Author Archives: Central

በአማራ ክልል የተሰጡት የ10ኛና የ12 ኛ ክፍል ፈተናዎች በርካታ ችግሮች ነበሩባቸው ተባለ

ሰኔ ፮ (ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዚህ አመት የተሰጡት የ10ኛና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎች የዓመተ ምሕረት መቀላቀል፣ የፈተና መለያ ኮድ መዘበራረቅና የጥያቄ መጉደል ታይቶባቸዋል። ወኪላችን ስማቸውና ድምጻቸው እንዳይተላለፍ የጠየቁ ተማሪዎችና ምሁራን በመጥቀስ እንደዘገበችው ወደ አማራ ክልል በተላኩ የ10ኛ ክፍል የመፈተኛ ወረቀቶች ላይ ጉልህ የሆኑ ስህተቶች ተከስተዋል። በመጀመሪያው ቀን የተከሰተው ስህተት ተማሪዎች በድንጋጤ ቀሪዎችን ፈተናዎች ተረጋግተው እንዳይፈተኑ እንዳደረጋቸው ...

Read More »

ካለፉት 6 ወራት ወዲህ በደሴ ከተማ የተከሰተው የውሃ እጥረት ተባብሷል

ሰኔ ፮ (ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የደሴ ከተማ ካለፉት ስድስት ወራት ጀምሮ በከፍተኛ የመጠጥ ውሃ እጥረት መቸገሯን የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ለውሃ ስርጭቱ መቋረጥ የመብራት እጥረት መፈጠሩን መስተዳድሩ በምክንያትነት ይጠቅሳል። ነዋሪዎች አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ አስር ብር ለመግዛት ተገደዋል። ለተጨማሪ ወጪዎች ከመዳረጋቸው በተጨማሪ የምንጭ ውሃ በአምራጭነት በመጠቀማቸው ለውሃ ወለድ በሽታዎች መጋለጣቸውን ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 በሳምንቱ መጨረሻ በርካታ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ

ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ በሰሜን ጎንደርና በአዲስ አበባ የተለያዩ ጥቃቶችን ፈጽሟል። በሰሜን ጎንደር አንድ የሱዳን ተሳቢ የፈሳሽ መጫኛ መኪና ከሱዳን ተነስቶ በመተማ መንገድ በማለፍ ጣራገዳም ተራራን ጨርሶ አዲስ ዘመን ከተማ ለመግባት 2 ኪሎ ሜትሮች ሲቀረው የንቅናቄው ታጋዮች በወሰዱት ጥቃት የመኪናው ሹፌር እና የመኪናው ጎማ እንደተመታ ተሳቢውንና መኪናው ለየብቻ መውደቃቸውን ...

Read More »

በቲሊሊ የፖሊስ አባላት እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው

ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በአዊ ዞን ቲሊሊ ከተማ የፖሊስ አዛዥ የሆነው ኮማንደር አወቀን ጨምሮ አንድ የፖሊስ መኮንንና ሌላ አንድ የወረዳ የካቢኔ አባል ታስረዋል። አንዳንድ ፖሊሶቹ የታሰሩት ባለፈው አርብ ከሰአት በሁዋላ ስብሰባ ጨርሰው ከወጡ በሁዋላ በቤታቸው ውስጥ ሲሆን፣ ኮማንደር አወቀ ደግሞ ስራ ቦታው ላይ መያዙን ታውቋል። የፖሊስ አባላት መስራት ያለባቸው ለአማራ ...

Read More »

መሬታችንን አንሰጥም ያሉ የደቡብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደሮች በጅምላ እየታሰሩ ነው

ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ካለምንም ምትክ ቦታና ካሳ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን እና የግጦሽ ማሳዎችን በልማት ስም መነጠቃቸውን የተቃወሙት አርብቶ አደሮች በገፍ ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቀዋል። በኩራዝ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የሃመር፣ ጸሚያ፣ ዳሰነች፣ ናያቶም፣ ሙርሲ፣ ኤርቦሬ፣ ማና ብሄረሰብ አባላት የግፍ እስራቱ ተጠቂዎች ሆነዋል። በዞኑ በሚገኙ የወረዳ እስርቤቶችና ...

Read More »

ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ለሦስተኛ ጊዜ ተቃጠለ ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮልፈ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ካራቆሬ በሚባለው አካባቢ ዘይት ቤት በመባል በሚጠራው ግቢ የሚገኘው ‹‹ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ›› ከጥቅምት 05/09 ጀምሮ እስከ ሰኔ 3 ቀን 20099 ዓ.ም ድረስ ባሉት 9 ወራት ለሦስተኛ ጊዜ መቃጠሉን ዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 8 ሰዓት ...

Read More »

በቆሼ አደጋ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸው ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ተጓትቶብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ

ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ደርሶ ከነበረው የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ጋር በተገናኘ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸው ከ20 በላይ ሰዎች ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ተጓትቶብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ 23 የሚሆኑት ሰዎች በስፍራው ይኖሩ ስለመሆናቸው አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው እንዲመጡ መታዘዛቸውን ገልጿል። ከአደጋው የተረፉት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች ጉዳቱ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ተመድ የእርዳታ ምግብ አቅርቦት በተያዘው ወር ሊያልቅ ይችላል ሲል የሰጠውን ማሳሰቢያ አስተባበለች

ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሃገሪቱ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የተጋለጡ ወደ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች የሚያስፈልጋቸው የምግብ አቅርቦት በተያዘው ወር ሊያልቅ ይችላል ሲል የሰጠውን ማሳሰቢያ አስተባበለች። አለም አቀፍ ተቋማትና የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም ተረጂዎች ከሰኔ ወር መገባደጃ ጀምሮ የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ እንደማይኖር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። ይሁንና በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽን የሰጡ የመንግስት ባለስልጣናት በችግሩ ምክንያት ...

Read More »

የቂሊንጦ እስር ቤት አቃጥለዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው ታሳሪዎች የክስ ቻርጁን ወደ ዳኞችና አቃቢያነ ህጎች ወረወሩ

ኢሳት (ሰኔ 5 ፥ 2009) ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በማቃጠል ጉዳት አድርሰዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች የታደላቸውን ክስ ቻርጅ ወደ ጃኞቹና አቃቢያነ ህጎቹ በመወርወር እንዲሁም በድምፅ ተቃውሟቸውን ማቅረባቸው ተገለጸ። ፍ/ቤቱም ሁኔታውን ተከትሎ የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል። የፍርድ ውሳኔው የተላለፈባቸው ተከሳሾች በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ጋር በተገናኘ ተደራራቢ ክስ ተመስርቶባቸው ከነበሩ 121 እስረኞች መካከል መሆናቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ሰሞኑን ...

Read More »

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ስራአስኪያጅ አባ ሃይለማርያም የመመረቂያ ጽሁፋቸውን ከሌላ ተማሪ ጽሁፍ ገልብጠው የዶክትሬት ዲግሪ እንዳገኙ ተጋለጠ

ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ፣ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የስራ አስፈጻሚ አባልና በቅርቡ ደግሞ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት “ዕጩ ቆሞስ” ኾነው የተሾሙት አባ ሃይለማርያም መለሰ ፣ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 ለደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ባቀረቡት የዶክትሬት የመመረቂያ ጽሀፍ ላይ ፣ ከዚህ ቀደም በአንድ ኢትዮጵያዊ ቄስ የተጻፈውን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ...

Read More »