Author Archives: Central

በቤንሻንጉል በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ቁጥር 62 ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 1/2011) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በማምቡክና አከባቢው ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ቁጥር 62 መድረሱ ተገለጸ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በማምቡክ 50 በጃዊ ደግሞ 12 ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ኮሚሽኑ ጨምሮ እንደገለጸው በአሁኑ ወቅት በአከባቢዎቹ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል። ተቋርጠው የነበረው የትራንፖርት አገልጎሎትም መጀመሩን ኮሚሽኑ አስታውቋል። የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ ...

Read More »

ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት አደረገች

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2011)በመጨረሻ ሳዑዲ አረቢያ የረመዳን ጾም መግባትን ምክንያት በማድረግ ለኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት ማድረጓ ተገለጸ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው 1 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያን እስረኞች በሳዑዲ አረቢያ የረመዳን ምህረት ተጠቃሚ በመሆን ከእስር ተለቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ እስረኞች በተለያዩ ወንጀሎች የብዙ ዓመታት ቅጣት ተጥሎባቸው በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን አማጺያን ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲጠጋ ትዕዛዝ ተሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2011)የደቡብ ሱዳን አማጺያን ወታደራዊ አዛዥ ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲጠጋ ማዘዛቸው ተሰማ። የሪክ ማቻር ሰራዊት አባላት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ጆር ወረዳ በድብቅ ወታደራዊ ካምፕ መስርተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል። በአርሶአደሩና በጋምቤላ ልዩ ሃይል በተፈጸመባቸው ጥቃት የኢትዮጵያን ግዛት ለቀው የወጡት የደቡብ ሱዳን አማጺ ታጣቂዎች ተመልሰው ወደ ለመግባት በመሰባሰብ ላይ መሆቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የጋምቤላ ክልል ካቢኔ ጉዳዩን ...

Read More »

የአቶ ጌታቸው አሰፋ  ክስ መታየት ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2011)በከባድ የሌብነት ወንጀልና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሌሉበት ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህነንት መስሪያ ቤት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ ዛሬ  ክስ መታየት ጀመረ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ክሳቸው የተሰማው አቶ ጌታቸው አሰፋ በተለያዩ ስውር ቤቶችና በፌደራል መንግስት ስር በሚታወቁ እስር ቤቶች ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ ከባድ ግርፊያ፣ ድብደባና ጥፍር በመንቀል ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲፈጸምባቸው አስደርገዋል ...

Read More »

በቡርጂና በሰገን አካባቢዎች ለአንድ ወር የሚቆይ ወታደራዊ ዕዝ ተቋቋመ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2011)በደቡብ ኢትዮጵያ በአማሮ ልዩ ወረዳ በቡርጂና በሰገን አካባቢዎች ለአንድ ወር የሚቆይ ወታደራዊ ዕዝ መቋቋሙ ተገለጸ። ከኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ጋር የሚዋሰኑት የደቡብ ክልል አካባቢዎች በወታደራዊ ዕዝ ኮማንድ ፖስት ስር እንዲሆኑ የተወሰነው ላለፉት ሁለት ዓመታት በህዝቡ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ለማስቆም መሆኑን የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል። የደቡብ ዕዝ አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ሙዜይ መኮንን ህዝብ ላይ እየተፈጸመ የመጣው ...

Read More »

በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና የልማት ጉባዔ ሊዘጋጅ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 28/2011) የአውሮፓ ህብረት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና የልማት ጉባዔ ሊያዘጋጅ ነው። በሶማሊያ የህብረቱ ጉዳይ ተጠሪ ፉልጀንሺዮ ጋሪዶ ሩዝ እንደገለጹት ከዓለም ባንክና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ጉባዔ በመጪው ሀምሌ በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ የተፈጠረው አዲስ የግንኙነት መስመር ይበልጥ መጠናከር  አለበት የሚል አቋም እንዳለው ነው በህብረቱ የሶማሊያ ልዩ ተጠሪ የገለጹት። በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በሶስቱ ...

Read More »

የብፁዕ ዶክተር አቡነ ገሪማ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን እሁድ ይፈጸማል

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 28/2011) የብፁዕ ዶክተር አቡነ ገሪማ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን እሁድ እንደሚፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃላፊነቶችና ሃይማኖታዊ ተልዕኮዎች ሲያገለግሉ የቆዩት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ህይወታቸው ያለፈው በትላንትናው እለት ነው። በእምነቱ ከፍተኛ መለኮታዊ የትምህርት ደረጃ ላይ በመድረስ ከሚጠቀሱ አባቶች አንዱ የሆኑት ዶክተር አቡነ ገሪማ ከ፵ዓመታት በላይ ቤተክርስቲያኒቱን ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችሏል። ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ እስካለፈው ሰኞ ሚያዝያ ...

Read More »

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለህክምና ባለሙያዎች ምላሽ ሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 28/2011)በጠቅላይ ሚኒስትሩና በህክምና ባለሙያዎች ባለፈው ቅዳሜ የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ምላሽ ሰጠ። በህክምና ባለሙያዎቹ ለተነሱት ጥያቄዎች መፍትሄ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉንም አስታወቋሎ። የህክምና ባለሙያዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት በተመለከተ ቅሬታ ማቅረባቸው ታውቋል። በውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገቢው መንገድ አላስተናገዱንም ብለዋል አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎች። ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጥያቄዎቹን እየመለስኩ ነው የተቀሩትንም ግብረሃይል ተቋቁሞ በመስራት ላይ ነው ሲል ዛሬ ...

Read More »

በአፋርና ሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት በውይይት እንዲፈታ ተጠየቀ  

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 28/2011) በአፋርና ሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት በውይይት እንዲፈታ ሁለቱም ወገኖች ጥረት እንዲያደርጉ ተጠየቀ። የሶማሌ ክልል ካቢኔ ባለፈው ዓርብ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የተፈጠረው ውዝግብ መካረሩን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተፈጠረውን ግጭት ለማስወገድ በሳምንቱ መጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሁለቱንም ወገኖች ማነጋገራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሶማሌና አፋር ክልሎች መካከል የከረሩ ቃላት ልውውጡ ወደ ግጭት አምርቶ አካባቢው ዳግም ውጥረት ...

Read More »

የመንግስት አመራሮች ተፈናቃዮችን ለፖለቲካዊ ፍላጎታቸው ማስፈጸሚያ እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ተገለጸ 

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 28/2011) በአንዳንድ ክልሎች የመንግስት አመራሮች ተፈናቃዮችን ለፖለቲካዊ ፍላጎታቸው ማስፈጸሚያ እየተጠቀሙባቸው መሆኑን ፌደራል መንግስቱ አስታወቀ። በመጠለያ ጣቢያዎች ተፈናቃዮችን እስከማገት የሚደርሱ የክልል አመራሮች መኖራቸውን ባለፈው ዓርብ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  በቀረበው ሪፖርት ላይ  ተመልክቷል። የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የትኛውንም ዋጋ ከፍለን የዜጎችን ስቃይ ለማስቆም ወስነናል ብለዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ዓርብ እለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት ተቋቁሞ ወደተለያዩ አካባቢዎች የተሰማራን ግብረ ...

Read More »