Author Archives: Central

ዜጎች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መፍለሳቸውን ቀጥለዋል

ሚያዚያ ፲፱(አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙና በምእራባውያን የአኗኗር ዘዴ የሚኖሩ ጥቂት ግለሰቦች የመኖራቸውን ያክል፣ ተገኘ የሚባለው የኢኮኖሚ እድገት የዘለላቸው ወይም ፈጽሞ ያላያቸው እጅግ በርካታ ዜጎች ስደትን እንደአማራጭ በመውሰድ ባህር እና በረሃ አቋርጠው ወደ አረብ አገራት ወይም ወደ አውሮፓና አሜሪካ ሲሰደዱ ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ጉልበቱ የሌላቸው አቅመ ደካሞች ደግሞ ወደ ዋና ዋና የክልል ...

Read More »

በአዲስ አበባ ስራቸውን የሚለቁ ፖሊሶች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሮአል

ሚያዚያ ፲፱(አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሚሰሩት ስራ ክብደት አንጻር የሚከፈላቸው ክፍያ ህይወታቸውን በአግባቡ ለመምራት እንዳላስቻላቸው የሚናገሩት ፖሊሶች፣ በገዢው ፓርቲ በኩል መፍትሄ ባለማግኘታቸው ስራቸውን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። የፖሊስ እጥረት ያጋጠመው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቅጥር ማስታወቂያ ቢያወጣም የሚመዘገብለት ሰው አላገኘም። አንድ ፖሊስ ለኢሳት ወኪል ሲናገር፣ ከእርሱ ጋር ሰልጥነው ከተቀጠሩት ከ2 ሺ 300 ፖሊሶች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ...

Read More »

ሰመጉ በጋምቤላ ለጠፋው የሰው ህይወትና ለወደመው ንብረት መንግስትን ተጠያቄ አደረገ

ሚያዚያ ፲፱(አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባወጣው ጋዜጣው መግለጫ፣ ከ200 በላይ ንጹሃን ዜጎች ለተገደሉበት ከ100 በላይ ዜጎች ለቆሰሉበትና በርካታ ህጻናትና ሴቶች ተጠልፈው ለተወሰዱበት ድርጊት ፣ መንግስትን ግንባር ቀደም ተጠያቂ አድርጓል። ከደቡብ ሱዳን የሚመጡ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ግድያና ዝርፊያ እየፈጸሙ መሆኑ እየታወቀ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ራሳቸውንና ንብረታቸውን የሚከላከሉበትን መሳሪአ በመንግስት እንዲፈቱ መደረጉ አንድ ጥፋት መሆኑን ...

Read More »

በአዲስ አበባ አንድ በመሰራት ላይ ያለ ህንጻ ተደረመሰ

ሚያዚያ ፲፱(አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ጠዋት አያት ሰሚት አካባቢ ሞሃ ለስላሳ ፋብሪካ አጠገብ በመገንባት ላይ ያለ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ የተደረመሰ ሲሆን፣ በህንፃው ውስጥ የዳሽን እና አቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፎች ይገኙበት እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡ አደጋው በስራ ሰአት ቢከሰት ኖሮ በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችል እንደነበር የገለጸው ዘጋቢያችን፣ አደጋው በየቀበሌው ያለው የግንባታ ቁጥጥር መስሪያ ቤት ...

Read More »

አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ሶስት ሰዎች በቂሊንጦ ምንነቱ ያልታወቀ መድሃኒት እንድንውጥ ተጠየቅን አሉ

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ የሽብርተኛ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመራርና ሌሎች ሶስት አባላት በቂሊንጦ እስር ቤት የማያውቁትን መድሃኒት እንዲውጡ መጠየቃቸውን ማክሰኞ ለችሎት ገለጹ። በእስር ቤቱ የቀረበላቸውን መድሃኒት አንውጥም በማለታቸውም ከሌሎች ተከሳሾች ተለይተው ለብቻቸው ለአራት ቀን ያህል በጨለማ ክፍል ውስጥ መቆየታቸውን የፓርቲ አመራት የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ለፍርድ ቤት አስረድተዋል። የፓርቲው አመራርን ጨምሮ ...

Read More »

በጋምቤላ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎች እየታሰሩ ነው

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) በቅርቡ በጋምቤላ ክልል የተፈጸመን ግድያ በማውገዝ በጋምቤላ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍን ያካሄዱ ነዋሪዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየታሰሩ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ፎቶግራፍ አንስታችኋል እንዲሁም ሰልፉን አስተባብራችኋል የተባሉ ነዋሪዎች  ቤት ለቤት በመካሄድ ላይ ባለ የእስር ዘመቻ ሰለባ መሆናቸውን እማኞች ገልጸዋል። የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን እየገለጹ ያሉት ነዋሪዎች ከሰልፉ ጀርባ ...

Read More »

ዴቪድ ካሜሩን ኢትዮጵያን ያልጎበኙበት ምክንያት አልታወቀም

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) የብሪታኒያው ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በመጋቢት ወር በኢትዮጵያ ያደርጉታል የተባለው ጉብኝት ከአንድ ወር በላይ ሳይካሄድ የቀረበት ምክንያት ሳይታወቅ ቀጥሏል። ሁለም መንግስታት ጉብኝቱ ስለቀረበት ምክንያት የሰጡት መግለጫ የለም። የብሪታኒያው ጠ/ሚ/ር ዴቢድ ካሜሩን፣ በመጪው ሰኔ ወር በኬንያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ በጥር ወር ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ ይኸው የኬንያ ጉብኝት በታቀደው ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ይፋዊ መረጃዎች አመልክተዋል። የብሪታኒያው ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን፣ ...

Read More »

በጋምቤላ የተከሰተው ግጭት የግብረሰናይ ድርጅቶችን ስራ አውኳል ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) ሁለት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በመኪና ተገጭተው መሞታቸውን ተከትሎ፣ በጋምቤላ ከተማ የቀጠለው ግጭት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የሌሎች ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ እያወከ መገኘቱ ታወቀ። የደቡብ ሱዳን ኑዌር ተወላጆች ከካምፕ ወጥተው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያደረሱት ጥቃት ለመበቀል የተንቀሳቀሱት ወገኖች፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ንብረቶች ላይ ጭምር ጥቃት ማድረሳቸው ተመልክቷል። አክሽን አጌንስት ሃንገር (ACF) የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሾፌር ሁለት የኑዌር ...

Read More »

ሃረር ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ ተወጥራ ዋለች

ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ 2 ሺ በላይ ቤቶችን ለማፍረስ በዝግጅት ጋር ያለው የክልሉ መንግስት፣ ዛሬ ከህዝብ ጋር ተፋጦ መዋሉን ወኪላችን ገልጿል። ህዝቡ “ከ10 አመታት በፊት ቤቶችን ስንሰራ ዝም ብላችሁ አሁን ለምን እርምጃ ለመውሰድ ተነሳችሁ? በክረምት ቤተሰቦቻችንን ሜዳ ላይ መበተን ሰብአዊነት ነው ወይ? ለምን ቤቶቹን ህጋዊ አታደርጉልንም?” የሚሉ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ የቆዬ ቢሆንም፣ መልስ ሊያገኝ አልቻለም። ...

Read More »

የደቡብ ኦሞ መምህራን ያነሱዋቸው አገራዊ ጥያቄዎች ባለስልጣናቱን አስቆጡ

ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም የጸረ ሙስና ጥምረት በሚል ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ቦዲ ፣ የ8 ወረዳዎች ጸረ-ሙስና ኮሚሺነሮች፣ የሃይማሮት ተቋማት ተወካዮች፣ የእድር አመራሮች፣ የመምህራን ማህበራት፣ የንግድ ማህበረሰብ ማህበር ተወካዮች፣ የሴቶችና ወጣቶች ፎረም እንዲሁም የደኢህዴን ተወካዮች በተገኙበት በተካሄደው ስብሰባ መምህራንና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች በርካታ አገራዊ ጥያቄዎችን አንስተዋል። የንግዱ ማህበረሰብ ተወካይ ...

Read More »