ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህብር ራዲዮ ከላስቬጋስ እንደዘገበው፤የመገንጠል ሀሳቡን ከፕሮግራሙ ያወጣው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ በአሁኑ ወቅት የግንባሩ ዋነኛ ዓላማ በተባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ ክንድ ወያኔን በማንበርከክ ለህዝቡ ጥያቄ እንዲገዛ ማድረግ መሆኑን በድጋሚ በማረጋገጥ፤ ህዝቡ ሳይከፋፈልና ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። እንደ ህብር ዘገባ፤ጄኔራል ከማል ይህን ጥሪ ያቀረቡት፤እሳቸው የሚመሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፤ በቅርቡ የመገንጠል ፕሮግራሙን ...
Read More »Author Archives: Central
ኢሳትን ለመደገፍ በቦስተን የተዘጋጀው የእራትና የመዝናኛ ምሽት የተሳካ እንደነበር ኮሚቴው አስታወቀ
ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ የገና በአልን በማስመልከት እና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳትን) ለመደገፍ በቦስተን የተዘጋጀው የእራትና የመዝናኛ ምሽት በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት እና ኢሳትንም ለመደገፍ በርካታ ገንዘብ የተሰበሰበበት እንደነበር ኮሚቴው አስታወቀ አርቲስት ታማኝ በየነ በሚታወቅበት ተመልካቾቹን በተለያየ ስሜት ውስጥ በሚከተው በቭድዮ መረጃዎች እና ቀልዶች በሚዋዛው ንግግሩ ሃገራችን ያለችበትን ሁኔታ ለዝግጅቱ ታዳሚዎች አስረድቷል! ንግግሩን የጀመረው ቦስተን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እጅግ ...
Read More »ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች ያለፈቃዳቸው ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲነሱ ተደርጓል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ክስ አቀረበ
ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የሰብአዊ መብቶች አቀንቃኝ ድርጅት “ሞትን እዚህ እየጠበቅን ነው፤ በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል ሰዎች በሀይል ከቦታቸው እየተፈናቀሉ በመስፈር ላይ ናቸው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ የመለስ መንግስት ሰፈራ በሚባለው መርሀ ግብር ከ70 ሺ በላይ የጋምቤላ ተወላጆችን ከቀያቸው አፈናቅሎ፣ ምግብ፣ የእርሻ መሬት፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎት በሌለበት ቦታ አስፍሯቸዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በሰፈራው አንሳተፍም ባሉት ሰዎች ላይ የሀይል ...
Read More »ፈኖተ ነጻነት ያሳለፍነው ሳምንት በመላ አገሪቱ ውስጥ ውጥረት የሰፈነበት ነበር አለ
ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነጻነት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውጥረት ሰፍኖ መሰንበቱን አስነብቧል። በምእራብ ጎጃም ዞን በአዴት ከተማ ቤት ከማፍረስ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ አንድ የወረዳ ባለስልጣን መገደሉንና ሎሎች ሶስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጧል። በአሁኑ ጊዜም ህዝቡ ቤቱን ላለማስፈረስ በመወሰኑ፣ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑን ጋዜጣው ዘግቧል። በጅማ ዩኒቨርስቲ ደግሞ አንድ የግቢው ሰራተኛ የተወሰኑ ተማሪዎችን ሰብስቦ እናንተ ...
Read More »በእስራኤል ኢትጵያዊቷ ከስራ ሃላፊነቷ በዘረኝነት ምክንያት መነሳቷ እያነጋገረ ነዉ
ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእስራኤል ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ከስራ ሃላፊነቷ እንድትነሳ ያደረጋት የኢትዮጵያዊቷ ፀጋ መላኩ ጉዳይ ከዘረኝነት ጋር የተያያዘ መሆኑን የቴል-አቪቭ የጋዜጠኞች ማህበር ዳይሬክተር ዮሲ ባርሞሃ መናገራቸዉን ጀሩሳሌም ፖስት የተባለዉ ጋዜጣ ገልጿል። ፀጋ መላኩ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት/እስራኤላዊ በመሆን የእስራኤል ረሸት አሌፍ የራዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር በመሆን ለሶስት አመታት በኮንትራት ስታገለግል የቆየች ሲሆን በሙያና ተግባሯ እጅግ ተቀባይነትን አግኝታ እንደነበር ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ ...
Read More »የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት የሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ
ጥር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በለድ-ዌይን በተባለዉ የማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ክልል ዉስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ሁለት የሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን ኦጋዴን ቱዴይ የዜና ምንጭ ከናይሮቢ ገለፀ። በቁጥጥር ስር የዋሉት የሶማሊያ የሽግግር መንግሰት ተባባሪ የሆነዉ የአህሉ ሱና ሱፊ ፓራ ሚሊቴሪ ቡድን መሪ አዳን አዋሌና ከፊል ራስ ገዝ የሆነዉ የሸበሌ ሸለቆ አስተዳዳሪ አብዱል ፈታህ ሃሰን ጃማ ናቸዉ። መሪዎቹን የኢትዮጵያ ...
Read More »በጋምቤላ ሲካሄድ የሰነበተው ግምገማ አነጋጋሪ ሆኗል ሲል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ገለጠ
ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ሲካሄድ በሰነበተው ግምገማ ከሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ ውጪ መወሰኑ አነጋጋሪ ሆኗል ሲል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ገለጠ፣ የኢሳት የጋምቤላ ምንጮች ግን ፕሬዚዳንቱም በቅርቡ ከስልጣን ይወርዳሉ ይላሉ። ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ዜና የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋሕአዴን/ ከፌደራል ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት በተላኩት አቶ ዘመዴ ዘመድኩንና አቶ አለባቸው ንጉሤ አማካይነት ከታህሳስ 17 ቀን ...
Read More »የአወልያ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዛሬ ትምህርት ጀምረዋል፣ ኮሌጁ ግን አሁንም እንደተዘጋ ነው
ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአወልያ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና እና የአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት ትምህርታቸውን አቋርጠው የተለያዩ ሀይማኖታዊ መብቶችን ሲጠይቁ ነበር። ተማሪዎች መንግስት አንዳንድ ጥያቄያቸውን በመመለሱ እና ቀሪዎችን ጥያቄዎቻቸውን በመረጡዋቸው ወኪሎች አማካኝነት ለመጠየቅ በመስማማት በዛሬው እለት ትምህርት ጀምረዋል። ተማሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጡት ምንም እንኳ አብዛኞቹ ጥያቄዎቻቸው፣ በተለይም መጅሊስ እንዲፈርስና አህባሽን ያማስፋፋት ተልእኮው እንዲቋረጥ ያቀረቡት ጥያቄ ባይመለስም ፣ አስተማሪዎቻቸው ...
Read More »በሳኡዲ አረቢያ በፖሊስ ቁጥጥር ውለው ወደ እስር ቤት ከተጋዙት 35 ኢትዮጵያውያን መካከል ሦስቱ ሞቱ
ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳኡዲ አረቢያ-ሪያድ ውስጥ የገናን በዓል ለማክበር በተሰበሰቡበት በፖሊስ ቁጥጥር ውለው ወደ አስፈሪ እስር ቤት ከተጋዙት 35 ኢትዮጵያውያን መካከል ሦስቱ በእስር ቤት ውስጥ መሞታቸውን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘገበ። ዘጋቢያችን እንዳረጋገጠው፤ የገናን በዓል ለማክበር በመሰብሰባቸው ሳቢያ ለ እስር ከተዳረጉት 35 ኢትዮጵያውያን መካከል፤ ህፃናት 29ኙ ሴቶች ናቸው። ከነዚህ ሶቶች መካከል ብዙዎቹ የሚጠቡ ህፃናት ልጆቻቸውን በቤታቸው ትተው ...
Read More »በመጪዎቹ 100 ዓመታት ውስጥ ይፈጸማሉ ስለተባሉት ነገሮች ምን ሰምተዋል? ይላል ቢቢሲ
ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ፕርሰን እና ቱከር የተባሉ ተምባዮች በመጪዎች መቶ አመታት ውስጥ ምን ምን አይነት ለውጦችን ትጠብቃላችሁ ብለው ላቀረቡት ጥያቄ፣ አስተያየት ሰጪዎች የሚከተሉትን ብለዋል። ውቅያኖሶች ለአሳ ምርት ብቻ ሳይሆን የአረንጓዴ ሀይል ምርትን ለመጨመር እንዲሁም እያደገ የመጣውን ህዝብ ለመመገብ ይታረሳሉ። በድምጽ ወይም በድርጊት ሳይገልጡ ሀሳብን በማወቅ ብቻ ለመግባባት የሚያስችሉ መሳሪያዎች ይፈጠራሉ። ሳይንቲስቶች ለዘላለሙ የማይሞቱ እና እጅግ ...
Read More »