Author Archives: Central

የመለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው የስልጣን ብወዛ መቀጠሉ ተዘገበ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህም መሰረት የአዳማ ከተማ ወይንም የናዝሪት ከተማ ከንቲባ ተነስተው በምትካቸው ሌላ ሰው መሾሙን ጉለሌ ፖስት የተባለው ድረ ገጽ ዘግቧል። እርምጃው የኦህዴድን መካከለኛ አመራር የመጥረግ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። ከሩብ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት አዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጉታ ላንቼሮ በድንገት ተነስተው በምትካቻቸው የኳሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ባካር ሻሊ እንደተኰቸውም ተመልክቷል። ባለፉት ሶስት ወራት በሙስናና ...

Read More »

ሆላንድ ካር በኪሳራ ለመዘጋት የበቃው በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ባለመገኘቱ መሆኑ ተነገረ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ መኪና በመገጣጠም የመጀመሪያው በመኋን ሲሰራ የቆየው ሆላንድ ካር በኪሳራ ለመዘጋት የበቃው በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ባለመገኘቱ መሆኑን የኩባንያውን ባለቤት የጠቀሱ ዘገባዎች አመልክተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ሳምንታዊው የቢዝነስ ጋዜጣ ካፒታል እንደዘገበው ለኩባንያው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። የኋላንድ ካር ባለድርሻና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ ለካፒታል ጋዜጣ ...

Read More »

በጉዲፈቻ ወደ ዴንማርክ የመጣች ህጻን ለከፍተኛ የስነ አዕምሮ ችግር መዳረጎን ከዴንማርክ የደረሰን ዘገባ አመለከተ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዛሬአራት አመት ከወላጅ እናቷና አባቷ ተረክበው ህጻኗን ከወንድሟ ጋር የወሰዳት የዴንማር ሰዎች ህጻኗ ለቤተሰቦቿ ያላትን ናፍቆት በየአጋጣሚው በመግለጽ እናቷ ጋር እየዲወስዷት በመጠየቅና ያልተለመደ በሀሪእያሳየች ደስታ በማጣቷ ለህጻናት ማሳደጊያ እንደሰጧት የኢሳት ምንጮች ከዴንማርክ ገልጣለች:: ከዴንማርክ የደረሰን ይሀው መረጃ እንደሚያመለክተው የህጻኗ ማእሾ ታሪክ በዴንማርክ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ቤተሰቦቿን ያነጋገረና የህጻኗን ወደ ሀገር ቤት ...

Read More »

በናዝሬት በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 4 ከንቲባዎች ተቀያየሩ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በተደረገ ግምገማ ላለፉት አራት ወራት በስልጣን ላይ ቆይተው የነበሩት የናዝሬት ወይም የአዳማ ዋና ከንቲባ እና ከእኝሁ ባለስልጣን ጋር ግንኙነት አላቻው የተባሉት የከተማዋ የኦህዴድ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርጓል። ገምጋሚዎቹ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት የነበሩ ሲሆን ግምገማውም በመልካም አስተዳዳር፣ በከተሞች እድገት፣ በኪራይ ሰብሳቢነትና በልማት ሰራዊት አደረጃጃት ላይ ያተኮረ ነበር። የከተማው ከንቲባ የነበሩት ...

Read More »

መንግስት በመላ አገሪቱ ሙስሊሞችን እያስገደደ ለተቃውሞ ሰልፍ ሊያስወጣ ነው

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙና መንግስት በሙስሊሙ ላይ በሚፈጽመው ኢሰብአዊ  ድርጊት የተነሳ ተቃውሞ ያስነሳሉ በተባሉ አካባቢዎች በሙሉ ፣ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ይደረጋሉ። አብዛኛው ህዝብ ተገዶ እንዲወጣ፣ የድርጅት አባላት ከፍተኛ ተልእኮ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሎአል። በዛሬው እለትም በቅርቡ የመንግስት ታጣቂዎች 4 ሰዎችን በገደሉበት ገርባ እና ደጋን መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተደርገዋል። የሰልፉ ...

Read More »

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ላለመውሰድ ወሰኑ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ2005 ዓ.ም ለሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማና የአካባቢ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፓርቲዎች ጋር ለመነጋገር በአዳማ ከተማ ምርጫ ቦርድ በጠራው ስብሰባ ፒቲሽን የተፈራረሙት የ34 ፓርቲዎች ህብረት፤ የምርጫ ችግሮች ሳይፈቱ  የመወዳደሪያ ምልክታቸውን እንደማይወስዱ በአንድ ድምጽ መወሰናቸው ታወቀ፡፡ 34ቱ ፓርቲዎች  የምርጫ ምልክት ላለመውሰድ የወሰኑት ፤ ህዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በመላው  ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ...

Read More »

የብር ዋጋ እየወደቀ ነው ተባለ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ በ17 በመቶ ጨምሮ በ16.35 ብር እንዲመነዘር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መወሰኑ ይፋ ከተደረገበት መስከረም 2003 ዓ.ም. ወዲህ ባሉት ሁለት ዓመታት፣ የብር ምንዛሪ አቅም እየቀነሰ ከ10 በመቶ በላይ ወርዷል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነው። በኅዳር 2004 ዓ.ም. የየዕለቱ የውጭ ምንዛሪ ዋጋን በሚያመለክተው መረጃ መሠረት የአንድ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 17 ብር ...

Read More »

ባለፉት 10 አመታት በአዲስ አበባ የተገነባው ከአጼ ሚኒሊክ ጀምሮ ከተገነባው ይበልጣል ሲሉ አቶ ኩማ ደመቅሳ ተናገሩ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከንቲባው ይህን የተናገሩት  በቅርቡ የአዲስ አበባ 125ኛ አመት ክብረ በአል ሲጠናቀቅ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ነው። አቶ ኩማ ከተማዋን የቆረቆሩትን እና በከተማዋ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉትን በሙሉ በማውገዝ የኢህአዴግን ስራ ለማሞካሸት ሞክረዋል። በነገሥታቱ ዘመን የከተማዋ የመሬት ይዞታ ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና ለጦር አበጋዞች ተከፋፍሎ አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪዎች ሲሰቃዩ እንደኖሩ፣ የከተማዋ ዕድገት ማስተር ፕላንን ያልተከተለ በመሆኑና በመኳንንቱና ...

Read More »

በኢትዮጵያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎዳና ተዳዳሪዎች አሉ

ህዳር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከተማ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ጎዳና ተዳዳሪዎች መኖራቸውን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ጥናት አመለከተ። የኢትዮጵያ መንግስት ማእከላዊ ስታትስቲክ መስሪያ ቤት ደግሞ በአዲስ አበባ ያሉት ጎዳና ተዳዳሪዎች 60 000 ብቻ ናቸው የሚል መረጃ አሰራጭቷል። የተባበሩት መንግስታት የአለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ እንዳመለከተው በኢትዩኦጵያ በአጠቃላይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎዳና ተዳዳሪዎች ...

Read More »

በአዲስ አበባ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰዋል

ህዳር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ መስተዳድር በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት ክፍለ ከተሞች ብቻ ያፈረሳቸው ቤቶች በሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን አዲስ አበባ ከተማ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘገበ ። ሳምንታዊው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አዲስ ፎርቹን እሁድ ዕለት እንደዘገበው በቦሌ ክፍለከተማና በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የፈረሱ ቤቶች 7ሺህ ደርሰዋል። መስተዳድሩ ከገበሬዎች በግዢ ወደ ነዋሪዎች የተላለፉት መሬቶች ሕጋዊ ማረጋገጫ የላቸውም ...

Read More »