Author Archives: Central

በጂዳ የብአዴን ዝግጅት ላይ የተገኙ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተባረሩ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 32ኛ አመት ለማክበር አርብ ምሽት በጅዳና በአካባቢዋ በተዘጋጀ ዝግጅት ለመሳተፍ የሄዱ በርካታ ነዋሪዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንና ስብሰባው በጊዜ መበተኑን ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ገልጿል። ዛሬ በተጠራው የብአዴን ዝግጅት ላይ የተቃውሞ ድምጻችን እናሰማለን በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወረቀት በህቡዕ የበተኑ ሲሆን፤ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ እንዳያካሂዱ በሚል ፍራቻ ጥሪ የተደረገላቸው አንዳንድ ...

Read More »

በአንዋር መስጊድ ዛሬም የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋቡ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እስላም ኢትዮጵያውያን በታላቁ የአንዋር መስገድ በመገኘት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እየተከተለ ያለውን ፖሊሲ አምርረው ተቃውመዋል። ምእመናኑ 27 ቁጥር የተጻፈበት ወረቀት በማውለብለብ ” አንቀጹ ይከበር፣ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፣ አሸባሪዎች አይደለንም” በማለት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ተሰምቷል። ምእመናኑ 27 ቁጥር በመያዝ ተቃውሞአቸውን ያስተጋቡት በህገመንግስቱ በአንቀጽ 27 ላይ የተደነነገገው የሀይማኖት እኩልነት መብት ይከበር በማለት ነው። ...

Read More »

በባህር ዳር ፍተሻው ተጠናክሯል ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው  ህዳር 29/ 2005 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የሚያከብረውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተከትሎ ወደ ባህር ዳር የሚገቡ ንፁሀን ዜጎችን በሁለቱም የተሽከርካሪ መግቢያዎች እና በአውሮፕላን የሚገቡትን በፍተሻ እያጨናነቀ፣ ነፃነታቸውን በእጅጉ እየገፈፈ እና ህዝቡን ከመንገዱ እያስተጓጎለ ይገኛል በማለት ነዋሪዎች ገልጸዋል። ግርማ አያሌው የተባለ ነጋዴ፣ ጌትነት ታየ የተባለ አርሶአደርና ውብሸት የተባለ ተማሪ ...

Read More »

በትግራይ ክልል ህወሀትን አትደግፉም የተባሉ ዳኞች እየታሰሩ ነው

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ የሚገኙ ዳኞች ለኢሳት እንደገለጹት በቅርቡ በክልሉ ከፍተኛ ግምገማ በመካሄድ ላይ ሲሆን አመለካከታቸው ከመለስ ራእይ ውጭ ነው የተባሉ ዳኞች ተይዘው ታስረዋል። ድምጻቸው እንዳይተላለፍ የጠየቁ ዳኞች ለኢሳት እንደገለጹት  በውቅሮ ከተማ ውስጥ በተደረገው ግምገማ 4 ዳኞች ታስረዋል። አቶ መለስ ከሞተ በሁዋላ ሁኔታው ተባብሶ መቀጠሉን የገለጡት ዳኞች፣ ለምን የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ዳኞች ድብደባ ሳይቀር ይደርስባቸዋል። ...

Read More »

በድልድይ መሰበር ምክንያት የወዳደቁ የታንክ ብረ የጫነ ተሽከርካሪ ገደል ውስጥ ገባ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቀድሞው መንግስት ጋር በተደረገው ጦርነት የወዳደቁ የታንክና ሌሎች ተሽከርካሪ ብረቶችን በማጓጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ያልፍበት የነበረው ድልድይ በመሰበሩ አንድ አርሶ አደር ሲሞት ሾፌሩና ረዳቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሰዎች ለሰዎች በተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በብዙ ሚሊየን ብር ተገንብቶ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ዘመናዊ ባለብረት ድልድይ፣  ከሚዳ ወረሞ ወረዳ መራኛ ከተማ ተነስቶ ወደ አዲስ ...

Read More »

በቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው ስብሰባ የሁለተኛ ቀን ሪፖርት

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን  አባቶች  መካከል  ትናንት  ጥቅምት  26/2005  በዳላስ  ቴክሳስ  የተጀመረው  ስብሰባ  ዛሬ ለሁለተኛ  ቀን  የቀጠለ ሲሆን  ፕሬዚዳንት  ግርማ  ወ/ጊዮርጊስ  አቡነ  መርቆርዮስ  ወደ  መንበራቸው  እንዲመለሱ  የፃፉት  ደብዳቤና  ደብዳቤውን በተመለከተ  ለቪኦኤ  የሰጡት  መግለጫ  ዐቢይ  መነጋገሪያ  ሆኖ  ወጥቶዋል። የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን  ምእመናን  አለም  አቀፍ  ማህበር  ለተደራዳሪዎቹ  አባቶች  በላከው  ግልፅ  ደብዳቤ ለቤተክርስቲያኒቱ  አንድነት  ሲሉ  በመቻቻልና  ሰጥቶ መቀበል  መረህ  መፍትሄ  እንዲያመጡ  ጥሪ  አቅርበዋል። የኢትዮጵያ  ፕሬዚዳንት  ግርማ ወ/ጊዮርጊስ  ማክሰኞ  ከትላንት በስቲ ሕዳር  25/2005 ለብፁዕ  አቡነ  መርቆርዮስ  በፃፉት  ደብዳቤ  ወደ መንበራቸው  እንዲመለሱ ጥሪ  አቅርበዋል፣  ፕሬዚዳንት  ግርማ  በፃፉት  በዚህ  ደብዳቤ  አዲስ  ፓትሪያርክ  እንዳይሾም  በሀገር  ሽማግሌዎችና በምእመናን  የሚደረገው  ጥረት  በርሳቸውም  በኩል  ተቀባይነት  እንዳለውም  አመልክተዋል።  ፕሬዚዳንቱ  መልእክታቸውን  ሲያጠቃልሉም የሚከተለውን  ጥሪ  አቅርበዋል። “ቅዱስነትዎ  ይህን  ሀሳብ  ተቀብለው  ልዩነትን  በማጠበብ  በቤተክርስቲያናችን  አንድነትና  ሰላም  እንዲሰፍን  በቅዱስነትዎ  የሚመራውን  ቅዱስ ሲኖዶስ  ይዘው  ወደ  አገርዎትና  ወደ  ቤተክርስቲያንዎ  አንዲገቡ  ይህን  ደብዳቤ  ፅፈናል”  በማለት  ከስማቸው  ጋር  ፊርማቸውን  አያይዘዋል። ፕሬዚዳንት  ግርማ  የህንን  ደብዳቤ  ለጠቅላይ  ሚኒስትሩ  ቢሮ ፣  ለውጭ ጉዳይ  ሚኒስትር፤  ለፌድራል  ጉዳዮች  ሚኒስትር፣  እንዲሁም  ለሀገር ውስጥ  ጉዳይ  ሚኒስትር  እንዲያውቁት  የላኩ  ሲሆን  በግልባጭ  በኢንጂነር  አርጋው  ጥሩነህ  ለሚመራው  የሽመግሌዎች  ቡድን  አድርሰዋል። ፕሬዚዳንት  ግርማ  ወ/ጊዮርጊስ  ይህ  ደብዳቤ  ከርሳቸው  የተፃፈ  መሆኑን  በትናንትናው  ዕለት  ለቮይስ  ኦፍ  አሜሪካ  የአማርኛው  አገልግሎት አረጋግጠዋል። በዚህ  ቃለ-ምልልስ  ብፁዕ  አቡነ  መርቆርዮስ  ከስልጣናቸው  ታግደው  መነሳታቸውን  ይህንንም  የቀድሞው  ጠ/ሚ/ር ታምራት  ላይኔ መመስከራቸውን  እንደተረዱ  አመልክተዋል። ፕሬዚዳንት  ግርማ  ወ/ጊዮርጊስ  ለቪኦኤ  እንደገና  በሰጡት  ቃለ-ምልልስ  ደብዳቤውን  ከስልጣናቸው  አልፈው  የፃፉት  በመሆኑ  እንደሳቡት ገልፀውል። ይህ  በእንዲህ  እንዳለም  በከፍተኛ  ጉጉት  በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ምዕመናን  የሚጠበቀው  በዳላስ  ቴክሳስ  የተጀመረው  ድርድር  ዛሬ  ለሁለተኛ ቀን  ቀጥሎዋል። ይህ  ድርደር  የተሳካ  እንዲሆን  የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን  ምዕመናን  ዐለምአቀፍ  ማህበር  የቦርድ  ሊቀመንበር  አቶ  ይስሐቅ ክፍሌ  የወጣው  ደብዳቤ  የመለያየቱ  ጊዜ  ያበቃ  ዘንድ  ጥሪ  አቅርቦዋል። “የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን  ምእመናን  በአንድ  ቅዱስ  ሲኖዶስ፣  በአንድ  ፓትሪያርክ  እና  በአንድ  እረኛ  የምንመራ  አንድ መንጋ  መሆን  እንችል  ዘንድ  ወጥነት  ያለው  ሰንሰለታዊ  መዋቅር  ባስቸክዋይ  ተጠንቶ  እንዲተገበርልን  ልመናችንን   እናቀርባለን”  ሲል የምዕመናት  አለም  አቀፍ  መህበር  ጥሪ  አቅርቦዋል።

Read More »

በሀና ማርያም አካባቢ የተፈናቀሉ ወገኖች መሰብሰብና ሁለት ሆነው መቆም አትችሉም መባላቸውን አስታወቁ

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደት  ሌላ  ሀገር  የምንሄድበት  ሁኔታ  ካለ  ይመቻችልን  ሲሉም  ጥያቄ  አቀረቡ።ቤታቸው  በመንግስት  ትእዛዝ  ፈርሶ  ከአደባባይ  ከሚገኙ  የንፋሰልክ  ላፍቶ  ክፍለ  ከተማ  ወረዳ  01  ነዋሪዎች  ጋር  ኢሳት  ባደረገው  ቃለ-ምልልስ  ነዋሪዎች  እንደገለፁት  ምን  ማድረግ  አለብን  ብለን  በችግሮቻችን  ላይ  ለመወያየት  ስለሞከርን  የመንግስት  ታጣቂዎች  የናንተ  ጥያቄ  ሌላ ነው  ሲሉ በትነውናል  ብለውናል። ለመንግስት  ባለስልጣናት  አቤት ለማለት  ባንዲራ  ይዘን  በወጣን  ጊዜ  ባንዲራውን  በመንጠቅ  ኢትዮጵያውያኞች  አለመሆናችንን  ነግረውናል ያሉት  ነዋሪዎቹ  አሁን  ካሉበት  የስቃይ  ኑሮ  ለመላቀቅ  በስደት  የምንሄድበት  ሀገር  ይመቻችልን  ሲሉ  መንግስትን  ጠይቀዋል። በንፋስልክ  ላፍቶ  ክፍለከተማ  መንግስት  ባደረገው  የቤት  ማፍረስ  ዘመቻ  ከ30 ሺህ  በላይ  ሰዎች  መፈናቀላቸውን  መዘገባችን  ይታወሳል።

Read More »

በቅርቡ ሶስት ም/ጠቅላይ ሚኒስትሮች መሾማቸው ከህገ-ወጭ በመሆኑ በተለያዩ የመንግሰት አካላት ላይ ክስ ሊመሰረት መሆኑ ተገለፀ

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-34  የተቃዋሚ  ፓርቲዎችን  በአባልነት  ያቀፈው  ጊዜያዊ  አስተባባሪ  ኮሚቴ  ባወጣው  መግለጫ  እንዳስታወቀው  ህገ-መንግስቱን  በመጣስ   ሶስት ጠ/ሚኒስትሮች በሾሙት  በ/ጠ/ሚ/ር  ሀ/ማርያም  ደሳለኝ፣  በህዝብ  ተወካዮች  ም/ቤትና  ሹመቱን  በተቀበሉት  ሶስቱ  ም/ጠ/ሚኒስትሮች  ላይ  ክስ ሊመሰረት  መሆኑን  ገልጠዋል። ተሾሚዎቹም  ቢሆኑ  ሹመቱን  መቀበል  የለባቸውም  ነበር  ያሉን  መግለጫውን  አስመልክተን  ያናገርናቸው  ያስተባባሪ  ኮሚቴው  ፀሀፊ  አቶ ግርማ  በቀለ  ህገ-ወጥ  መሆኑን  እያወቁ  በመቀበላቸው  ተከሳሾች  ኛቸው  ብለዋል።   በሙስሊሙ  መፍትሄ  አፈላላጊ  ኮሚቴ  አመራር  አባላት  ላይ  የተመሰረተው  ክስ  አግባብ  አይደለም  ያሉት  የ34  ተቀዋሚ  ፓርቲ  ጊዜያዊ አስተባባሪ  ኮሚቴ  ፀሀፊ  አቶ  ግርማ  በቀለ  በዚህና  በአዲስ  አበባ  ከተሞች  በሚኖሩ  ነዋሪዎች  ላይ  ቤታቸውን  በማፍረስ  የመኖር  መብታቸውን መንግሰት  በመጣሱ  እንቃወመዋለን  እዚህ  ላይም  እየሰራን  ነው  ብለዋል። መንግስት  ሁሉንም  በእኩል  የማስተዳደር  ሀላፊነት  እንዳለበት  የገለፁት   አቶ  ግርማ  ከዚህ  በፊት  ያቀረብናቸውን  ጥያቄዎች  አልመለሱልንም ለዚህም  በተለየ  አግባብ  ለጥያቄያችን  መልስ  ለማግኘት  እንሰራለን  ሲሉ  አስታውቀዋል።

Read More »

በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት እስላማዊ መንግስት ለመመስረት እንሰራ ነበር ብላችሁ እመኑ በመባል እየተደበደቡነ እየተሰቃዩ መሆኑ ተገለጠ

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት እስላማዊ መንግስት ለመመስረት እንሰራ ነበር ብላችሁ እመኑ በመባል እየተደበደቡነ እየተሰቃዩ  መሆኑ ተገለጠ:: በዛሬው እለት የነበራቸው ቀጠሮም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መሰረዙ ታወቀ:: በሌላ በኩል ደግሞ በነገው እለት በአጠቃላይ በሀገሪቱ ታላቅ የተቃውሞ ትእይንት በየመስኪዱ እንደሚደረግ ተገለጠ:: ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት አሸባሪ በሚል ክስ የተመሰረተባቸው የሙስሊሙ ...

Read More »

በግብጽ በፕሬዚዳንቱ ቤተመንግስት በተቃዋሚዎችና በፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች መሀከል በተነሳ ግጭት 5 ሰዎች መገደላቸውንና ከ 644 በላይ መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘገበ::

 ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህን ግጭት ተከትሎም የግብጽ ሰራዊት ከፕሬዚዳንቱ ቤተመንግስት አካባቢ ተቃዋሚዎችንና የመገናኛ ብዙሀን አባላትን በማስወጣት ላይ ይገኛል:: ከቤተ መንግስቱ አካባቢ እንዲለቁ በተሰጣቸው የሰአት ገደብ መሰረት አብዛኖቹ ተቃዋሚዎች መልቀቃቸው ሲታወቅ የተወሰኑ የተቃዋሚ አክቲቪስቶች በዛው እንደሚገኙ የቢቢሲዘገባ አመልክቶል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋነኛው የግብጽ እስላማዊ አካል ፕሬዚዳንት ሙርሲ የሀገሪቱን አጠቃላይ ስልጣን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል የተባለውን ህግ እንዲያነሱ ጠይቆል:: ...

Read More »