(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 15/2010) በኬንያ ሀሙስ ለማካሄድ የታቀደው ምርጫ በእቅዱ መሰረት የሚካሄድ መሆኑ ታወቀ። ምርጫው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው ማመልከቻ ከሰባቱ ዳኞች ሁለቱ ብቻ በመገኘታቸው ሳይታይ መቅረቱ ታውቋል። ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ምርጫውን ለማደናቀፍ ጠርተውት የነበረውን የሰላማዊ ሰልፍ እቅድ በመሰረዝ ደጋፊዎቻቸው ቤት በመዋል ቀኑን እንዲያሳልፉ መክረዋል። በኬንያ ሀሙስ በድጋሚ እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በተወሰነለት ...
Read More »Author Archives: Central
የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከአፍሪካ የመጨረሻዎቹ አምስት ሀገራት ውስጥ ተመደበ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 15/2010)የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከአፍሪካ የመጨረሻዎቹ አምስት ውስጥ ሲመደብ ከአለም ደግሞ 185ኛ በመሆን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘቱን ፓስፖርት ኢንዴክስ ይፋ ያደረገው አዲስ ሪፖርት አስታወቀ። የሀገራትን የጉዞ ሰነድ ወይንም ፓስፖርት ጥንካሬ የሚገመግመው ፓስፖርት ኢንዴክስ ይፋ ባደረገው በዚህ አዲስ ጥናት ከአለም ሲንጋፖር ቀዳሚ ሆና ስታልፍ ከአፍሪካ ሲሸልስ የመሪነቱን ቦታ ይዛለች። የየሀገራቱን ፓስፖርት በመያዝ ያለቪዛና አየር ማረፊያ ሲደርሱ በሚመታ ቪዛ በአለም ላይ ወደ ...
Read More »በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ሁለት እስረኞች በድብደባ ሕይወታቸው አለፈ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 15/2010)በቂሊንጦ ወህኒ ቤት የሚገኙ ሁለት እስረኞች በድብደባ ሕይወታቸው ማለፉን የሟቾቹ አባሪዎች ዛሬ ለፍርድ ቤት አስታወቁ። ከሟቾቹ አንዱ ለደህንነቴ እሰጋለሁ እስር ቤት ይቀየርልኝ ብሎ ለፍርድ ቤት ካመልከተ በኋላ መገደሉም ይፋ ሆኗል። በድብደባ ሕይወታቸው ያለፈው አለማዬ ዋቄ ማሞና መሀመድ ጫኔ የተባሉ እስረኞች ሲሆኑ የቂሊንጦ ወህኒ ቤትን በማቃጠል ተወንጅለው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት በመከታተል ላይ እንደነበሩም ታውቋል። ዛሬ ጥቅምት 15/2010 አዲስ አበባ ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የመንግስት ቃል አቀባይን ተቹ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 15/2010)የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የመንግስት ቃል አቀባዩን ተቹ:: ቃል አቀባዩ ነገሬ ሌንጮ በተሳሳተ መልኩ መረጃ ያቀረቡ የመገናኛ ብዙሃንን ላይ ህግን መሰረት በማድረግ እርምጃ ይወሰዳል በማለት የሰጡትንም መግለጫ የግላቸውን እንጂ የመንግስት አቋም አይደለም ሲሉ አጣጥለውታል። ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዘርአይ ጨምረውም በብሮድካስት ሚዲያው ላይ የሚታይ አደገኛ አዝማማሚያ መኖሩንም ጠቁመዋል። የህወሃት ነባር ታጋይና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ...
Read More »በኬንያ ምርጫው ወደ ሌላ ጊዜ እንዲሸጋገር ተጠየቀ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 14/2010) በኬንያ ሀሙስ በድጋሚ ሊደረግ የታሰበውን ምርጫ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምርጫውን ወደ ሌላ ጊዜ እንዲያሸጋግር ተጠየቀ። ፍርድ ቤቱ በሶስት ኬንያውያን የቀረበውን ይህን ሀሳብ ነገ ያያል ተብሎም ይጠበቃል። በስልጣን ላይ ያሉት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ደግሞ ምርጫው በተወሰነለት ጊዜ እንዲካሄድ በመወትወት ላይ መሆናቸው ታውቋል። በኬንያ ሀሙስ ሊደረግ የታሰበው ምርጫ ተአማኒነት ላይኖረው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት ባለበት በዚህ ወቅት ...
Read More »የኦዴግ አመራሮች ወደ ሱዳን ካርቱም ለኤክስፐርቶች በተዘጋጀው መድረክ ላይ ለመሳተፍ እንደሄዱ ገለጹ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 14/2010) የኦዴግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶክተር ዲማ ነገዎ ወደ ሱዳን ካርቱም ያመሩት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመደራደር ሳይሆን የአፍሪካ ሕብረት ባቀረበላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑን አረጋገጡ። አመራሮቹ በተለይ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ህብረቱ ግብዣውን ያደረገላቸው በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያደረጉትን ጥናት መነሻ በማድረግ በሱዳን ካርቱም ለኤክስፐርቶች በተዘጋጀው መድረክ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሚስጥር በሱዳን ...
Read More »የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ውሳኔ እንዲመረመር ተጠየቀ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 14/2010)ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ተላላፊ ያለሆኑ በሽታዎች የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርገው ከሾሙ በኋላ ያነሱበት ሂደት እንዲጣራ የተባበሩት መንግስታት ጉዳይ ተመልካች ድርጅት ጠየቀ። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ተመልካች ድርጅቱ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን ተመልክተው ሹመቱን ቢያነሱም ሞራለቢስ ውሳኔያቸው ግን ሊመረመር ይገባል ብሏል። ሮበርት ሙጋቤ በአለም ጤና ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የበጎ ...
Read More »ኢህአዴግ እያለቀለት መሆኑን የቀድሞው የሕወሃት አመራር አባል ገለጹ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 14/2010) በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንና ኢህአዴግም እያለቀለት መሆኑን የቀድሞው የሕወሃት አመራር አባል አቶ ገብሩ አስራት ገለጹ። ኢህአዴግ እየገዛ ያለው በደህንነቱና በሰራዊቱ አማካኝነት እንደሆነም ተናግረዋል። ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ የገለጹት አቶ ገብሩ አስራት ኢትዮጵያ ትፈራርሳለች የሚለው ሟርት ግን ተቀባይነት የለውም ብለዋል። እስከ 1993 የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት ሀገር ውስጥ ...
Read More »በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ካርታ በሚመለከተው አካል ያልጸደቀ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 13/2010) በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ካርታ በሚመለከተው አካል ያልጸደቀ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። ካርታው ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች ብቻ ስራ ላይ ሊውል እንደሚችልም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ለሶስተኛ ጊዜ የተሳሳተ የኢትዮጵያ ካርታ መጠቀሙን በማመን ይቅርታ በጠየቀበት ዘገባ በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ካርታ በሚመለከተው አካል ያልጸደቀ እንደሆነ የኢትዮጵያ ካርታ ስራዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሱልጣን መሐመድ አስታውቀዋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሱልጣን ...
Read More »በኦሮሚያ ኢሊባቦር በጮራ ወረዳ ቦሮ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች መገደላቸው ተሰማ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 13/2010) በኦሮሚያ ኢሊባቦር በጮራ ወረዳ ቦሮ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች መገደላቸውንና መፈናቀላቸውን የኢሳት የአካባቢው ምንጮች ገለጹ። በአካባቢው የሚኖሩ አማሮች ቤታቸው ተቃጥሎ፣ንብረታቸው ወድሞ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። የሚሸሹበት መንገድ ስለተዘጋባቸውም ሕጻናትና ሴቶች እንዲሁም ሽማግሌዎች በረሃብና በጥም እየተሰቃዩ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በሕወሃት መራሹ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ምክንያት የብሔር ግጭትን ማራገብ ከተጀመረ 26 አመታት ተቆጥሯል። በዚሁ የጎሳ ፖለቲካ ምክንያት በርካታ ...
Read More »