በጉጂ ዞን የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ሜድሮክ ኢትዮጵያ በሻኪሶ አካባቢ ላለፉት 20 አመታት ሲያወጣ የነበረው የወርቅ ማእድን በዜጎች ጤና እና በተፈጥሮ ላይ ያስከተለውን ውድመት በመጥቀስ፣ ኩባንያው ተጨማሪ ፈቃድ እንዳይሰጠው የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን ወደ አደባባይ በመውጣት እየገለጹ ነው። ትናንት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በተለያዩ የዞኑ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን፣ ተቃውሞው ከዚህ ቀደም ይታይ እንደነበረው መንገዶችን በመዝጋት ...
Read More »Author Archives: Central
በሽንሌ ዞን አብዲ ኢሌ ያዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ከሸፈ
በሽንሌ ዞን አብዲ ኢሌ ያዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ከሸፈ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የአቶ አብዲ ኢሌን አገዛዝ በኢትዮ-ሶማሊ ክልል እየፈጸመ ያለውን ግድያ፣ እስርና ሌሎችም ኢ ሰብአዊ ድርጊቶች በመቃወም ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎች ከተካሄዱ በሁዋላ፣ ፕሬዚዳንቱ በሽንሌ ከተማ ያዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ሳይስካለት ቀርቷል። ህዝቡ በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች የሰበሰባቸውንና በመኪና ጭኖ ያመጣቸውን እንዲሁም የልዩ ሃይሉን ሚሊሺያዎች የሲቪል ...
Read More »መንግስት ለሜቴክ የተሰጠውን የማዳበሪያ ፋብሪካ በመቀማት ለአለማቀፍ ጫረታ ሊያቀርብ መሆኑ ተጠቆመ
መንግስት ለሜቴክ የተሰጠውን የማዳበሪያ ፋብሪካ በመቀማት ለአለማቀፍ ጫረታ ሊያቀርብ መሆኑ ተጠቆመ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ብሉምበር የመንግስት ባለስልጣናትን በመጥቀስ እንደዘገበው እርምጃው አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ለመከላከያ ሰራዊት በአድሎ የሚሰጡትን ፕሮጀክቶች ለማምከን የገቡትን ቃል ወደ ተግባር እየለወጡት መሆኑን ማሳያ ነው። የያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት መንግስት በህወሃት ጄኔራሎች ለሚመራው የመከላከያ እና ምህንድስና ተቋም ስራውን ቢሰጥም ፣ ተቋሙ ግን በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ...
Read More »የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ተጫዋቾችና የቡድን መሪ በመሃል ዳኛ እያሱ ፈንቴ ላይ ሜዳ ውስጥ ድብደባ መፈጸማቸውን ተከትሎ የሊጉ ጨዋታ ተቋረጠ
የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ተጫዋቾችና የቡድን መሪ በመሃል ዳኛ እያሱ ፈንቴ ላይ ሜዳ ውስጥ ድብደባ መፈጸማቸውን ተከትሎ የሊጉ ጨዋታ ተቋረጠ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ/ም) በትናትናው እለት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 22ኛው ሳምንት የጫወታ መርሃግብር ከቀኑ 11፡00 ሰዓት መከላከያ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ በአዲስ አበባ ያደረጉት ጫወታ፣ የወልዋሎ ቡድን መሪና ተጫዋቾች በፈጸሙት ድርጊት ምክንያት ጨዋታው ተቋረጠ። ጫወታው በተጀመረ በ22ኛው ...
Read More »የኢሳት 8ኛ አመት በአል በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) በመላው አለም በሚገኙ 50 ከተሞች የተዘጋጀው የኢሳት 8ኛ አመት በአል በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ። በአሜሪካ፣አውሮፓ፣በውስትራሊያእንዲሁም በሩቅ ምስራቅና በመካከለኛው ምስራቅ በአንድ ቀን የተዘጋጀው የኢሳት 8ኛ አመት ክብረ በአል በርካታ እንግዶች በታደሙበት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁም ተመልክቷል። የኢሳት ሶስት ስቱዲዮዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በቀረበበት እንዲሁም የኢሳት 8 አመታት ጉዞ በዘጋቢ ፊልም በቀረበበት በዚህ ዝግጅት ስነ ስርአት ላይ የታደሙት እንግዶች ኢሳት በደረሰበት ...
Read More »በአፍጋኒስታን በተፈጸመ ጥቃት 29 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) በአፍጋኒስታን ርዕሰ መዲና ካቡል አሸባሪዎች ባደረሱት ጥቃት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 29 ሰዎች ተገደሉ። የአፍጋኒስታን የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት እንደገለጹት ከሁለት ተከታታይ ፍንዳታዎች በኋላ ከሞቱት 29 ሰዎች በተጨማሪ 49 ሰዎች ቆስለዋል። አለም አቀፉ የአሸባሪ ቡድን አይሲስ በጥቃቱ ሃላፊነትን ወስዷል። ዛሬ ሰኞ ማለዳ በአፍጋኒስታን ርዕሰ መዲና ካቡል በደረሰው የሽብር ጥቃት የመጀመሪያው ፍንዳታ አንድ ሞተር ቢስክሌት በሚያሽከረክር ግለሰብ በሃገሪቱ የጸጥታ መስሪያ ቤት ...
Read More »የገዛህኝ ነብሮ የቀብር ስነስርአት ብዙዎችን ያስደነቀ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) በደቡብ አፍሪካ ከሃገሪቱ ዜጋ ውጪ ባልተለመደና በደመቀ መልኩ የተከናወነው የገዛህኝ ነብሮ የቀብር ስነስርአት በዙዎችን ያስደነቀ ሆኖ ማለፉ ተገለጸ። የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቴሌቪዥንም ለቀብር ስነስርዓቱ የዜና ሽፋን በመስጠት ኢትዮጵያውያን የማህበረሰብ መሪያቸውን በታላቅ ሀዘን ሸኙት ሲል በዘገባው አስደምጧል። የአክቲቪስት ገዛህኝ ገብረመስቀል ነብሮ የቀብር ስነስርዓት በደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ መሆኑ ተሰምቷል። የቀብር ስነስርዓቱንም የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በልዩ ...
Read More »የሶማሌ ክልል የፍትህ ጥምረት የፖለቲካ ንቅናቄ ተመሰረተ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010)የሶማሌ ክልል የፍትህ ጥምረት የተሰኘ የፖለቲካ ንቅናቄ በይፋ ተመሰረተ። ጥምረቱ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የምስረታ ጉባዔውን አካሂዷል። በሶማሌ ክልል እየተፈጸመ ያለውን መጠነ ሰፊ ጭቆና ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር በመሆን ይታገላል ይላል በይፋ የወጣው የጥምረቱ ጋዜጣዊ መግለጫ። የተበታተነውን የሶማሌ ክልል ተወላጆች ትግል ወደአንድ የተጠናከረ ሃይል በማምጣት ለፍትህና ነጻነት መስፈን ከምንጊዜውም በላይ በአንድነት ለመታገል መዘጋጀቱንም ጥምረቱ አስታውቋል። በሚኒሶታ ሚኒያፖሊስ የሶማሌ ክልል ...
Read More »ከካማሽ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች እየተንገላቱ ናቸው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) ከቤንሻንጉል ጉምዝ አካባቢ ካማሽ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በባህርዳር ቴክኒክና ሙያ ቅጥር ግቢ ሰፍረው እየተንገላቱ መሆናቸው ተነገረ። ሃብት ንብረታቸው ወድሞባቸው ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉት 120 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ከሰው ጋር እንዳይገናኙ ተደርገው እየተጎሳቆሉ ይገኛሉ ተብሏል። የብአዴን አመራሮች ጉዳዩን ከመሻፈፈን ወጭ ስለተፈናቃዮች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተነግሯል። ከቤንሻንጉል ጉምዝ አካባቢ ካማሽ ዞን እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራ ተወላጆች በባህርዳር ቀበሌ 11 ...
Read More »በሻኪሶ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ22/2010) ሜድሮክ የወርቅ ማዕድን በሻኪሶ ስራውን እንዲቀጥል መወሰኑን ተከትሎ በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። በጉጂ ዞን ሻኪሶና ፊንጫ ከተማ ከጠዋት ጀምሮ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። ሜድሮክ ኢትዮጵያ የወርቅ ማእድን የማውጣት ስራውን እንዲያቆም ከተደረገ ከ1 ዓመት በኋላ በድጋሚ ፈቃድ በማግኘቱ የአካባቢው ህዝብ በተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል። ተቃዋሚዎች ከፌደራል ፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው በፊንጫ እስካሁን 3 ሰዎች በአስለቃሽ ጭስ ተጎድተው ...
Read More »