Author Archives: Central

የአጫሉ ሁንዴሳ የሙዚቃ ኮንሰርት ተሰረዘ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) ታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አጫሉ ሁንዴሳ በጊዮን ሆቴል ያዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ተሰረዘ። የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጉዳዩ በሰጠው ምላሽ የሙዚቃ ኮንሰርቱ የተሰረዘው በጸጥታ ችግር ምክንያት መሆኑን አመልክቷል። ታዋቂው ድምጻዊ አጫሉ ሁንዴሳ በግዮን ሆቴል ሊያካሂድ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት መሰረዝ በርካታ ኢትዮጵያንን ያስቆጣ ሆኗል። የመንግስታትን ርምጃ በመቃወም በማህበራዊ ድረገጾች ከፍተኛ ትችቶች እየቀረቡ መሆናቸው ታውቋል። በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ በሆኑ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ...

Read More »

በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተሰጠ 

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) የፌደራሉ አቃቢ ህግ በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ ተጨማሪ ምስክሮችን ማቅረብ ባለመቻሉና በቀረቡት ማስረጃዎች ውሳኔ እንዲሰጠው በመጠየቁ ችሎቱ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ። በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ የቀረቡት ምስክሮች ከቤታቸው ጽሁፎች ሲወሰዱ ማየታቸውን ከመግለጽ ውጪ ስለጽሁፎቹ ይዘትም ሆነ በሌላ ጉዳይ ላይ የሰጡት ምስክርነት አለመኖሩ ተገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ዶክተር መረራ ጉዲና በብይን በነጻ የመፈታታቸው ጉዳይ የሰፋ መሆኑን አንድ የህግ ...

Read More »

በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃውሞ ተካሄደ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 26/2010) በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ። በአጋሮ ተማሪዎች አደባባይ ወተው የህወሀትን መንግስት አውግዘዋል። በባሌ ሮቤ መምህራን ተቃውሞ አሰምተዋል። በቦረና ዞን የሰላማዊ ሰው ግድያ እንዲቆም በመጠየቅ ሰልፍ ተደርጓል። በሀረር እስር ቤት በተነሳ ቃጠሎ በርካታ እስረኞች መጎዳታቸው ታውቋል። በሌላ በኩል በደቡብ ኦሞ በሙርሲ ታጣቂዎች 13 ሰዎች መገደላቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በኦሮሚያ ክልል ዛሬም የህዝብ ንቅናቄ በበርካታ ...

Read More »

ዜግነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ጎብኚ ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) በኢትዮጵያ አፋር ክልል ማንነታቸውና ዜግነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ጎብኚ ተገደሉ። ጎብኚውን ሲያዘዋውር የነበርው ሹፌርም መገደሉ ታውቋል። የኢሳት ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ዛሬ በአፋር ክልል ኤርታሌ በተባለው ወረዳ የተገደሉት ጎብኚ ወደ ኤርታሌ እሳተ ጎመራ በመጓዝ ላይ ነበሩ። ወደ አካባቢው ሰርገው የገቡት ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ከጎብኚው አጃቢዎችና ከአካባቢው ሃይሎች ጋር መጋጨታቸውም ታውቋል። ጎብኚው የተገደሉት በተኩስ ልውውጥ ይሁን አልያም ሆን ተብሎ ግን ...

Read More »

አሊ አብደላ ሳልህ ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳልህ ተገደሉ። ሳላህ የተገደሉት በሰነአ በመኪናቸው ላይ በተከፈተ ጥቃት ነው። የሃውቲ አማጽያን መሪ ሳላህ ከጠላት ጋር በማበር የሲቪሎችን ሕይወት በማጥፋታቸው ጥቃቱ ተፈጽሞባቸዋል ሲል መግለጫ ሰጥቷል። የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በሀገሪቱ መዲና ሰነአ በመኪናቸው ላይ በተከፈተ ጥቃት መገደላቸውን አልጀዚራ በሃውቲ ቁጥጥር ስር ያለን የሀገር ውስጥ ሬዲዮ ጠቅሶ ዘግቧል። በማህበራዊ ድረገጾች በተለቀቀ ...

Read More »

የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ወደ ሃዋሳና አዲስ አበባ እየሄዱ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010)  በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች አካባቢውን እየለቀቁ ወደ ሃዋሳና አዲስ አበባ እየሄዱ መሆናቸው ተነገረ። በአካባቢው ሃብትና ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ስፍራውን ለመልቀቅ የተገደዱት በጌዲዮ ተወላጅ አመራሮች ጫና እየደረገባቸው በመሆኑ ነው ሲሉ የኢሳት ምንቾች ገጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የአካባቢውን ሕዝብ ሰሞኑን ሰብስበው የጌዲዮ አመራሮችን መውቀሳቸው ተነግሯል። የጌዲዮ ዞን አስተዳደር አመራሮች በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ...

Read More »

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር በወልድያ ባሉ ከተሞች ተሰማራ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) በወልዲያ ትላንት የተጀመረው የህዝብ ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎች መዛመቱን ተከትሎ የህወሃት መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር በየከተሞቹ ማስገባቱ ተገለጸ። በወልዲያ፣ ሀይቅ፣ ቆቦ መውጪያና መግቢያ ላይ በርካታ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን የሚወጣና የሚገባ ተሽከርካሪ እያስቆሙ እንደሚፈትሹ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሀይቅ ከተማ ታግተው ያሉት የሰላም ባስ አውቶቡሶችን ለማስለቀቅ የህወሃት ወታደሮች በሄሊኮፕተር መግባታቸውን ተከትሎም በሀይቅ ከተማ ውጥረት መንገሱ ይነገራል። በትላንቱ ህዝባዊ ...

Read More »

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት የለም አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ የተመረጡት የቀድሞው የኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር የለም ሲሉ አስተባበሉ። አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት አለ ማለት ልጆችን አያ ጅቦ መጣብህ እያሉ እንደማስፈራራት ይቆጠራልም ብለዋል። የአማራና የኦሮሞ ሕዝን እሳትና ጭድ ናቸው በማለት የሚታወቁት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት አለ በሚል የተነዛው የፈጠራ ወሬ አደገኛ ውጤት አስከትሏል ...

Read More »

የሱዳን ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገቡ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የሱዳን ወታደሮች 40 ኪሎ ሜትር ያህል ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ ክልል በመግባት ሰብል ማቃጠላቸውን የኢሳት ምንጮች አጋለጡ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ወታደሮቹ በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ኮርመር እስከሚባል አካባቢ ዘልቀው መግባታቸው ታውቋል። አሰሪ የተባለውን የኢትዮጵያ መሬት መቆጣጠራቸውንም ለማወቅ ተችሏል። የህወሃት መከላከያ ሰራዊት ከባህርዳርና መተማ ተነስቶ ወደ ስፍራው እየተጓዘ መሆኑ ቢታወቅም የመከላከያ ሰራዊቱ አካሄድ ግን ወታደሮቹን ለማስወጣት ይሁን ...

Read More »

አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በመከላከያ ሃይል እንዲጠበቁ ተደረገ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010) በኦሮሚያ ክልል ያሉ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በመከላከያ ሃይል እንዲጠበቁ መደረጉ ተሰማ። የፖሊስ ሃይሉን ገሸሽ ያደረገ ይህ ተግባር ምናልባትም አመጽ እያሰማ ያለውን ህዝብ በሃይል ለማፈን የተቀነባበረ ሴራ መኖሩን እንደሚያሳይ ምንጮች ገልጸዋል። በክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም ግቢዎቻቸውን እየለቀቁ በመውጣት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትላንት በስቲያ በአዳማ ናዝሬት ስኳር ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ በህዝብ ቁጥጥር ...

Read More »