.የኢሳት አማርኛ ዜና

ግራ የተጋባው ፓርላማ ነገ ለልዩ ስብሰባ ተጠራ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት የመዝጊያው ጊዜ እስከዛሬ ድረስ ባልተለመደ ሁኔታ የተራዘመው ፓርላማ ፣ ነገ ረቡእ ለልዩ ስብሰባ ተጠርቷል። በነገው ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ይገኙ እንደሆን ለምንጫችን ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ፣ “እስካሁን ድረስ ይገኛሉ የሚል ፍንጭ አለመሰማቱን፣ ይሁን እንጅ ይገኛሉ ብለው እንደማያስቡ” ተናግረዋል። በፓርላማው አሰራር መሰረት አቶ መለስ በተገኙበት የሚቀጥለው አመት በጀት ለፓርላማው ተልኮ ...

Read More »

የቴልኮም አዋጅ ነገ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነገው ልዩ የፓርላማ ስብሰባ ላይ አወዛጋቢው የቴልኮም አዋጅ እንደሚጸድቅ ለማወቅ ተችሎአል። በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሳይቀር ከፍተኛ ውግዘት የደረሰበት አዲሱ የቴልኮም አዋጅ እንዲጸድቅ የሚደረገው ምንም አይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት ነው። ስካይፕ እና ሌሎች በኢንተርኔት የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎችን ማስተናገድ በወንጀል የሚአስከስሰውና እስከ አስር አመትና እስከ 100 ሺ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ከጸደቀ፣ የመለስ መንግስት ማንኛውንም ዘመናዊ ...

Read More »

የህዝበ-ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆቴላቸው በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኮምቦልቻ ከተማ በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ደማቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ተካፍለዉ የነበሩት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሼህ መከተ ሞሄ በፖሊስ ታፍነዉ መታሰራቸዉን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘግቧል። ሼህ መኸተ ሞሄ የታሰሩት ፕሮግራሙን ጨርሰዉ ወደ ማረፊያ ሆቴላቸዉ ከገቡ ቡሁዋላ በበርካታ ፖሊሶች ታፍነው ነው። ከሸህ መከተ በተጨማሪ በኮምቦልቻ ፕሮግራም ላይ ከተካፈሉት መካከል፤  ...

Read More »

የኦሮሞ ነጸናት ግንባር በቶሮንቶ የተሳካ ስብሰባ አደረገ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብርጋዲየር ጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው የአሮሞ ነጸናት ግንባር ባለፈው ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጁላይ 6 ቀን 2012 በቶሮንቶ ካናዳ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አድረገ። በዚህ በቶሮንቶ አካባቢ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት የግማሽ ቀን ስብሰባ ላይ፤ የድርጅቱ የበላይ አመራር አካላት፡ ማለትም ብርጋዲየር ጄነራል ሀይሉ ጎንፋ ከአስመራ በስልክ፡ ዶ/ር ኑሮ ደደፎና የድርጅቱ ቃል አቀባይ ...

Read More »

እስራኤል የመጨረሻዎቹን ቤተ-እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ልታጓጉዝ ነው

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእስራኤል መንግስት 2 ሺህ 200 ቤተ እስራኤላውያንን እ.ኤ.አ እስከ ማርች 2014 ድረስ ከኢትዮጵያ  ለማንሳት እንዳቀደ አስታወቀ። እነኚሁ ከኢትዮጵያ የሚጓጓዙት ቤተ እስራኤላውያን  የመጨረሻዎቹ እንደሆኑ የገለፀው የእስራኤል ካቢኔ፣ የሚያስፈልጋቸውን መጠለያና ሌላም ነገር ለማሟላት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የመደበ ሲሆን፣ በየወሩ 250 ቤተ እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ለማምጣት እንዳቀደ ገልጿል ። በተለምዶ “ፈላሻ-ሙራ” በመባል የሚታወቁት እነኚሁ ኢትዮጵያዊያን ይሁዲዎች፣ ...

Read More »

አዲስ አበባ በነዳጅ እጥረት ተጨናነቀች

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ በከተማ ውስጥ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች ስራቸውን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አቁመዋል። በዚህም የተነሳ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ የከተማዋ ትራፊክ ከወትሮው በባሰ ተጨናንቋል። አብዛኞቹ ታክሲዎች በነዳጅ እጥረት ስራቸውን አቋርጠዋል። የችግሩ መንስኤ የአቅርቦት ይሁን የስርጭት አልታወቀም፣ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ነዳጅ ከሱዳን ማስገባት ካቆመችበት ጊዜ ጀምሮ የነዳጅ አቅርቦቱ ችግር እየገጠመው ...

Read More »

ሚኒስትሩ ፤ በቴሌ ሠራተኞች ጠንካራ ተቃውሞ ገጠማቸው

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በአቶ  ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሰብሳቢነት የቴሌ ሠራተኞች በወቅቱ አገራዊ ጉዳይ ትናንት የጀመሩት ውይይት፤ በከፍተኛ ተቃውሞ እየቀጠለ እንደሚገኝ በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ዘጋቢ አመለከተ። እጅግ በርካታ የቴሌ ሠራተኞች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ ተሳታፊዎቹ  ከሰነዘሯቸው ተቃውሞዎች አንዱ፤ “የኮንዶሚኒየም ቤት ለደሀው ህዝብ እንደሚሠራ ስትናገሩ ከቆያችሁ በሁዋላ አሁን ሲጠናቀቅ ለሀብታሞችና ለተወሰኑ ብሔር አባሎች እየመረጣችሁ መስጠታችሁን ደርሰንበታል” ...

Read More »

የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሁንም ሚስጢር እንደሆነ ነው

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፓርላማ አባላት ግራ ተጋብተዋል፣ የተለያዩ ዝግጅቶች ተሰርዘዋል ፣ አንዳንድ መረጃዎች አቶ መለስ የወራት እድሜ እንዳላቸው ይጠቁማሉ ዝርዝሩ ኢሳት የፓርላማው መዝጊያ በአንድ ሳምንት እንደሚራዘም፣ ምክንያቱ ደግሞ የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ችግር እንደሆነ ከዘገበ በሁዋላ ፣ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ የመላው ኢትዮጵያውያን የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። በኢህአዴግ ዙሪያ የተሰባሰቡ አባላት ሳይቀሩ ግራ ተጋብተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ ...

Read More »

በደርግ ዘመነ መንግስት የነበረውን ጥበባዊ አሻራ ለማስቃኘት ታሰቦ የተከፈተው የሥዕል ኤግዚቢሸን በኢቲቪ እንዳይተላለፍ ታገደ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኤግዚቢሸኑ ዜና በኢቲቪ ከተዘገበ በኃላ እንዳይተላለፍ የታገደው ያለፈውን ሥርዓት የሚያንቆለጻጽስ ነው በሚል ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእስክንድር በጎሲያን ሥነ ጥበባት ኮሌጅ ሥር የሚገኘው ትምህርት ቤት ከ1967 እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ተማሪዎቹ ከሠሯቸው ልዩ ልዩ ሥዕሎች መካከል የተመረጣቸውን ሥዕሎች በሰኔ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለእይታ አብቅቷል፡፡ ዝግጅቱን አስመልክቶ የተዘጋጀው ካታሎግ በደርግ ዘመን የመጀመርያዎቹ ዓመታት የሥዕል ...

Read More »