ኢሳት (ጥቅምት 22 ፥ 2009) በኦሮሞና አማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳስቦኛል ስትል ኖርዌይ ስጋቷል ገለጸች። የአውሮፓ አጋር የሆነችው ኢትዮጵያ በፖለቲካ አለመረጋጋት ስትሰቃይ ማየት በጣም ያሳስባል በማለት የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ፈጣን የፖለቲካ ማሻሻያ ሳይውል ሳያድር መውሰድ ይኖርበታል ያሉት የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ቦርግ ብሬንዴ (Borge Brende) ፣ በአገሪቷ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታም ...
Read More »Author Archives: Central
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 22 ፥ 2009) በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቅሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ መንግስታዊ ባልሆኑ መስሪያ ቤቶች በሚሰሩ የዕርዳታ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሰራተኞቹ የወደፊት ስራ ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አለመታወቁም ተገልጿል። የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ድርጅቶችን ጨምሮ በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ እነዚህ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግስት ...
Read More »በጢስ አባይ ከተማ ወታደሮች አንድ የጎበዝ አለቃና ሁለት ሴቶችን ገደሉ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ የተኩስ ድምጽ ያልተለያት የምእራብ ጎጃሟ ጢስ አባይ ከተማ ዛሬ ቀን ላይ ሶስት ነዋሪዎቿ ተገድለውባታል። ከዚህ ቀደም በሁለት የደህንነት አባላት ላይ ተኩሷል በሚል ሲፈለግ የነበረውን ታፈረ ቢሻው የተባለውን አርሶ አደር ለመያዝ ሙከራ ያደረጉ ወታደሮች ሁለት ሴት ልጆችን ሲገድሉ፣ አርሶአደሩም አንድ የፌደራል ፖሊስ ገድሎ አምልጧል። በዚህ የተበሳጩት ...
Read More »ኢህአዴግ ህዝብን ያረጋጋልኛል ያለውን ሹመት ሰጠ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብዙዎች ሹመቱ ምንም ለውጥ የማያመጣ ነው ሲሉ ተችተውታል። በመላው አገሪቱ የሚታየው የለውጥ ፍላጎት ያስደነገጠው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ህዝቡን ያረጋጋልኝ ይሆናል ያለውን እርምጃ ሚኒስትሮችን በመሾም ጀምሯል። የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር የነበሩት ጌታቸው ረዳ በተሾሙ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከስልጣን በመነሳት የመጀመሪያው ሚኒስትር ሲሆኑ ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቴዎድሮስ አድሃኖም በዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ተተክተዋል። ...
Read More »ንግድ ባንክ ከአማራ ክልል ተፈናቀሉ ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች ገንዘብ ሊሰጥ ነው
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከክልሉ ተፈናቅለዋል ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች የሚደረገው የገንዘብ መዋጮ ወደ ባንኮችም ተሸጋግሮ ንግድ ባንክ፣ 5 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመስጠት መዘጋጀቱን የባንኩ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ የፊታችን ሃሙስ መቀሌ ላይ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ገንዘቡን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የባንኩ የሩብ አመት ...
Read More »በሎጊያ ከተማ የንግድ ሱቆች ከታሸጉ ከሁለት ሳምንት በላይ አለፋቸው
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ በርካታ የንግድ ሱቆች የታሸጉ ሲሆን፣ ነጋዴዎች ሱቆቻቸው እንዲከፈቱላቸው ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም። እጅግ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነጋዴዎች ለቫት እንዲመዘገቡ መጠየቃቸውና ነጋዴዎቹ ገቢያቸው አነስተኛ መሆኑን በመጥቀስ ትእዛዙን ለመቀበል ተቸግረው ቆይተዋል። የከተማው መዘጋጃ ሱቆችን በጅምላ ያሸገ ሲሆን፣ ነጋዴዎች ከሁለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ ስራ ፈትተው ተቀምጠዋል።
Read More »በኢትዮጵያ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አንድ ሺህ ያህል ሰው መገደሉን የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ አስታወቀ
ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009) ለአንድ አመት ያህል በዘለቀውና በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በቀጠለው ግድያ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አንድ ሺህ ያህል ሰው መገደሉን የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ አስታወቀ። ድርጅቱ ዕሁድ ጥቅምት 20 ቀን 2009 እንዳስታወቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 1ሺ ሲደርስ 40ሺ ሰዎች ደግሞ ታስረዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኦሮሚያ ክልል ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ...
Read More »ሲራጅ ፈርጌሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ የታሰሩትን ሰዎች ቁጥር ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደሉም
ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎችን ቁጥር ለመግለጽ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተዘገበ። የኮማንድ ፖስቱ ዋና ጸሃፊ ተደርገው የተሰየሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ዕሁድ በሰጡት መግለጫ፣ 2ሺህ ሰዎች ምክር ተሰጥቷቸው ተለቀዋል ቢሉም የታሰሩትን ቁጥር ለመገለጽ ግን ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተመልክቷል። በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ ...
Read More »አዲስ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እድገትና ብልጽግናን የሚያመጣ የፌዴራል ስርዓት መገንባት ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታወቀ
ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009) በአራት የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እድገትና ብልጽግናን የሚያመጣ የፌዴራል ስርዓት መገንባት ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታወቀ። በሃገራዊ ንቅናቄው የምስረታው ስነስርዓት ላይ ያወጣው የጋራ መግለጫ እንደሚያመለክተው ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው የተከበረባትና ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መመስረት የህብረቱ ዋነኛ ዓላም መሆኑ ታውቋል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ በአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በአፋር ህዝብ ፓርቲ፣ እና በሲዳማ ህዝቦች ዴሞክራሲያው ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቱሪዝም ዘርፍን ክፉኛ እየጎዳው እንደሆነ ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009) በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቱሪዝም ዘርፉን ክፉኛ እየጎዳው እንደሆነ መንግስት አስታወቀ። ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ በተጠራ ስብሰባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ የቱሪስቶች ፍልሰት ክፉኛ እንደተስተጓጎለና ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ ቱሪስቶች ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ቱሪስቶች ከፍተኛ ...
Read More »