(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010) የቀድሞው መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኮለኔል ጎሹ ወልዴ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፉ ገለጸ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎናቸው እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርበዋል። “ዝምታዬን የሰበርኩት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ራዕይ እንዲሁም የለውጥና የተሃድሶ አጀንዳ ለመደገፍና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቼም እንዲደግፉት ለማሳሰብ ነው።”በማለት የ6 ደቂቃ የድምጽ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እግዚአብሔር ግዜውን ጠብቆ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያጫቸውና የመረጣቸው ግለሰብ ናቸው ብዬም ...
Read More »Author Archives: Central
የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያና ኤርትራን የሰላም ሂደት እደግፋለሁ አለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010)የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያና ኤርትራ ለጀመሩት የሰላም ሂደት ድጋፉን እንደሚያደርግ ገለጸ። የመንግስታቱ ድርጅት ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ለጀመሩት ስራ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዩ ጉተሬዝ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል የጀመሩት በጎ ስራ የሚደነቅ ነው ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሁለቱን ወንድማማች ሀገራት ...
Read More »የኤርትራና የኢትዮጵያ ግንኙነት መሻሻሉ ለአፍሪካው ቀንድ ሰላም አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010) የኤርትራና የኢትዮጵያ ግንኙነት መሻሻሉ ለአፍሪካው ቀንድ ሰላም አስተዋጽኦው ከፍተኛ እንደሚሆን በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር ገለጹ። አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ ላይ እንደገለጹት ለ20 ዓመታት የዘለቀው የሁለቱ ሃገራት ፍጥጫ የሚያበቃበት ምዕራፍ ተጀምሯል። ይህ ደግሞ ለአፍሪካው ቀንድ ሰላም ወሳኝ እንደሆነ አምባሳደሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ልብ ናት ያሉት አምባሳደር እስጢፋኖስ ልብ ሲታመም ቀጠናው በሙሉ ይጎዳል። ኢትዮጵያ ሰላም ስትሆን ...
Read More »የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ብድር መክፈል ያቆሙ ተበዳሪዎች ቁጥር ጨመረ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 13/2010) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያልተመለሰ እዳ ወይንም ብድሩንም ሆነ ወለዱን መክፈል ያቆሙ ተበዳሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተገለጸ። የመንግስት የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል መሰብሰብ ያልቻለ ብድር 28 በመቶ ደርሷል ሲሉ ገልጿል። የኢሳት ምንጮች ግን ያልተሰበሰበው የብድር መጠን 70 በመቶ መድረሱን አጋልጠዋል። ይህ ደግሞ ባንኩ አደጋ ላይ እየወደቀ ለመሆኑ አመላካች ነው ተብሏል። መንግስት ችግሩን ለመፍታትም ...
Read More »በአዲስ አበባ የተጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ ፍቃድ አገኘ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 13/2010) በአዲስ አበባ ለመጭው ቅዳሜ የተጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ በከተማው አስተዳደር ጽሕፈት ቤት እውቅና እንደተሰጠው ታወቀ። ጽሕፈት ቤቱ ሕገመንግስቱ ከሚደነግገው አሰራር ውጭ በእውቅና መስጫ ደብዳቤው ለሰልፉ ፈቃድ ሰጥቻለሁ ማለቱም ተገልጿል። “ለውጥን እንደግፍ ዲሞክራሲን እናበረታታ”በሚል መርህ በተጠራው ሰልፍ በአዲስአበባ በሚሊየኖች የሚቆጠር ሕዝብ ይገኛል ተብሎም ይጠበቃል። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰልፉ መንግስትን ለመደገፍ የተጠራ ነው ማለቱን አስተባባሪዎቹ ትክክል አይደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምቷል። ...
Read More »የወልቂጤ ነዋሪ ህወሃትን በማውገዝ ተቃውሞ አሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 13/2010)ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቀባበል የወጣው የወልቂጤ ነዋሪ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ህወሃትን በማውገዝ ተቃውሞ ማሰማቱ ተገለጸ። በቅርቡ በወልቂጤ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ህዝቡን ለማነጋገር ወደ አካባቢው ያመሩት ዶክተር አብይ አህመድም በሀዋሳ፣ በወላይታና ወልቂጤ በደረሱት ግጭቶች እጃቸው ያለበት የመንግስት ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱና በህግ እንደሚጠየቁም አስታውቀዋል። የወልቂጤ ነዋሪ በቅርቡ የተከሰተው ግጭት የህወሃት እጅ እንዳለበት በመግለጽ ተቃውሞውን ማቅረቡ ተሰምቷል። በተያያዘ ዜና ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የትጥቅ ትግሌን ላቆም እችላለሁ አለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 13/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ የሰጡትን የዲሞክራሲ ተስፋ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ የትጥቅ ትግሉን ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ። ንቅናቄው የሰለጠነ ፖለቲካ የምንመርጠው፣የምናውቀውና የምመኘው የትግል ስልት ነው በሚል ባወጣው መግለጫ እንዳለው አርበኞች ግንቦት ሰባት የመሳሪያ ትግልን ዋነኛ የትግል ስትራቴጂው በማድረግ የፖለቲካ ስልጣን የመያዝ አላማ ኖሮት አያውቅም። ሆኖም ግን አገዛዙ ይከተለው በነበረው ኋላ ቀር ፖለቲካ ምክንያት ዜጎች ...
Read More »ኤርትራ ወደ አዲስ አበባ የልኡካን ቡድኗን ልትልክ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 13/2010) ኤርትራ ወደ አዲስ አበባ የልኡካን ቡድን እንደምትልክ አስታወቀች። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ በተከበረው የሰማዕታት ቀን ላይ ወደ አዲስ አበባ ስለሚልኩት የልኡካን ቡድናቸው በይፋ መናገራቸውም ታውቋል። በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ለውጥ ቀልብ የሚስብ ነው በማለት የገለጹት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ ሃገራት መካከል ለሚደረገው ገንቢ ውይይት የልኡካን ቡድናቸው ወደአዲስ አበባ ያመራል ብለዋል። የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሽ የመጣው የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ...
Read More »የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ አንድ የልኡካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩ አስታወቁ
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ አንድ የልኡካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩ አስታወቁ (ኢሳት ዜና ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት በየዓመቱ በሚከበረው የሰማዕታት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግር ነው። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ሁኔታ አዲስ ትብብር ለመመስረት ምቹ ነው ብለዋል። ህወሃት የውጭ ሃይሎችን አጀንዳ ለማራመድ ባደረገው ጥረት በሁለቱ አገራት መካከል ግጭት መቀስቀሱን የተናገሩት አቶ ኢሳያስ፣ ...
Read More »የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለጠ/ሚኒስትሩ አቀረቡ
የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለጠ/ሚኒስትሩ አቀረቡ (ኢሳት ዜና ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ስብሰባ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል። “የጉራጌ ህዝብ የክልል ጥያቄ መልስ ያግኝ፣ የጉራጌ ምሁራንን ማግለል ለምን ተፈለገ? ጉራጌን ከንግድ አለም ለማስወጣት አሻጥር ሲፈጸምበት ደኢህዴን የት ነበር? በቀቢናና ጉራጌ ብሄረሰቦች መካካል ግጭት የቀሰቀሱት ለፍርድ ይቅረቡ” የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ዶ/ር አብይ ሰሞኑን በክልሉ ግጭት የቀሰቀሱ አካላት ...
Read More »