ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ለከፈልነው መስዋትነት አቻ ውጤት እናመጣለን” በሚል መፈክር የተካሄደው ተቃውሞ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት አምርቷል። የፌደራል ፖሊሶች ሆን ብለው ባስነሱት ግጭት ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ቆስለዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኢሳት እስካሁን ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ ባይችልም አንዳንድ ሙስሊሞች ስልክ በመደወል የተገደሉ ሙስሊሞች መኖራቸውን ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊሶች እርምጃ ለመውሰድ ሲዘጋጁ ...
Read More »Author Archives: Central
በለንደን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድረጉ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ፣ የኢህአዴግ መንግስት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወሰደው ህገወጥ እርምጃ የእንግሊዝ መንግስት ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በስፍራው የነበረውን ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹን አነጋግረነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ አሸባሪዎችን እንዲዋጋላቸው በሚል ...
Read More »በዳንሻና ጸገዴ ወረዳዎች አካባቢ የብአዴን እና የህወሃት ታጣቂዎች ተፋጠው እንደሚገኙ ታወቀ
ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በጸገዴ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ በአማራው ክልል ስር ተካለው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ድርጊቱን በመቃወም ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ጋር ተፋጠው እንደሚገኙና በማንኛውም ሰአት ግጭት ይፈጠራል ተብሎ እንደሚፈራ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ወደ 400 የሚጠጉ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ወደ ድንበሩ የተጠጉ ሲሆን፣ በትግራይ ክልል በኩል ምን ያክል ...
Read More »የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት በ24 ሰአታት አገር ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ
ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሰአታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የታዋቂው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የወንድማቸውን ጉዳይ ለመከታተል በሚል ከ10 ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቢያመሩም፣ ከትናንት በስቲያ ደህንነት ጽ/ቤት ከተጠሩ በሁዋላ አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። በታዘዙበት ሰአት ለመመለስ እንደሚቸገሩ የተናገሩት ወ/ሮ ብዙአየሁ፣ የ 24 ሰአት ጊዜ የጊዜ ገደብ ከተሰጣቸው በሁዋላ ...
Read More »የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስርዓቱን በብዛት እየከዱ ነው
ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት ባለፉት 20 ቀናት ብቻ ከባድሜ ግንባር ከ 107 ያላነሱ ሰዎች ከድተው ወደ ኤርትራ እና ወደ መሃል አገር አቅንተዋል። ከ15 ቀናት በፊት በባድሜ አካባቢ ሲያጎ በተባለው ቦታ ላይ የሰፈሩ 60 የ 33ኛ ክፍለጦር አባላት በአንድ ሌሊት ሰራዊቱን ጥለው የጠፉ ሲሆን፣ ኤርትራ መድረስና አለመድረሳቸውን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ወታደሮቹ የጠፉት በክፈለጦሩ ...
Read More »በየረር ባሬ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከታሰሩት የአገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ አረፉ
ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በየረር ባሪ ጎሳዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት 19 አገር ሽማግሌዎች መካከል 2ቱ በእስር ቤት ውስጥ ማረፋቸው ታውቋል። የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች አስከሬን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ሟቾቹን በራሳቸው ጊዜ በመቅበራቸው የብሄረሰቡ ተወላጆች ተቃውሞ አስነስተዋል። ተቃውሞውን በሃይል ለመጨፍለቅ የክልሉ ፕሬዚዳንት ልዩሚሊሺያዎችን ወደ አካባቢው በመላክ ላይ እያሉ ፣ ከአዲስ አበባ በተላለፈ ትእዛዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ፈጥኖ ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ አወገዙ
ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ቁጥር ያላቸው በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጆሃንስበርግ ተነስተው የእንግሊዝ ቆንስላ ወደሚገኝበት ፕሪቶሪያ በማምራት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ ከእነሱ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘችው ዝናሽ ሃብታሙ ኢትዮጵያውያኑ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ነጻ እናወጣለን ማለታቸውን ገልጻለች በሌላ በኩል ደግሞ በአገር ቤት ...
Read More »አንድነትና መኢአድ የውህደት ቀናቸውን በሁለት ሳምንት አራዘሙ
ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አስታውሰው፣ ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ...
Read More »የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት እንደገና ተራዘመ
ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ሰበቦች እየቀረቡበት የሚራዘመው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት ዛሬም በችሎት አዳራሽ ለውጥ ምክንያት እንዲራዘም ተደርጓል። በአቶ አቡበክር ምዝገብ የተከሰሱት ኮሚቴዎች፣ የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ ማስደመጥ እንደጀመሩ ነበር የችሎት ሂደቱ በሰባሰብ እንዲራዘም የተደረገው። ዳኞችና አቃቢ ህጎች በቃሊቲ የሚገኘው የችሎት አዳራሽ ለትራንስፖርት የማያመች በመሆኑ እንዲቀየርላቸው ባመለከተቱት መሰረት አዲሱ ችሎት ሲ ኤም ሲ ሰሚት ...
Read More »የኤድስ ስርጭትን እኤአ እስከ 2030 ማቆም እንደሚቻል ተመድ ገለጸ
ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣ ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ ማቆም እንደሚቻል ገልጿል። አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል። በዚህ አመት በአለም ደረጃ 2 ሚሊዮን 300 ሺ ሰዎች ብቻ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ተይዘዋል። በአጠቃላይ ...
Read More »