ዶክተር ካሳ ከበደ በሃገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 28/2010) ዶክተር ካሳ ከበደ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በሃገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

ከ27 አመታት ስደት በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ አዲስ አበባ የገቡት ዶክተር ካሳ ከበደ ወቅታዊ በሆኑ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 አዲስ አበባ የገቡትና በዕለቱም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የተወያዩት ዶክተር ካሳ ከበደ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር የተወያዩት ትላንት ረቡዕ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

ዶክተር ካሳ ከበደ በቀድሞ መንግስት ውስጥ በሚኒስትርነትና አምባሳደርነትን ጨምሮ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።