Author Archives: Central

በጅጅጋ የተካሄደው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ማለፉ በክልሉ ሰላም አለመኖሩን ያመለክታል ሲሉ አንድ ታዛቢ ተናገሩ

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በመንግስት የሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ አንድ ስማቸው እንዳይገለጸት የፈለጉ ሰው ለኢሳት እንደተናገሩት በክልሉ በቆዩባቸው ቀናት የታዘቡት ነገር ቢኖር በክልሉ የሰላም እጦት ዋናው ችግር መሆኑን ነው። ምንም እንኳ መንግስት ያለምንም ችግር በአሉ መጠናቀቁን ቢገልጽም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ እንደነበር ሃላፊው ይናገራሉ። በከተማዋ ዳርቻዎች ታንኮች፣ ከባድ መሳሪያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ፣ ልዩ ኮማንዶችና እና እስካፍንጫቸው የታጠቁ እግረኛ ...

Read More »

የኢህአዴግ አመራር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖምን ገሰጸ

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የወደፊቱ ጠ/ሚንስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የሚነገርላቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ግሳጼው የቀረበባቸው ” በሳውድ አረቢያ ላይ ተመጣጣኝ የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን” ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ነው። ኢህአዴግ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን ዶ/ር ቴዎድሮስም ” ያለግንባሩ ውሳኔ እንዲህ አይነት ጠንካራ አስተያየት ለምን እንደሰጡ እንዲያብራሩ ተጠይቀዋል። “ዶ/ር ቴዎድሮስ በቂ ማብራሪያ ለመስጠት ባለመቻላቸው ግለ-ሂሳቸውን እንዲያወርዱ ተጠይቀዋል። ከፓርቲው ይልቅ ...

Read More »

አንድ ወጣት የመንግስት ሰራተኛ መንግስትን በመቃወም ራሱን አጠፋ

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤ ባለሙያ የሆነው  ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ በሙያው ለአመታት ህብረተሰቡን ሲያገለግል ቢቆይም የመንግስትን አሰራር በተደጋጋሚ በመተቸቱ፣ ከመስርያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ግዜያት ግጭት ውስጥ ከመግባቱም በላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሳይቀር ደርሶት ነበር። ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ መንግስትን በግልፅ በመቃወም፤ መስተካከል ያለበትን ጉዳይ በግልፅ መናገር ልዩ ባህሪው እንደነበር የሚናገሩት ጓደኞቹ፣ በዚህ ባህሪው ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአዲሲቷ አገር መሪ የሆኑት ሳልቫኪር  የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ታማኝ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሌሊቱን ተኩስ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነቱን ድርጊት እንደማይታገሱትና ሙከራውን ባደረጉት ላይ ሁሉ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። የአገሪቱ ቴሌቪዥን ከጠፋ ከሰአታት በሁዋላ እንደገና ስራ ጀምሯል። እስካሁን ድረስ ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ አልታወቀም። በደቡብ ሱዳን ...

Read More »

ለጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ ህክምና የሚውል የእራት ግብዣ ተዘጋጀ

ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በቀረረበባቸው የፕሬስ ክስ ወደ አዋሳ በተጉዋዙበት ወቅት በድንገት በተከሰተ የተሸከርካሪ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ  አዘጋጅ ለሆነው ለወጣት ኤፍሬም በየነ የሕክምና ወጪ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት ሰኞና ማክሰኞ በአዲስአበባ እንደሚካሄድ ከዕርዳታ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ለሪፖርተራችን ገልጿል፡፡ በዚህ የእራት ምሽት ላይ 500 ብር ዋጋ ያላቸው ትኬቶች ተዘጋጅተው በመሸጥ ላይ ሲሆኑ በተለይ ጋዜጠኞች ...

Read More »

በአዲስ አበባ የመሬት ማኔጅምንት እና ተዛማጅ ችግሮች እየተባባሱ መምጣታቸውን አመራሮች ገለጹ፡፡

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አልፎ አልፎ አንዳንድ አመራሮች በአመለካከትም ሆነ በተግባር በሙስና ተዘፍቀው ተገኝተዋል ያለው የአስተዳደሩ ሰነድ፣ በከተማው ውስጥ ሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ ሕገወጥ ግንባታና ሕገወጥ ንግድ አሁንም አሳሳቢ ችግሮች ሆነው መቀጠላቸውን አትቷል፡፡ በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮችን ጠርቶ የመከረው ቢሮው ችግሮች በስፋት የመልካም አሰተዳደር እጦት መገለጫ እየሆኑ መምጣታቸውን የቢሮው ሃላፊ አቶ ሰለሞን ሃይላይ ...

Read More »

ከ600 በላይ አባዎራዎች ቤታቸውን በ3 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ትእዛዙን የሰጠው የቦሌ ክፍለከተማ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ እስከ ማክሰኞ ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ ፣ አፍራሽ ግብረሀይል በጉልበት እንደሚያፈርስባቸው አስታውቋል። “በሶስት ቀናት ውስጥ የት እንሄዳለን?’ ሲሉ የሚጠይቁት ነዋሪዎች ፣በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚታየው የቤት ኪራይ መጨመር አስግቶናል ብለዋል። ሜዳ ላይ እንዃ እንዳንወድቅ ሜዳውም እየታረሰ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ባለስልጣናት በስልጣናቸው ...

Read More »

በኢትዩጵያ ያለ እድሜ ጋብቻ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ  62 በመቶ የሚሆኑት ከ 20- 49 እድሜ ክልል የሆናቸው ሴቶች ጋብቻ የመሰረቱት እድሚያቸው ከ 18 ዓመት በታች በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ አቶ ተስፋየ ተካ የህዝብ ጤና ባለሙያ ባደረጉት ጥናት በላፈው ዓመት ልዩነቶችን ለማወቅ በተካሄደ ጥናት  በአማራ ክልል ያለ እድሜ ጋብቻ  ከፍተኛውን መጠን እንደያዘ ይኸው ጥናት ይጠቁማል፡፡48 በመቶ በገጠር 28 በመቶ በከተማ ያገቡ ሴቶች ...

Read More »

የድምጻችን ይሰማ ዋና መሪዎች እንዲከላከሉ ተበየነባቸው

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ተከላከሉ መባላቸውን ጠበቃ  ተማም አባ ቡልጉ ተናግረዋል። 12 ሰዎች በነጻ የተለቀቁ ሲሆን፣ እነ አቶ አቡበከር አህመድና ሌሎች ደግሞ በተከሰሱበት ሽብር የማድረግ ወንጀል ሳይሆን ሽብር በማነሳሳት ጉዳይ ላይ እንዲካለከሉ ተበይኖአል። ሙራድ ሹኩር ጀማል፣  ኑሩ ቱርኪ  ኑሩ፣ ሼህ ባህሩ ኡመር ሸኩር እና ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ደግሞ ...

Read More »

መድረክ በኢትዮጵያ ያለው አፈና መባባሱን ገለጸ

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ  ዓርብ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን፣  ዶ/ር መረራ ጉዲና ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና እየተባባሰ መሄዱ መግለጫውን ለመስጠት አስገድዷቸዋል። የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም መድረክ ቢጠይቅም በገዢው ፓርቲ መከልከሉን ዶ/ር መረራ አውስተዋል ( 1፡49-03፡10) መንግስት የሳውድ አረቢያ ...

Read More »