Author Archives: Central

በቤንች ማጂ በተከሰተ ግጭት ከ150 በላይ ሰዎች ተገደሉ

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን በቤሮ ሻሻ ወረዳ በሳሊ ቀበሌ በሚገኝ ባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ መንደር በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት  ከ 162 ሰዎች በላይ መገደላቸው ታውቋል:: የአካባቢው የኢሳት የመረጃ ምንጭ እንደገለጸው  መንግስት የፌደራል ፖሊስ ሀይሎችን በስፍራው  ቢያሰማራም የክልሉ መንግስት የራሳችንን የውስጥ ችግር ራሳችን ነን የምንፈታው የሚል አቋም በመያዙ የፌደራል ፖሊስ ሀይሎች ወደ አካባቢው ...

Read More »

ለሞባይል ስርጭት ጥራት መጋደል የአዲስ አበባ ህንጻዎች ምክንያት ናቸው ተባለ

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት ሁለት ዓመታት በፍራንስ ቴሌኮም ኩባንያ የማኔጅመንት አባላት ሲተዳደር የቆየው ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስአበባ የሕንጻዎች ግንባታ መበራከት ጋር ተያይዞ የሞባይል አገልግሎት ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን በይፋ ገለጸ፡፡ የፍራንስ ቴሌኮም የማኔጅመንት አባላት ኮንትራት መጠናቀቅን አስመልክቶ ከሁለት ቀናት በፊት  በሸራተን ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙት ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የመገኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እንደተናገሩት ...

Read More »

በኢኦተቤተክ አባቶች መካከል ሲደረግ የነበረው የሽምግልና ጥረት ውጤት ባለማሳየቱ በሆላ የምእመናኑ ሀላፊነት መሆኑ ተገለጠ

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከአ ፃዲቅ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት በቤተክርስቲያኖ አባቶች መካከል አንድነት ለማምጣት ያደረግነው ጥረት ብዙም ተስፋ የሚጣልበት አይልሆነም ከዚ በሆላ ያለው ሀላፊነት በምእመኑ ላይ የሚወድቅ ነው ብለዋል:: የሽምግልና ቡድኑ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት ጥሮ ነበር ከሀገር ቤት የሚመጡት አባቶች ግን በስልክ መልካም ነገር ተለዋውጠን እዚህ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተነሳ ግጭት ተማሪዎች ተጎዱ

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ፋኩልቲ እየተባለ በሚጠራው ግቢ ትናንት ምሽት ተጀምሮ ዛሬ ከጧቱ 3 አሰት ላይ በድጋሜ በተፈጠረ የብሄር ግጭት በርካታ ተማሪዎች በመጎዳታቸው በአምቡላንስ ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስደዋል። ግጭቱ በመካረሩ ከሰአት በፊት ከአራት ኪሎ ወደ ስድስት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ነበር። የዩኒቨርስቲው ጠባቂዎች ግጭቱን መቆጣጠር ባለ  መቻላቸው ሙሉ የድንጋይ መከላከያ የለበሱ  ...

Read More »

በአማራ ክልል የተጀመረው የህዝብ ማመላለሺያ ሾፌሮችና ባለንብረቶች አድማ ለ4ኛ ቀን እንደቀጠለ ነው

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከታህሳስ 22 ቀን ጀምሮ በመካሄድ ላይ ያለዉ የአማራ ክልል የህዝብ ትራንስፖርት ሾፌሮች እና የመኪና ባለንብረቶች የስራ ማቆም አድማ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከባህር ዳር ወደ ጎንደርም ሆነ ወደ ደብረማርቆስ አገልግሎት የሚሰጡ አዎቶቡስና ሚኒባሶ መኪኖች  ባለመኖራቸዉ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ ተውቋል። የሚኒባስ ሾፌሮች ” መንግስት በእኛ ላይ በመድረስ ላይ ያሉትን ችግሮች በዉይይት ለመፍታት እንዲያነጋግረን ...

Read More »

በዲላ አንድ የመንግስት ሹም አንድ ወጣት ገድለ የወጣቱን አባትም አቆሰለ

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጌዲዮ ዞን በዲላ ከተማ ኮማንደር ግርማ በየነ የተባለ የዞኑ የፖሊስ የሰው ሀብት ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ ድርጊቱን የፈጸመው አባትና ልጅ ከግቢያቸው ፊት ለፊት ቆመው የግል ጉዳያቸውን በሚነጋገሩበት ጊዜ ነው። ከምሽቱ 12 ሰአት አካባቢ ኮማንደሩ ወደ ቤቱ እየሄደ በነበረበት ሰአት አባት እና ልጁን ውጭ ላይ ቆመው ሲያገኛቸው፣ ምን ታደርጋላችሁ ብሎ መጠየቁን፣ የሟቹ አባትም ” ከልጄ ...

Read More »

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያቀረበውን የመነጋገርና የመታረቅ ጥያቄ ውድቅ አደረጉ

ታህሳስ  ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ቃል የተመላለሱት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኤርትራ ስልጣን ላይ ካሉ ግለሰቦች መቀያየር ጋር የምታያይዘው አንዳችም ነገር የለም ካሉ በሆላ ዝንባሌው እራሱ ከኤርትራ ባህልና እሴት የሚቃረን መሆኑን ገልጠዋል:: እንነጋገር የሚለው አባባል ምንጩ ከየት እንደሆነ እንረዳልን ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይህ አይነት አካሄድ ትኩረት ከማስቀየር በቀር ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ኤርትራም የምትገባበት ድራማ እንዳልሆነ አመልክተዋል:: ...

Read More »

በመቀሌ ከተማ የግል ጋዜጣና መጽሄት አዞሪዎችና ሻጮች ስራቸው ህገወጥ በመሆኑ ከስራ መታገዳቸው ተገለጠ

ታህሳስ  ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በከተማዋ በቆሚነት ደርድረውና እያዞሩ ጋዜጣና መጽሄት የሚሸጡ በመከልከላቸው ህዝቡ ጋዜጣ ማግኘት አለመቻሉን የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎችና የቅርብ ምንጮች ያላቸውን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቦል:: ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁና በአካባቢው ጋዜጣና መጽሄት በመሸጥ የሚተዳደሩ ወጣቶች የጠቀሰው ዘገባ የከተማዋ ወያኔ ወረዳ ንግድና ኢንዱስትሪ አስተዳደር ስራው ህገወጥ መሆኑ ተገልፆላቸው ከታህሳስ 5፣2005 ጀምሮ በአካባቢው የገል ጋዜጣና መጽሄት የመሸጥ ስራ እንዳይሰራ ...

Read More »

ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አወዛጋቢ መልሶችን ሰጡ

ታህሳስ  ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት መልስ በርካታ አወዛጋቢ ነገሮችን ተናግረዋል። በኤርትራ ዙሪያ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለምልልሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተተቹት አቶ ሀይለማርያም በዛሬው ንግግራቸው በተተቹበት ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል። አቶ ሀይለማርያም ” አስመራ እሄዳለሁ ያልኩት በየትኛውም ቦታ እንደራደራለን የሚለውን የመንግስት አቋም አጽንኦት ለመስጠት ነበር” ሲሉ  ተናግረዋል። ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ...

Read More »

ተማሪዋን አስገድዶ የደፈረው የተማሪዎች ዲን በነጻ ተለቀቀ

ታህሳስ  ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ዲን የሆኑት አቶ ናትናኤል ህዳር 27 ቀን 2005 ዓም የሚያስተምሯትን ተማሪ ስልክ በመደወል ከምሽቱ 1፡30 ገዳማ ቢሯቸው ድረስ ካስጠሩ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸሙባት መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ተማሪዎች እንደገለጹት ደግሞ የጸጥታ አካላት እንዲሁም የዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ለፖሊስ ሊተባባሩ ባለመቻላቸው የተማሪዋ ህይወት አደጋ ውስጥ ወድቋል። የተደፈረችው ተማሪ በግሏ ጥረት ወደ ዩኒቨርስቲው ሆስፒታል ...

Read More »