ተክለው ከውጪ አገር የሚደውሉ የስልክ ጥሪዎችን በራሳቸው መሣርያዎች በመቀበልና ለደንበኞች በማስተላለፍ በሕግ የተከለከለ የስልክ አገልግሎት እየሰጡ ነው ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አጋለጠ። በ1995 ዓመተ ምህረት ሟቹ ኢያሱ በርሄ እና ሌሎች ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ ባስገቧቸው የቪሳት መሳሪያዎች ተመሳሳይ አገልግሎት ሢሰጡ ተይዘው ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል። ይሁንና ...
Read More »ምርጫ ቦርድ ከሰማያዊ ፓርቲ የህጋዊነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ ሰማያዊ ፓርቲንና ፕሬሱን አስጠነቀቀ
ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲ በሚል ሰያሜ ሕጋዊ ሰውነት እንዳገኘ አድርጎ የሚጠራው አካል ሕጋዊ ሰውነት አለማግኘቱን በመግለጽ ወሬውን የሚዘግቡ ፕሬሶችንና ፓርቲውን ከአድራጎታቸው እንዲቆጠቡ ሲል አሰጠነቀቀ፡፡ በቦርዱ ጽ/ቤት ምክትል ዋና ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ አሰፋ ፊርማ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ የተሰራጨው መግለጫ እንደሚያትተው ሰማያዊ ፓርቲ ቦርዱ እንዲያሟላ የጠየቀውን ሰነዶች ያላሟላ በመሆኑ ሕጋዊ ሰውነት አልተሰጠውም፡፡በመሆኑም ...
Read More »የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ከዚህ በላይ ልንታገሰው አንችልም ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ሚያዚያ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ጉዳዮች ሚ/ር የሆኑት ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም ሙስሊሙ ኀብረተሰብ በሰላም እንዳይጸልይ ያውካሉ ያሏቸውን ጸረ ሠላም ኃይሎች መንግስት ሊታገሰቻው በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የገለጡት፡፡ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የመ/ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በአሁኑ ግዜ በየመስጊዱ ህዝበ ሙስሊም የአርብ ጸሎትን በሰላም እንዳይጸልይ በማወክ በግልጽና በህቡዕ የሚንቀሳቀሱና ሰላምን ፣ልማትን ...
Read More »