በኢኦተቤተክ አባቶች መካከል ሲደረግ የነበረው የሽምግልና ጥረት ውጤት ባለማሳየቱ በሆላ የምእመናኑ ሀላፊነት መሆኑ ተገለጠ

ታህሳስ  ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከአ ፃዲቅ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት በቤተክርስቲያኖ አባቶች መካከል አንድነት ለማምጣት ያደረግነው ጥረት ብዙም ተስፋ የሚጣልበት አይልሆነም ከዚ በሆላ ያለው ሀላፊነት በምእመኑ ላይ የሚወድቅ ነው ብለዋል::

የሽምግልና ቡድኑ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት ጥሮ ነበር ከሀገር ቤት የሚመጡት አባቶች ግን በስልክ መልካም ነገር ተለዋውጠን እዚህ ሲመጡ አንዳች ነገር የሚስማሙት ያጣሉ ያሉት አቡነ መልክአፃዲቅ ምንአልባትም ከመንግስት ጫና ሳይኖርባቸው አይቀርም ብለዋል::

ምን ልባት ለወደፊት ይህ አሁን የሚፈለገው አንድነት ይመጣ ይሆን ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ የመለሱት  ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከአ ፃዲቅ የለም አይመስለኝም ፡ አሁን ካመለጠን አበቃ ከዚህ በሆላ የሚመጡት አዲሶች ናቸውና የነገሩን ስር አያውቁም እኛም በአዲስ መተካታችን አይቀርም ብለዋል::

ቤተክርስቲያን ሲፈርስ ምእመናን ዝም ብሎ መመልከት የለበትም ፡ከዚ በሆላ ያለው ሀላፊነት የህዝብ ነው ብለዋል::

ለቀጣይ ድርድር በሎስ አንጀለስ ቀጠሮ ይዛችሆል ምን ይጠብቃሉ ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ብዙም አዲስ ነገር ይመጣል ብዬ አልጠብቅም ሲሉ መልሰዋል ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከአ ፃዲቅ::

የህውሀት አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሀት ነጋ እርሶ ሙስሊሞችን ደግፈው መግለጫ ሰጥተዋል ፡አክራሪነትን ከሚደግፍ ጋር እንዴት መደራደር ይቻላል ተብለዋል ምን መልስ አሎት ተብለው ለተጠየቁት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከአ ፃዲቅ ሲመልሱ ሙስሊሞችም እኮ ኢትዮጵያኖች ናቸው ፡መብታቸው መከበር አለበት ማለቴ ትክክል ነው ሲሉ መልሰዋል::

በተጨማሪም በሀይማኖት ሳሚያ ማንም ሰው መጨቆንና መበደል የለበትም ያሉት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከአ ፃዲቅ ሙስሊሞቹም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ናቸው የነሱም መብት መከበር አለበት ባይ ነኝ አሁንም በዚህ አቆሜ እጸናልሁ ብለዋል::

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእምነት ነጻነት ዙሪያ  ባነሱት ጥያቄ ከመንግስት ጋር ተፋጠው ለአመት መታገላቸው የሚታወቅ ሲሆን በርካቶች በእስር ቤት ይገኛሉ ፡የተገደሉና የተሰደዱም ጥቂት የሚባሉ እንዳልሆኑ ይታወቃል::