Author Archives: Central

በእስር ላይ የሚገኘው እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2014 የፔን አለማቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት ቶማስ ብሩኒጋርድ ” እስክንድር አፋኝ የፕሬስ ህግ ባለበት አገር በድፍረት ለመጻፍ በመቻሉ ሽልማቱ እንደተሰጠው ገልጸው፣ የኢትዮጵያ መንግስት እስክንድርን ጨምሮ በአሸባሪነት ታስረው የሚገኙትን ሰሎሞን ከበደ፣ ውብሸት ታየ፣ ርእዮት አለሙ እና የሱፍ ጌታቸውንም እንዲለቅ ጠይቀዋል። የፔን አለማቀፍ  ሽልማት ለፕሬስ ነጻነት ለሚታገሉት ጋዜጠኞች በእየአመቱ የሚሰጥ ሽልማት ነው። ከዚህ በፊት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናም ...

Read More »

የአረና ትግራይ መሪዎች ለቅስቀሳ በሄዱበት አዲግራት ተደበደቡ

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባሩ የቀድሞው የህወሀት ታይ እና አሁን የአረና ከፍተኛ አመራር አቶ አስገደ ገብረስላሴ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጻፍ የሚታወቀው ና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር አብረሃ ደስታ እንዲሁም የፓርቲው የአመራር አባል አቶ አምዶም ገ/ስላሴ እሁድ እለት ከአዲግራት ህዝብ ጋር ለመነጋገር ወደ ስፍራው ቢያቀኑም በከተማው የደህንነት ፣ የፖሊስና የቀበሌ ሹሞች የሚመሩ ወጣቶች ድብደባ በመፈጸማቸው ስብሰባውን ማከሄድ ሳይችሉ ...

Read More »

በሽብርተኝነት ህጉ ውይይት ስም የአዲስ አበባ ህዝብ እየተሸበረ ነው ሲሉ አንዳንድ ተወያዮች ገለጹ

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና በተዋረድም ከህዝቡ ጋር እተደረገ ባለው የሽብርተኝነት ህግ ውይይት፣  ነዋሪዎች ጥላቸውን እንኳን ማመን እንደሌለባቸው በአሰልጣኞች እየተነገራቸው ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ የተካፈሉ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች፣ ስለሽብረተኝነት ልንማር ሂደን ተሸብረን መጣን ሲሉ ተናግረዋል። በመንግስት  ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የማሰልጠኛ ሰነድ ኢሳት እጅ የገባ ሲሆን፣ ሰነዱ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን ቆሞ ...

Read More »

በቁጫ ከታሰሩት መካከል 13 ቱ ፍርድ አገኙ

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 16፣ 2006 ዓም ባስቻለው ችሎት በእነ አቶ ደፋሩ ዶሬ መዝገብ የተከሰሱ 13 ሰዎች በሙሉ በ2 አመት ከ9 ወራት እስር እንዲቀጡ ወስኗል። በውሳኔው መዝገብ ላይ እንደተመለከተው እስረኞቹ የተፈረደባቸው “ እኛ ወይም ቁጫ የጋሞ ብሄረሰብ አይደለንም በሚል ህዝብን አነሳስታችሁዋል፣ ህገወጥ ስብሰባ አድርጋችሁዋል፣ እንዲሁም የጸረ- ህዝብ አቋም አራምዳችሁዋል” ...

Read More »

በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ባልመረጥነው መጅሊስ  አንተዳደርም!  ያላመንንበትን የሀይማኖት አስተምህሮ አንቀበልም! የህዝበ-ሙስሊሙ የትምህርት ተቋም የሆነው አወሊያ ትምህርት ቤት  በገለልተኝነት ይተዳደር” የሚሉ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው የ አሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው የሙስሊም አመራሮች ወደ ወህኒ ከወረዱ ከሁለት ዓመታት በላይ ተቆጠሩ። ለሁለት ዓመታት ከዘለቀው የፍትህ ሂደት በሁዋላ  በቅርቡ  ለብይን  በተቀጠረው  ችሎት ላይ በብዘዎች ሰንድ ታሳሪዎቹ  በሙሉ ይፈታሉ የሚል ...

Read More »

ለወራት ተቋርጦ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ተጀመረ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬው የሰደቃ እና ዱአ መርሀ ግብር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሚገኙ ሙስሊሞች በእስር ላይ የሚገኙ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትን አስበው ውለዋል። እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሳትም ለፈጣሪያቸው ተመጽኖ አቅርበዋል። በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ በመቶሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቶ ድዋ አድርጓል። መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ተቆጣጥሬዋለሁ በማለት መግለጫዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። የተለያዩ ፊልሞችን በመስራትም ...

Read More »

ከቁጫ ችግር ጋር በተያያዘ በአርባምንጭ እስር ቤት የታሰሩ የ232 ሰዎች ስም ዝርዝር ታወቀ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት፣ ከልማትና መልካም አስተዳዳር ጋር በተያያዘ በአርባምንጭ እስር ቤት የታሰሩ የ232 የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች ስም ዝርዝር የወጣው ከራሳቸው ከእስረኞች ነው። ለኢሳት ከተላከው ስም ዝርዝር ለመረዳት እንደተቻለው አብዛኞቹ እስረኞች አርሶ አደሮች ቢሆኑም፣ 5 የሃይማኖት አባቶች፣ 7 መምህራን፣ 6 ነጋዴዎች፣ 25 ተማሪዎች፣ 22 በልዩ ልዩ የመንግስት ስራ ላይ የሚገኙ፣ 5 መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ...

Read More »

በይርጋጨፌ መምህራን ለሁለተኛ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፍላጎታቸው ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የይርጋ ጨፌ ሁለተኛ ደረጃ መምራህራን ከወር በፊት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ ፣ የተቆረጠባቸው ደምዞ ተመልሶ እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረ ቢሆንም፣ የወረዳው አስተዳዳሪ ገንዘቡ በዝግ አካውንት የገባ በመሆኑ፣ ገንዘብ ለመክፈል አንችልም በሚል ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ መምህራኑ ከትናንት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ አድረገዋል። አድማው ዛሬም ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳደር 285 የተለያዩ መኪኖችን ለሰራተኞቹ ገዛ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ መኪኖችን የገዛው በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ላይ ለሚገኙት ሰራተኞቹ ነው። ከተገዙት መኪኖች መካከል 18፣  የ2013 ምርት የሆ ኑ ፕራዶ መኪኖች፣ 2 መቶ 40 ባለ ሁለት ጋቢና ማዝዳ ፒክ አፕ፣ 27 ያሪስ ቶዮታ መኪኖች የቢሮ ሃላፊዎች፣ም/ቢሮ ሃላፊዎችና ፣የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የካቢኔ አባላት እንዲጠቀሙባቸው አየተሰራጩ ነው። መኪኖቹ በጉምሩክ በኩል ከገቡ በኋላ ...

Read More »

የሰንደቅ ጋዜጣ አዘጋጆች በማእከላዊ ምርመራ ቀርበው ቃላቸውን ሰጡ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋዜጣው አዘጋጆች በማህበራዊ ድረገጾች ላይ በለቀቁት ዜና “በሰንደቅ ጋዜጣ ቁጥር 434 ታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓ.ም በወጣው “ጉዲፈቻ፤ በኢ-ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የኪራይ ሰብሳቢዎች ዋሻ ተንኳኳ” በሚል ርዕስ በገጽ 5 በፖለቲካ ዓምድ ላይ በሰፈረው ጽሁፍ መነሻነት የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ እና በም/ዋና አዘጋጁ ፋኑኤል ክንፉ ...

Read More »