የሶማሊ ልዩ ሃይል ሚሊሺያዎች በአሮምያ ክልል አዋሳኝ ከተሞች በመግባት ጥቃት ፈጸሙ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ-ሶማሊ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ ፐሬዚዳንት አቶ አብዲ አሌ ሚሊሺያዎችን ወደ ጭናክስን በመላክ ቢያስን 4 ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል። ከ100 ያላነሱ ሰዎች አካባቢውን ጥለው ሲሸሹ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ደግሞ መቃጠላቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው አቶ አብዲ አሌ የፌደራል ...
Read More »Author Archives: Central
የጅማ ከተማ ህዝብ በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጀግና አቀባባል አደረገ።
የጅማ ከተማ ህዝብ በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የጀግና አቀባባል አደረገ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) እጅግ በርካታ የከተማዋ ህዝብ በጅማ ስቴዲየም ተገኝቶ አህመዲን ጀበልን የተቀበለው ሲሆን፣ ከህዝቡ የተዋጣውን የገንዘብ ስጦታም አበርክቶለታል። ኡስታዝ አህመዲን “ ከዚህ በሁዋላ ውሸታም መሪ፣ አስመሳይ አስተዳደር የኢትዮጵያ ህዝብ አይፈልግም። እኔ ሁሉንም ዘር ሃይማኖት ሳልለይ እውዳለሁ። ኦሮሞ ነኝ፣ ሙስሊም ነኝ፣ ሰው ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ...
Read More »ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ አደረጉ
ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) የረሃብ አድማው “ግንቦት 20 ለባርነት የተዳረግንበት ቀን ነው፣ እየተሰቃየን ያለነው በግንቦት 20 ቀን ወደ ስልጣን በወጡት ነው” በሚል ምክንያት መሆኑን ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል። እስረኞቹ ከቂሊንጦ እስር ቤት የሚሰጣቸውን ምግብ “አንቀበልም” በማለት መልሰዋል። በአሁን ሰዓት ከ250 በላይ የክስ ሂደታቸውን በፍርድ ...
Read More »በፓሪስ ከአራተኛ ፎቅ ቁልቁል ሊወድቅ የነበረን የአራት ዓመት ህጻን ልጅ የታደገው ማላዊ ስደተኛ፣ የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጠው።
በፓሪስ ከአራተኛ ፎቅ ቁልቁል ሊወድቅ የነበረን የአራት ዓመት ህጻን ልጅ የታደገው ማላዊ ስደተኛ፣ የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጠው። (ኢሳት ዜና ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ማሞዱ ጋሴማ የተባለው ይህ ወጣት ማላዊ ከፎቅ ላይ ቁልቁል ሊከሰከስ የነበረን ህጻን በደረቱ ተስቦ በመውጣት የመታደጉ ዜና ከተሰማ በኋላ፣በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንና በመላው ፈረንሳውያን ዘንድ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ተችሮታል። በኤሊሴ በሚገኘው ቤተሰምንግስ ከፕሬዚዳንት ማክሮን ጋር ከተገናኘም በኋላ የፈረንሳይ ...
Read More »የሕጻን ሕይወት የታደገው ማሊያዊ የፈረንሳይ ዜግነት አገኘ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 20/2010) ከአራተኛ ፎቅ ሊወረወር የነበረውን ሕጻን ሕይወት የታደገው ማሊያዊ የፈረንሳይ ዜግነት አገኘ በአካባቢው ሰው ተሰብስቦ የደረሰው ማሊያዊው ወጣት የሕጻኑን ሁኔታ ሲያይ ጊዜም አላባከነም አራቱን ፎቅ በፍጥነት በመውጣት የሕጻኑን ሕይወት ታድጎታል ብሏል የቢቢሲ ዘገባ። የመገናኛ ብዙሃንን ቀልብ የሳበው ማሊያዊው ማሞዱ ጋሳማ የተባለው ወጣት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም ምስጋና ተችሮታል። በኤልሴ ቤተመንግስት በክብር ጠርተው ጋሳማን ያናገሩት ማክሮን ይህ ወጣት የትውልደ ...
Read More »የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ መቱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 20/2010) በግንቦት 20 ቀን የፖለቲካ እስረኞች የርሃብ አድማ ማድረጋቸው ተሰማ። የርሃብ አድማውን ያደረጉት በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች መሆናቸውም ታውቋል። እስረኞቹ የረሃብ አድማ ያደረጉት “ግንቦት 20 ለባርነት የተዳረግንበት ቀን ነው በሚል እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በአሁኑ ወቅት ከ250 በላይ እስረኞች በሽብር ስም ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ። እነዚሁም የፖለቲካ እስረኞች መሆናቸው ነው የተነገረው። እስረኞቹ ከቂሊንጦ እስር ቤት ...
Read More »ኢሕአዴግ የመሰነጣጠቅ እና የመከፋፈል አደጋ ይገጥመዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 20/2010) ኢሕአዴግ የመሰነጣጠቅ እና የመከፋፈል አደጋ እንደሚገጥመው የኢሕአዴግ የቀድሞ መሪዎች ገለጹ። ትምክህተኛ እና ጠባብ የሚሉ ቃላትን መጠቀም ነውር የሆነበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብተናል ብለዋል። የሕወሃት መስራች እና ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ስዩም መስፍን ፣የሕወሃት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከብአዴን አቶ ሕላዊ ዮሴፍ በመሩት የመቀሌው ስብሰባ በቅርቡ በጡረታ የተሰናበቱት ዶክተር ካሱ ኢላላን ጨምሮ ጥቂት ነባር ...
Read More »በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የአቶ መላኩ ፋንታና ሌሎችም ባለስልጣኖች ክስ ተቋረጠ
በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የአቶ መላኩ ፋንታና ሌሎችም ባለስልጣኖች ክስ ተቋረጠ (ኢሳት ዜና ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ በሙስና ወንጀል ተጠርትረው በእስር ቤት የቆዩት አቶ መላኩ ፋንታ ክሳቸው እንዲቋረጥ አቃቢ ህግ ጠይቋል። አቶ መላኩ ፋንታ በሴራ ፖለቲካ እንደታሰሩ የሚያመለክቱ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲለቀቁ ቆይቷል። ለውጥ ፈላጊ የብአዴን የአመራር አባላትም አቶ መላኩ ከእስር እንዲፈቱ ...
Read More »በቡራዩ የፈረሰው መስጂድና በህዝቡ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ኡዝታዝ አቡበክር አህመድ አወገዙ
በቡራዩ የፈረሰው መስጂድና በህዝቡ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ኡዝታዝ አቡበክር አህመድ አወገዙ (ኢሳት ዜና ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) “በቡራዩ ከተማ በልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ ፍሪዶሮ “ፀበል ማዶ” ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሙስሊሙ ሲገለገልበት የነበረው መስጂድ በታጠቁ የመንግስት ሃይሎች እንዲፈርስ መደረጉ ብሎም በንፁሃን የአካባቢው ሙስሊሞች ላይ የተወሰደው ኢ ሰብአዊ የሃይል እርምጃ ሃገራችን በአዲስ የለውጥ ጎዳና ላይ ገብታለች የሚለውን እሳቤ ጥላሸት የሚቀባና ሙስሊሙ ...
Read More »ትምህርት ሚኒስቴር የሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢን ከስልጣን አነሳ
ትምህርት ሚኒስቴር የሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢን ከስልጣን አነሳ (ኢሳት ዜና ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የስልጣን መልቀቂያ አስገብተው በቅርቡ ከሃላፊነት ከተነሱት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው የነበሩት የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ስለሺ ጌታሁን ከስልጣን ተነስተው በምትካቸው የኦህዴድ የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ሰሎሞን ኩቹ ተመድበዋል። አቶ ስለሺ ከግዢ ጋር በተያያዘ በሙስና ይወነጀላሉ። በተማሪዎች ላይ ሲደርስ ለነበረው ጥቃት ተጠያቂ ...
Read More »