በሎጊያ ከተማ የንግድ ሱቆች ከታሸጉ ከሁለት ሳምንት በላይ አለፋቸው

ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ በርካታ የንግድ ሱቆች የታሸጉ ሲሆን፣ ነጋዴዎች ሱቆቻቸው እንዲከፈቱላቸው ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም። እጅግ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነጋዴዎች ለቫት እንዲመዘገቡ መጠየቃቸውና ነጋዴዎቹ ገቢያቸው አነስተኛ መሆኑን በመጥቀስ ትእዛዙን ለመቀበል ተቸግረው ቆይተዋል። የከተማው መዘጋጃ ሱቆችን በጅምላ ያሸገ ሲሆን፣ ነጋዴዎች ከሁለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ ስራ ፈትተው ተቀምጠዋል።