ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲ መስራችና የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ የነበሩት አሁን ደግሞ የፓርቲው የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ አኬልዳማ በሚል በመንግስት የተዘጋጀውን ዶኩመንታሪ ፊልም በአዲስ ጉዳይ መጽሄት ላይ ዘለፋ አዘል ጽሁፍ ጽፈዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ፣ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ለአንድ ሳምንት ታስረው በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርቡ ወስኗል። በዚህም መሰረት ...
Read More »Author Archives: Central
የሃሙሲት ነዋሪዎች ገዢው ፓርቲ እየተበቀለን ነው ይላሉ
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር 30 ኪሚ ርቃ በምትገኘው በደቡብ ጎንደሩዋ ሃሙሲት ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ገዢው ፓርቲ እየተበቀለን ነው ሲሉ ይናገራሉ። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር ሲያደርግ በነበረው ጦርነት ሃሙሲት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። በዚህም በቀል ይመስላል ይላሉ ነዋሪዎች ፣የህወሃት የደህንነት ሰዎች በከተማ ውስጥ አሉ የሚባሉ ታላላቅ ሰዎችን ከመግደል ጀምሮ አፍነው ...
Read More »የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት በመስተዳድሩ ግቢ ውስጥ የሚቆሙ መኪኖች ታርጋቸው እንዲፈተሽ አሳሰበ
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አሰግድ ጌታቸው ይመኑ ጥር 29 ቀን 2006 ዓም ለሁሉም የመስተዳድሩ ቢሮችና ለክፍለከተሞች በጻፉት ደብዳቤ ፣ ማንኛውም በግቢው ውስጥ የሚያድር መኪና የማን እንደሆነ ለማወቅ ይቻል ዘንድ ታርጋቸው ተገልጾ ይቅረብልን ብለዋል። ደብዳቤው በግልባጭ ለግቢው ጸጥታ ዴስክ ተመርቷል። መስተዳድሩ ይህን ደብዳቤ የጻፈው ኢሳት በቅርቡ በመስተዳድሩ ግቢ ውስጥ ...
Read More »አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ክብረ-ወሰን ሰበረች።
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊድን-ስቶኮሆልም በተካሄደው የቤት ውስጥ የ 3 ሺ ሜትር ውድድር አትሊት ገንዘቤ ዲባባ በአስደናቂ ብቃት በማሸነፍ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች። ገንዘቤ ዲባባ ርቀቱን በ8:ደቂቃ 16 ሴኮንድ 60 ማይክሮ ሴኮንድ በማጠናቀቅ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2007 ዓመተ ምህረት፣ ማለትም ከ 7 ዓመት በፊት በአገሯ ልጅ በአትሌት መሰረት ደፋር ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ከ7 ሰከንድ በላይ አሻሽላለች። ...
Read More »የዩክሬንን የውስጥ ቀውስ አስመልክቶ የ አሜሪካ ባለስልጣናት የአውሮፓ ህብረትን ሲዘልፉ የሚደመጡበት የስልክ ምልልስ አፈትልኮ ወጣ።
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩናይትድ ስቴስት ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ምክትል ሴክሬታሪ ቪክቶሪያ ኑላንድ- በዩክሬን ከ አሜሪካ አምባሳደር ጋር ስለ ዩክሬን ግጭት በስልክ ያወሩት ወሬ ተጠልፎ በድረ ገፆች መለጠፉ አሜሪካን ማሳፈሩን ዘገባዎች አመልክተዋል። ቪክቶሪያ ኑላንድ በዙሁ የስልክ ምልልስ ላይ ስለዩክሬን ግጭት ሲያወሩ የአውሮፓ ህብረትን ሲወቅሱና በወረደ ቃላት ሲዘልፉ ይሰማሉ። በሁኔታው የደነገጠችው አሜሪካ ፦”ቪክቶሪያ ኑላንድ ለተናገሩት ነገር ይቅርታ ጠይቀዋል” ...
Read More »በለገጣፎ ለገዳዲ አስደንጋጭ የመሬት ዝርፊያ እየተካሄደ ነው
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የኦሮምያ ልዩ ዞን እየተባለ በሚጠራው የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የሚገኘው የአርሶአደሩ መሬት በከተማዋ ውስጥ ባልኖሩና ማንነታቸው በማይታወቅ ሰዎች ስም መያዙን ለኢሳት የደረሰው ሰነድ አመልክቷል። ከ4 ሺ በላይ ሰዎችን ስም ዝርዝር በያዘው በዚህ ሰነድ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች የአባታቸውን ስም ብቻ በመቀያየር ከ 140 እስከ 500 ካሬ ሜትር ...
Read More »በአማራው ክልል መሪ ንግግር ህዝቡ ቁጣውን እየገለጸ ነው
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን የጽ/ቤት ሃላፊና የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት የሆኑት አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ መዝለፋቸውን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቁጫቸውን እየገለጹ ነው። በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች ከሚሰጡት አስተያየቶች በተጨማሪ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በመደውል አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ ግለሰቡ ከመነሻቸ ጠንካራ የትምህርት ደረጃ የሌላቸው በመሆኑ፣ ከዚህ ያለፈ እንዲናገሩ አይጠበቅም ብለዋል ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ...
Read More »አራት ኢትዮጵያውያን በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ተያዙ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ አፍሪካ ሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት አራቱ ኢትዮጵያውያን በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል የታየዙት በተለያዩ ቀናት ነው። ቱምሳ ሮባ ካቲሶ የተያዘው ኢስሊ እየተባለ በሚጠራው የገበያ ስፍራ ሲሆን፣ በሁለት መኪኖች የመጡ የጸጥታ ሃይሎች በፈረንጆች አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 1፣ አፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ ወስደውታል። ጫላ አብደላ፣ ናሚ አብደላ፣ እንዲሁም ስሙ በውል ...
Read More »የጣሊያን ፖሊሶች ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ህይወት አተረፉ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአፍሪካ በመርከብ ተሳፍረው ወደ አውሮፓ ለመግባት የሞከሩ 1 ሺ 100 የሚጠጉ ስደተኞች በጣሊያን ፖሊሶች እርዳታ አውሮፓ እንዲገቡ ተድርጓል። ከዚህ በፊት ላምባዱሳ እየተባለ በሚጠራው የጣሊያን ግዛት አካባቢ ከደረሰውን አሰቃቂ አደጋ በሁዋላ የጣሊያን ፖሊሶች ወደ አውሮፓ የሚገቡ አፍሪካውያንን ህይወት እየታደጉ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ወደ አውሮፓ ከገቡት መካከል 50 ህጻናትና 47 ሴቶች ...
Read More »አውራ የኢህአዴግ ፓርቲዎች አዳጊ ክልሎችን ለማስተዳደር ስልጣን ተሰጣቸው
ጥር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ እየተባለ የሚጠራውን ግንባር የመሰረቱት 4ቱ ፓርቲዎች ህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን አዳጊ ክልሎች እየተባሉ የሚጠሩትን ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ ድሬዳዋ፣ ሶማሊና አፋር ክልሎችን ለማስተዳደርና በበላይነት ለመምራት መከፋፈላቸውን ከኢህአዴግ ፅ/ቤት የተገኘው የውሰጥ መረጃ አመለከተ። በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 52 ክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣን የተሰጣቸው ሲሆን፣ ስልጣናቸውን ተጠቅመመውም የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የመህበራዊና የልማት ...
Read More »