አቶ አስራት ጣሴ ታሰሩ

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲ መስራችና የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ የነበሩት አሁን ደግሞ የፓርቲው የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ አኬልዳማ በሚል በመንግስት የተዘጋጀውን ዶኩመንታሪ ፊልም በአዲስ ጉዳይ መጽሄት ላይ ዘለፋ አዘል ጽሁፍ ጽፈዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ፣ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ለአንድ ሳምንት ታስረው በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርቡ ወስኗል። በዚህም መሰረት አቶ አስራት ጣሴ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።

አቶ አስራት በዋስ የመውጣት መብት ቢኖራቸውም ፍርድ ቤቱ ለምን በመዋስ እንዲለቀቁ እንዳላደረገ የታወቀ ነገር የለም።