(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) በምዕራብ ጎጃም የቻግኒ ከተማ ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ አደረገች። የድጋፍ ሰልፉ በዳውሮና በሌሎችም የደቡብ ክልል አካባቢዎች መካሄዱ ታውቋል። አርባምንጭ ለነገው የድጋፍ ሰልፍ የሚደረገውን ዝግጅት የከተማዋ አመራር እያደናቀፈ መሆኑ ተገለጿል። በውጭ ሀገራትም በኢትዮጵያ የሚታየውን የለውጥ ጅምር በመደገፍ ሰልፎች መካሄዳቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በጄኔቫ ስዊዘርላንድ፣ በስቶክሆልም ስዊዲን፣ በካናዳ ቶሮንቶ ኢትዮጵያውያን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ድጋፋቸውን አሳይተዋል። ቻግኒ ዛሬ የህወሀት ...
Read More »Author Archives: Central
የተፈጠረውን ሁኔታ ለማደፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎች የትም አይደርሱም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማደፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎች የትም የማይደርሱ፣መንግስት የሚያውቃቸውና የሚቀጣቸው ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። እነዚህ ርምጃዎች ባዶ ፍላጎቶች እንጂ ለውጥን ማቆም የሚችሉ አይደሉም ብለዋል። በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ዛሬ በፓርላማ ቀርበው የ2011 በጀት ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ለቀጣዩ በጀት አመት ዛሬ 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በጸደቀበት የፓርላማው ...
Read More »አሁን የሚታዩት ግጭቶች ለውጥ ማቆም የሚችሉ አይደሉም ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ
አሁን የሚታዩት ግጭቶች ለውጥ ማቆም የሚችሉ አይደሉም ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትሩ በ2011 ረቂቅ በጀት ላይ ለመወያየት ፓርላማ ተገኝተው ከአባላቱ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት መልስ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማድፍረስ እዚህም እዛም ሙከራዎች ቢኖሩም፣ የትም አይደርሱም ብለዋል። እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መንግስት የሚያውቀውና የሚቀጫቸው ናቸው ያሉት ጠ/ሚኒስትር አብይ፣ ያሉት ባዶ ፋላጎቶች እንጅ አጠቃላይ ለውጥ ማቆም የሚችልዩ አይደሉም ...
Read More »ያኮረፉ የኦህዴድ አባላት ለውጡን ለመቀልበስ ከሚንቀሳቀሱት ሃይሎች ጋር ጥምረት ፈጥረው እየሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ተናገሩ
ያኮረፉ የኦህዴድ አባላት ለውጡን ለመቀልበስ ከሚንቀሳቀሱት ሃይሎች ጋር ጥምረት ፈጥረው እየሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ኦህዴድ ግጭት በመፍጠር፣በሙስናና በህዝቡ ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ያባረራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ አባላች፣ የለውጡን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ እየሞሩ ካሉ ሃይሎች ጋር አብረው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። እነዚህ የተባረሩ የኦህዴድ አባላት የለማ እና የአብይን መሪነት ከሚቃወሙ ሃይሎች ...
Read More »ኦነግ በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ የሚካሄደውን ጦርነት ህዝቡ እንዲያከሽፈው ጠየቀ
ኦነግ በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ የሚካሄደውን ጦርነት ህዝቡ እንዲያከሽፈው ጠየቀ ድርጅቱ አቶ ለማንና ዶ/ር አብይንም አውግዟል (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ባወጣው መግለጫ በቄለም ወለጋ ውስጥ “ ለምን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እንቅስቃሴን ትደግፋላችሁ?” በማለት የጦር ሃይሉ ግዳጅ ወስዶ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ዘመቻው በኦሮምያ ክልል መስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ትእዛዝና እውቅና እንዲሁም በጄኔራል ገብሬ ...
Read More »የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች 700 ሜትር ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን ገለጹ
የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች 700 ሜትር ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን ገለጹ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች በባህርዳር ከተማ ተይዞ የተወጣውን ባንዲራ የሚበልጥ ረጅም ባንዲራ በመያዝ ዶ/ር አብይ አህመድ እያደረጉ ላሉት የለውጥ እንቅስቃሴ ድጋፉን ገልጿል። የመተከል ከተማ ነዋሪዎች ፣ በአውራጃቸው የሚፈናቀሉና የሚገደሉ ወገኖች ሰቆቃ ይቁም፣ አገር በጭንቅላት እንጅ በአፈሙዝ አይገዛም የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በመያዝ ወደ ...
Read More »በሲዳማ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የዞኑ አስተዳደሪና ከንቲባው ስልጣን ለቀቁ
በሲዳማ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የዞኑ አስተዳደሪና ከንቲባው ስልጣን ለቀቁ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ የሲዳማ አመታዊ በአል ጨምበለላ በተከበረበት ወቅት በተቀሰቀው ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ወደ ሃዋሳ ያቀኑት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ በግጭቱ እጃቸው ያለበት ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ በጠየቁት መሰረት የዞኑ አስተዳደሪ አቶ አክሊሉ አዱላ እና የሃዋሳ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ ስልጣናቸውን ለቀዋል። ግለሰቦቹ ለፍርድ ...
Read More »አሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ነው
አሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የትራምፕ አስተዳደር ቻይና ወደ አሜሪካ በምትልካቸው እቃዎች ላይ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ የቀረጥ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ ፣ ቻይናና ሩስያ ተመሳሳይ እርምጃዎችን ወስደዋል። ቻይና በአለማችን የተከሰተ ታላቁ የኢኮኖሚ ጦርነት ስትል የአሜሪካንን ውሳኔ አደገኝነት ገልጻለች። አሜሪካ 34 ቢሊዮን ዶላር በሚደርስ የቻይና ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ጭማሪ ስታደርግ፣ ...
Read More »የዲላ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ስልጣናቸውን ለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 28/2010) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በጌዲዮዎች ላይ የደረሰው ጥቃትና መፈናቀል ትኩረት ተነፍጎታል በማለት የዲላ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት በተቃውሞ ስልጣናቸውን ለቀቁ። 700 ሺ ያህል ዜጎች የተፈናቀሉበት፣ብዙዎች የተገደሉበትና የቆሰሉበት የጉጂ ዞን ግጭት በሽምግልና እንደተፈታ ቢገለጽም ችግሩ ግን መፍትሔ አለማግኘቱ ተመልክቷል። ወራት ላስቆጠረው የጌዲዮዎች መፈናቀልና ግድያ የፌደራል መንግስትም ሆነ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቂ ትኩረት አልሰጠም ብለዋል የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ቃልኪዳን ነጋሽ። በዚህም ...
Read More »ዶክተር ካሳ ከበደ በሃገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 28/2010) ዶክተር ካሳ ከበደ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በሃገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ። ከ27 አመታት ስደት በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ አዲስ አበባ የገቡት ዶክተር ካሳ ከበደ ወቅታዊ በሆኑ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 አዲስ አበባ የገቡትና በዕለቱም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የተወያዩት ዶክተር ካሳ ከበደ ከጠቅላይ ሚኒስትር ...
Read More »