.የኢሳት አማርኛ ዜና

አልሸባብ ፕሬዚዳንት ኦባማንና ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩዋን ለመግደል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጡ ሁሉ እንደሚከፍል አስታወቀ

ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አልሸባብ ፕሬዚዳንት ኦባማንና ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩዋን ለመግደል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጡ ሁሉ ገንዘብ እንደሚከፍል አስታወቀ የሶማሊያ ታጣቂ ሀይል ይህን መልስ የሰጠው የባራክ ኦባማ አስተዳዳር የአልሸባብ መሪዎች ያሉበትን ለጠቆመ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጥ ማስታወቁን ተከትሎ ነው። የአልሸባብ የቆዩ መሪ የሆኑት ሼክ ሾንጎሌ እንደተናገሩት ፕሬዚዳንት ኦባን ለመግደል የሚያስችል በቂ መረጃ ለሚያመጣ ሰው 10 ግመሎችን ይሸልማሉ፤ በአንጻሩ ሂላር ...

Read More »

በዋልድባ ገዳም አካባቢ ማይጋባ በሚባል ቦታ ላይ በፌደራል ፖሊስና እና በአርሶ አደሩ መካከል በተነሳ ግጭት 15 ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ግጭቱ የተነሳው ግንቦት25 ሲሆን፣ የፖሊስ አባላቱ የአካባቢው አርሶአደሮች ቤቶቻቸውን እንዲያፈርሱ ሲጠይቁ አርሶአደሮች ለማፍረስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በተነሳ ግጭት ነው ፖሊሶችና አርሶአደሮች የተገደሉት። በተመሳሳይ ዜና ደግሞ በዋልድባ አካባቢ በምትገኘዋ የዛሬማ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በትናንትናው እለት በርካታ መኪኖችን አግተው ውለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከወታቶች ጋር በፈጠሩት ግጭት በርካታ ወጣቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ60 ...

Read More »

ሰኔ 1 ዛሬ በተለያዩ አካባቢዎች እየታሰበ ነው

ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምርጫ 97 የመለስ መንግስት የህዝብ ድምጽ ማጭበርበሩን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን በአዲስ አበባ እና በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እየዘከሩት ነው። ከመኢአድ የተለዩት እና በዶ/ር ታዲዮስ የሚመራው መኢአድ አባላት በዛሬው እለት በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸውን በመያዝ እለቱን አስበው ውለዋል። 22 አካባቢ ከሚገኘው የአቶ ተስፋ ድረቤ ቤት በርካታ ወጣቶች በተገኙበት ቀኑን በግጥም እና በተለያ  ...

Read More »

የጣት አሻራ መረጃን ለደህንነት ተግባር ለመጠቀም ታቅዷል

ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥርን በጣት አሻራ ለማስደገፍ ባለፉት ሶስት ዓመታት እየሰበሰበ ያለውን በፎቶግራፍ የተደገፈ የአሻራ መረጃ ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለአገሪቱ ደህንነት ተቋም ሥራ ለማዋል ዕቅድ መኖሩን አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገለጹ፡፡ ባለሥልጣኑ በሐምሌ ወር 2001 ዓ.ም የጣት አሻራ መሰብሰብ ሲጀምር ታሳቢ አድርጎ የነበረው የታክስ ሥርዓቱን ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ በቅርቡ የነዳጅ ሀብት ባለቤት እንደምትሆን መናገራቸው ጠንከር ያለ ትችት አስከተለ

ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የ አለም ኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በቅርቡ የነዳጅ ሀብት ባለቤት እንደምትሆን መናገራቸው ጠንከር ያለ ትችት አስከተለ። የማዕድን ሚኒስትሯ በበኩላቸው የነዳጅ ዘይት ግኝት ሊረጋገጥ ሚችለው ነዳጁ ተቆፍሮ ሲወጣ ብቻ ነው በማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩን  የችኮላ ንግግር ውድቅ አድርገውታል። “ከነዳጅ ዘይት ግኝቱ በፊት ወሬው ምነው ቀደመ?” በሚል ርዕስ  ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ብራሰልስ ገቡ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዛሬ በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራሰል የተገኙት በህክምና ቀጠሮዋቸው መሰረት ነው። በአእምሮ እጢ በሽታ እንደተጠቁ የሚነገርላቸው አቶ መለስ፣  ብራሰልስ የገቡት  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑትን አቶ ብርሀነ ገብረክርስቶስን አስከትለው መሆኑን ከኢምባሲ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አምባሳደር ብርሀነ ከአቶ መለስ ጋር የመምጣታቸው ምክንያት ቀደም ሲል ለ10 አመታት ብራሰልስ በነበሩበት ወቅት የአቶ መለስን ህክምና ...

Read More »

በአፋር የተጀመረው ግጭት ቀጥሎ 8 ሰዎች ተገደሉ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው እለት የኢሳ ተወላጅ የሆኑ ልዩ  ሀይል የሚባሉት ታጣቂዎች 8 የአፋር ከብት አርቢዎችን  ገድለዋል። የአካባቢው ህዝብም በስጋትላይ መሆኑ ታውቋል ። የአፋር ህዝብ መሬቱ ለሸንኮራ አገዳ ተክል ይወሰደብኛል ብሎ እየሰጋ ባለበት ጊዜ  ጥቃት መፈጸሙ ችግራቸውን ይበልጥ እንዳወሳሰበባቸው ተወላጆች ይናገራሉ።፣ አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአካባቢው ተወላጅ እንደተናገሩት በዛሬው እለት በ7 ላንድ ክሩዘር መኪና የመጡ የኢሳ ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግሥት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ምትክ የሚመረጠው አዲሱ መጅሊስ በቀበሌና በወረዳ በካድሬዎች ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነው ተባለ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዑላማዎች ምክር ቤት በበላይነት ይመራዋል በተባለው የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌና በወረዳ በመንግሥት መዋቅር የሚካሄድ ሲሆን የፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት በሚመድበው ቀጥተኛ በጀት ደግሞ ከሰኔ 13 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2004 ዓ.ም የክልሎች የእስልምና ምክር ቤት (መጅሊስ) ይመረጣል።   ሰኔ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ደግሞ የአዲስ አበባ እስልምና ምክር ቤት ምርጫ ይካሄዳል የሚል መርሃ- ግብር በመንግሥት በኩል ...

Read More »

ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ይግባኝ ጠየቀች

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥት አሸባሪ ተብላ 14 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደባትና  33 ሺህ ብር የተቀጣችው ጋዜጠኛና መምህርት ርዮት ዓለሙ ከመንግሥት በኩል በተዘዋዋሪ የቀረበላትን የይቅርታ ጥያቄ ችላ ትናንት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቀረበች፡፡ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበችው አቤቱታ ላይ ጋዜጠኛ ርዮት ምንም ዓይነት ወንጀል እንዳልሰራች ገልጣለች። ይልቁኑም መንግሥት በእርሷ ላይ ወንጀል መፈጸሙን፣ ...

Read More »

ለልማት የሄዱ ዲያስፖራዎች ፦”የመንግስት ያለህ!”እያሉ ነው

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “የመንግስትን የልማት ጥሪ አምነን ወደ አገራችን  ከገባን በሁዋላ  በሙስና እየተንገላታንና እየተሰቃየን ነው” ሲሉ  ለሪል ስቴት ግንባታ   ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑ  ዲያስፖራዎች  እሮሮ እያሰሙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ  ዲያስፖራው ወደ አገሩ ገብቶ በኢንቨስትመንት አስንዲሳተፍ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ሰምተን ነው ለዓመታት በምቾት ስንኖርባት አሜሪካ ለልማት ወደ አገራችን ያቀናነው ይላሉ-የ ጂ. ኤም.ኤ.ኤስ ሪል ስቴት አክስዮን ...

Read More »