ትምህርት ሚኒስቴር የሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢን ከስልጣን አነሳ

ትምህርት ሚኒስቴር የሃረማያ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢን ከስልጣን አነሳ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የስልጣን መልቀቂያ አስገብተው በቅርቡ ከሃላፊነት ከተነሱት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው የነበሩት የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ስለሺ ጌታሁን ከስልጣን ተነስተው በምትካቸው የኦህዴድ የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ሰሎሞን ኩቹ ተመድበዋል።
አቶ ስለሺ ከግዢ ጋር በተያያዘ በሙስና ይወነጀላሉ። በተማሪዎች ላይ ሲደርስ ለነበረው ጥቃት ተጠያቂ መሆናቸውና ከአዲሱ የኦህዴድ አመራር ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በዚህ አቋማቸው ከኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ ታግደው ቆይተዋል።